እኔ እርሳስ በ ሊኦናርድ ሪድ (I Pencil by Leonard Read)

Image

 “I Pencil” is a superb case study of free markets in action. Half of the world’s economic problems would vanish id every one would read “I,Pencil.”

Burton W.Wolfsom,Jr.

Profesor of History

Hillsdale College

 

 “I, Pencil,” as become a classic, and deservedly so.  I know of no other piece of literature that so succinctly, persuasively, and effectively illustrates the meaning of both Adam Smith’s invisible hand-the possibility of cooperation without coercion.

Milton Friedman

Nobel Laureate,1976

 

እኔ የሊድ (lead) እርሳስ Pencil) ነኝ፡፡ያዉም ተራ የእንጨት እርሳስ-ማንበብ እና መጻፍ የሚችሉ ወንዶች ና ሴቶች ልጆች እንዲሁም ጎልማሶች ሁሉ ሚያዉቁኝ፡፡መጻፍ ሙያየ ነዉ፤ሙያየም አይደለም፡፡በቃ ይህ ነዉ ስራዮ፡፡ስለዘር ሀረግ እጽፋለሁ፡፡ለምን እንደምጽፍ ሊገርማችሁ ይችላል፡፡ታሪኬ መሳጭ መሆኑን በመናገር እጀምራለሁ፡፡በመቀጠል ደግሞ ከዛፍ ወይም ከጸሃይግባት ወይም ከመበረቅ ብልጭታ የላቅሁ እንቆቅልሽ (mystry)መሆኔን እናገራለሁ፡፡ይሁን እንጂ የሚጠቀሙኝ ሰዎች እኔን ከቁብ እንደማይቆጠር የተራ ክስተት ዉጤት ና መሰረት የለሽ ነገር አድርገዉ መመልከታቸዉ ያሳዝናል፡፡በዚህ አንዱን ከሌላዉ አሳንሶ የመመልከት አባዜ የተነሳ ሰዎች እኔን ከተራነት ጎራ መድበዉኛል፡፡የሰዉ ልጅ እየፈጸመ ያለዉ ይህ ከፍተኛ ስህተት ራሱን ከክፉ አደጋ ዉስጥ አዉጥቶ ረጅም ዘመን መኖር እንዳይችል አድረጎታል፡፡ብልሁ ጂኬ ቼስተረቶን ትዝብቱን ሲገልጽ‹እጹቦችን ትተን እጹብን ፍለጋ ስንባዝን እንጠፋለን›ይላል፡፡

 

   እኔ እርሳስ፡ቀላል (ተራ) መስየ ብታይም፡አድናቆት እና አክብሮት ይኖራችሁ ዘንድ እዉነታዉን በማስረዳት ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡በርግጥ ይህ የሚሆነዉ ልትረዱኝ ከቻላችሁ ነዉ፡፡ይህማ ይቅር፡፡እንድትረዱኝ መጠየቅ ብዙ ማስቸገር ይሆንብኛል፡፡ይልቅ በተአምራዊነቴ የምወክለዉን ተምሳሌት መገንዘብ ከቻላችሁ ይበቃል፡፡ያኔ የሰዉ ዘር በመከፋት እያጣ ያለዉን ደስታ መልሶ እንዲጎናጸፍ እና ነጻነቱን እንዲታደግ አጋዡ ትሆናላችሁ፡፡እናም የማስተምረዉ ታላቅ ትምህርት አለኝ፡፡ይህን ትምህርት ሳስተምር አዉቶሞቢል ወይም አይሮፕላን ወይም ሳሕን ማጠቢያ ማሽን ማስተማር ከሚችለዉ በላይ አስበለጬ ነዉ -አዎ፡ምክንያቱም ለሰዎች በጣም ቀላል እመስላለሁና፡፡

   ቀላል……አይምሰላችሁ! እኔ እንዴት እንደምፈጠር (እንደምሰራ) በብቸኝነት ሊያዉቅ የሚችል ግለሰብ በገጸምድር ላይ ቢፈለግ ጨርሶ ሊገኝ አይችልም፡፡ይህን ስላችሁ የማይመስል ተአምር ይመስላችኋል አይደል? በተለይ ደግሞ በየአመቱ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን የሚሆን እኔን መሰል ማለትም እርሳስ በሃገር አሜሪካ የሚመረት መሆኑን ስትገነዘቡ ይደንቃችኋል፡፡

    እስቲ በእጃችሁ ብድግ አድረጉና ሁለመናየን ተመልክቱ፡፡ምን አያችሁ…….አይን የማይሞላ ነገር–የሆነ እንጨት ፡ደረቅ የቀለም ቅብ ፡መለያ ጽሁፍ ፡የግራፋይት ሊድ (graphite lead) ፡ መናኛ ብረት ና ላጲስ፡፡

 

ይቀጥላል…

One thought on “እኔ እርሳስ በ ሊኦናርድ ሪድ (I Pencil by Leonard Read)

  1. Pingback: እኔ እርሳስ ክፍል 4 – ስለእኔ ጠንቅቆ የሚያውቅ ማን ይሆን? | tmuv

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.