ልማታዊ መንግስት እና የኢኮኖሚው ዓይነት

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የደቀቀችውን አውሮፓ ለመገንባት አሜሪካ መልሶ የማቋቋም እቅድ ነደፈች። ይህ የኢኮኖሚ ሪከቨሪ ፕሮግራም ብዙዎቻችን ማርሻል ፕላን በሚል እናውቀዋለን። ስያሜውን ያገኘው በወቅቱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበረው ሴክሬተሪ ጆርጅ ማርሻል ነው። ይህ እቅድ ከሰብዓዊ እርዳታው በተጨማሪ ምዕራብ አውሮፓ በፍጥነት ራሷን እንድትችል የሚያደርጋትን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ቀመር ጭምር ያካተተ ነበር። ምዕራብ አውሮፓ የነፃ ገበያ ስርዓት በክላሲካል ሊበራሊዝም ደምብ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች። ውጤቱም አውቶማቲክ እና ፈጣን ነበር። የምዕራብ አውሮፓ ሰዎች ህይዎት ተሻሻለ። የማይቀር የተባለው የማህበረሰብ ውጥንቅጥ እና አለመረጋጋት ተወገደ። ይህም ለነፃ ማህበረሰብ ተቋማት ግንባታ በሩን በመክፈቱ ዴሞክራሲ በምእራብ አውሮፓ ሊገነባ ቻለ።

በወቅቱ አሜሪካ የምትሰጠውን ገንዘብ ለአውሮፓዊያኑ ሃገራት ለማከፋፈል በሚል የአውሮፓ የኢኮኖሚ ትብብር ድርጅት (Organization for European Economic Cooperation/OEEC) በ1960 እንዲቋቋም አድርጋለች። ይህ ድርጅት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በአውሮፓ የተቋቋመ የመጀመሪያው ዓለም ዓቀፍ ተቋም ነው። ይህ ድርጅት ስሙን ከOEEC ወደ OECD ቀይሮ ዛሬም አለ። ስራው ግን እንደ ድሮው የአሜሪካን እርዳታ ለአውሮፓ ማከፋፈል አይደለም።

አሜሪካ እርዳታ ስትሰጥ እና የማርሻል እቅድ ለአውሮፓዊያኑ ስትነድፍ ያዩት ኢኮኖሚስቶች “እርዳታ እና ለሌሎች ማቀድ” ላይ ቀልባቸውን ጣሉ። እናም የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መገባደዱን ተከትሎ ኢኮኖሚስቶች ትኩረታቸውን ሶስተኛው ዓለም በሚባለው ወይም በኦፊሴል ያላደጉ ሃገራት በሚባሉት የኤዥያ፥አፍሪካ እና ደቡብ አሜሪካ ድሆች ላይ አደረጉ። እነዚህ ስፍራዎች ባብዛኛው ያልተማረ ህዝብ የሚኖርባቸው እንዲሁም ስራ አጥነት በከፍተኛ ደረጃ የተንሰራፋባቸው እና ፈጣን የህዝብ ቁጥር እድገት የሚታይባቸው ከመሆናቸው በተጨማሪ ኢኮኖሚያቸውም ከኋላ ቀር ግብርና ጋር የተሳሰረ ነው። በነዚህ ስፍራዎች የሚኖር ህዝብም በከፍተኛ ግሽበት ኑሮው የተጎዳ፥ የመሰረታዊ ሸቀጦች እጥረት ሰለባ የሆነ፥ ለጥቁር ገበያም ተጋላጭ ሲሆን የህዝብ ሃብትም በገሃድ ሲመዘበር እና ወደ ውጭ ሃገራት ሲሸሽ የሚታየው ከነዚህ አካባቢዎች ነው።

ዋልት ዊትማን የተባለ የMIT ኢኮኖሚስት ሁኔታውን ካጤነ በኋላ በ1960ዓ/ም የፀረ ኮሚኒስት ማኒፌስቶ ነው ያለውን “የኢኮኖሚ እድገት ደረጃዎች፡- የሶስተኛው ዓለም እቅድ” በማለት ፃፈ። ዋልት ዊትማን እንደሚለው ከሆነ ያላደጉ ሃገራት በድህነት አዙሪት ቀለበት የወደቁ ስለሆነ እድገት ከውስጥ ማመንጨት አይቻላቸውም። ስለዚህ መንግስት ይህን የድህነት ቀለበት ጥሶ እስኪወጣ ድረስ መጠነ ሰፊ ፕሮጄክቶች በመንግስት መከናወን አለባቸው ባይ ነው። እንደ ዊትማን ከሆነ ለነዚህ መጠነ ሰፊ ፕሮጀክቶች የሚሆነውን ገንዘብ የዓለም ባንክ በብድር መልክ ሊሰጥ ይገባል። በርግጥ የዓለም ባንክም በዋልት ዊትማን የተነደፈውን የልማታዊ መንግስት እቅድ ተቀብሎ ገንዘብ ሲያበድር ኖሯል።

