ታላቁ ሳይንቲስት፡-አልበርት አንስታይን! 

ታላቁ የቲወረቲካል ፊዚክስ ሊቅ፣ የሰላም መልክተኛ እና አቻ ያልተገኘለት ጂኒየስ ‘በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ’ ከተያዘ ሰንብቷል። ከሌቱ 7 ሰዓት፡ከ15 ደቂቃ ሚያዚያ 18 ቀን 1955ዓ/ም ይህ ድንቅ ሳይንቲስት በፕሪንስተን ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል በተኛበት አልጋ ላይ ሆኖ አጠገቡ ላለችው ነርስ ቶሎ ቶሎ የሆነ ነገር አወራት። ነርሷ ጀርመንኛ ቋንቋ አስተርጓሚ ለመጥራት በወጣችበት ሰዓት የታላቁ ሳይንቲስት ነፍስ ከስጋው ተለይታለች። ከተናገራቸው ጀርመንኛ ቃላቶች ውስጥ ነርሷ ‘አንጎል’ ‘ሞት’የሚሉትን የጀርመነኛ ቃላት ብቻ በመያዟ ‘ምናልባትም ስለ አንጎልና ሞት ግንኙነት አንዳች ነገር ብሎ ይሆናል።” የሚል ግምት አለ። ያም ሆኖ ሳይንቲስቱ ለማንም ወደማይቀረው ሞት ሄዷል። በሞቱ ማግስት ከሲያት በኋላ እዚያው ኒውጀርሲ ውስጥ የአንስታይን በድን በሳጥን ተደርጎ እንዲቃጠል ተደርገ። በሚቀጥለው ቀን ጧት የአልበት አይንስታይን ልጅ ሃንስ አልበርት የታላቁን ሳይንቲስት ሞት በማስመልከት ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ይዞት የወጣውን ፅሁፍ አንብቦ ሳይጨርስ ጋዜጣውን ወርውሮ ወደ ፕሪንስተን ዩኒቨርስቲ ሮጠ።

ኒው ዮርክ ታይምስ ላይ ያነበበው ፅሁፍም እውነት ሆኖ አገኘው። ሃንስ በስፍራው ሲደርስ የአይንስታይንን ጭንቅላት ከፍተው አንጎሉን ያወጡት የዩኒቨርስቲው ሳይንቲስቶች የሪሌቲቪቲ ቲወሪ የወለደውን እና ለኒውክሌር ቴክኖሎጅ መሰረት የጣለውን አንጎል በፕላስቲክ ውስጥ አስቀምጠው [አሁን አንች ነሽ ኢ=MC2 የቀመርሽው•••] እያሉ ይደመሙበት ይዘዋል።የአንስታይንን አንጎል ከፍቶ ያወጣው ዶ/ር ቶማስ ሃርቬይ እጅግ የተቆጣውን የአልበት አይንስታይን ልጅ ወደ ቢሮው ወስዶ ለማሳመን ብዙ ጥረት አደረገ። “ከተፈጥሮ እንቆቅልሾች ውስጥ አንዱ የሆነውን የአንተን አባት የታላቅነት ሚስጥር እንመረምር ዘንድ እባክህ ፍቀድልን!?” ሲል ልጁን ተማፀነው። በመጨረሻም ፈቀደለት። ይህ ሰው የአንጎሉ ባለቤት በሆነ ማንግስት የአሜሪካ መከላከያ ሚንስቴር ‘የአንስታይንን አንጎል ወዲህ በል!’ አለው። ሃርቬይ ‘እምቢ!ፍቃድ የተሰጠኝ ለኔ ነው።” አለ። የአይንስታይን አንጎል በቤቱ መኖራቸውን ያወቁ አድናቂዎቹ እና ሳይንቲስቶች ኒውጀርሲ የሚገኘውን ቤቱን ወረሩት። እሱም የቻለውን ያህል ለማስታወሻ እያለ በሳይንሳዊ መንገድ ከደረቀው አንጎል ላይ ጥቂት ጥቂት እየቆረሰ ሲያደል ኖረ። በመጨረሻም ዶ/ር ሃርቬይ ወደ ቤቱ የሚጎርፈውን ሰው ለማቆም የተረፈውን የአንጎል ክፍል ለፕሪንስተን ዩኒቨርስቲ ሜዲካል ሴንተር ወስዶ አስረከበ።አይናቸውን ወደ ዩኒቨርስቲው ያዞሩት የአንስታይን አድናቂዎችን ለመግታትም ዩኒቨርስቲው የሳይንቲስቱን አንጎል ለማንም እንደማያሳይ አስታወቀ።•••

ኣልበይህ በእንዲህ እንዳለ በእስራኤል የሚገኘው ሂብሩ ዩኒቨርስቲ (Hebrew University) የዚህን ድንቅ እና አነጋጋሪ ሳይንቲስት ሃውልት 2 ነጥብ 5 ሜትር ርዝመት ባለውና 350ኪሎ ግራም ክብደት በሚመዝን ነሃስ አስቀርፆ ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ አስመርቋል። አልበርት አይንስታይን የዩኒቨርስቲው መስራች ሲሆን በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይንሳዊ ትምህርት የሰጠውም በዚሁ ዪኒቨርስቲ ውስጥ ነው። ሁሉንም ሳይንሳዊ ፈጠራዎቹን፣ የምርምር ስራዎቹን እና የህትመት ውጤቶቹን የባለቤትነት መብት ከሞቱ ቀደም ብሎ ያወረሰውም ለዚሁ ዩኒቨርስቲ ነው።

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.