በዚያን ወቅት ከወደ ለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የሚጮኽውን ሰው ለማድመጥ የወደደ አልነበረም። ይህ ድንቅ ኢኮኖሚስት ፒተር ባወር ነበር። “እባካችሁ! እርዳታ አገር ያሳድጋል ማለት እብደት ነው። በውጭ ኢንቨስትመንት እንጅ በውጭ እርዳታ ያደገ አንድም ሃገር የለም። እርዳታ በድሃ ሃገር ላሉ ባለ ስልጣናት ችሮታ እንጅ ለድሃ ዜጎቻቼው ስጦታ ሊሆን አይችልም። መንግስት ኢኮኖሚውን በሚቆጣጠርበት ሃገር ውጤቱ እድገትና ብልፅግና ሳይሆን ጭቆና፥ሙስና እና ሰቆቃ ብቻ ነው።” በማለት ድምፁን አሰማ።

ልማታዊ መንግስት የሚባለውን እቅድ የተወረው ሰው ዋልት ዊትማን በ1990ዓ/ም ባደረገው ቃለ ምልልስ “የፒተር ባወርን አቋም ስራየ ብየ ባጤነው ኖሮ የእኔ አቋም ስህተት እንደነበር ለማወቅ ሶቬት ህብረት እስክትፈራርስ መጠበቅ ባላስፈለገኝ ነበር።” ብሏል።  የዓለም ባንክም በ1996ዓ/ም ባወጣው From Plan to Market በሚለው ሪፖርቱ ላይ የዋልት ዊትማንን መንገድ መከተሉ ስህተት ላይ እንደጣለው በመግለፅ አቋሙን ከፒተር ባወር ጋር አንድ አድርጓል። በመንግስት ተጠፍንጎ የተያዘ ኢኮኖሚ ማንም ያቅደው ማን ለገበያ ምቹ የሆነ ስርዓትን እስካልፈጠረ እና የነፃ ማህበረሰብ ተቋማት እስካልተገነቡ ድረስ ውጤቱ ከሶሻሊዝም ስርዓት የተለየ አይሆንም።

ያችን ሚጢጢ የኤዥያ ምድር አታውቋት ይሆን? ያችን ትንሽ የድሆች የአሳ ማስገሪያ መንደር መንደር የነበረች። ከሃገሯ መሬት አንዳችም ማዕድን የማይዋጣባት፥ የግብርና ምርቷ 0% የሆነባትን፥ የመጠጥ ውሃ ጉድጓድ እንኳ የሌላት ሃገር። ይህች ሃገር ከውጭ ሃገር ንግድ ሸሪኮቿ በአማካይ ከ1600ኪሎ ሜትር በላይ ትርቃለች። ስታስቡት ይህች ሃገር እንደ ኢትዮጵያ ዓለም የጣለውን ስርዓት ለብሳ የእርዳታ ገንዘብ ሁሉ የሚጎርፍላት አይመስላችሁም? አዎ! ሆንግ ኮንግ ግን እኛ እንደምናስባት አይደለችም።የኢትዮጵያ የቆዳ ስፋት በዚች ሚጢጢ ሃገር ልክ ሲሰላ አንድ ሽህ ሰላሳ ሰባት ሆንግኮንግን የሚያካክሉ ሃገራት ትሆናለች-ትልቋ ኢትዮጵያ! ። ስታስቡት ይህች ሃገር እንደ ኢትዮጵያ ዓለም የጣለውን ስርዓት ለብሳ የእርዳታ ገንዘብ ሁሉ የሚጎርፍላት አይመስላችሁም? አዎ! ሆንግ ኮንግ ግን እኛ እንደምናስባት አይደለችም።እርዳታ አታውቅም። ለምዕራባዊያንም የሆንግ ኮንግ የኢኮኖሚ እድገት ተዓምር ሆኖባቸዋል።

በ1993ዓ/ም በአራቱ የምስራቅ ኤዥያ አናብርት ላይ በተካሄደ የኢኮኖሚ ጥናት ሃገራቱ ተዓምራዊ የኢኮኖሚ እድገት ሊያስመዘግቡ የቻሉት የነፃ ገበያ መርህ ጋር የማይጣረስ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረጋቸው እንደሆን ይገልፃል። ይህ ሃገራቱ ሃብት እንዲያከማቹ እና ያላቸውንም በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲያዉሉ አስችሏቸዋል።

***ዘመኖቹ በሙሉ እንደ ኤሮፓዊያን አቆጣጠር(እኤአ) ናቸው።

One thought on “ልማታዊ መንግስት እና የኢኮኖሚው ዓይነት

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.