ግብር እና ሞት-2

የአሜሪካ ምስረታ የነጻነት ሰነድ ላይ “መንግስት ለዜጎች የሚሰጠው መብት የለም፤የተቋቋመው ቀድሞውኑ የነበራቸውን መብት ለመጠበቅ ነው።” ይላል። ከዚህ መግቢያ ተነስቼ በቀጥታ ወደ ጥንት ልውሰዳችሁማ። አይ! መግቢያ አያሻኝም የሚል ደግሞ ችግር የለውም ወደፊት እንጅ ወደኋላ ለመሄድ የመግቢያ ክፍያ ስለሌለ የጊዜ ፈረስን በጋራ የኋሊት እንጋልብ። ድሮ….ድሮ…..ድሮ…… እንዲህ ሆነ።አዎ! አሁን እየደረስን ስለሆነ ልጓምዎን ጠበቅ አድርገው ይያዙ። እና ያኔ ጥንት … Continue reading ግብር እና ሞት-2

ግብር እና ሞት

መንግስት የዜጎችን ሰላማዊ ህይዎት፣ ነጻነት፣ እና ንብረት የመጠበቅ ግዴታውን ይወጣ ዘንድ ግብር መሰብሰብ ይኖርበታል። ይህ የማይታበል ሃቅ ነው። በግብር መልክ የሚሰበሰበው ገንዘብ ለተለያዩ የጤና፣ የትምህርት፣ የመከላከያ እና ሌሎች ለህዝብ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የመንግስት ወጭዎችን ለመሸፈን ይውላል። በተጨማሪም ግብር ነጋዴው በገበያ ላይ ለማዋል የማይችላቸውን ወይም ለገበያ ለማቅረብ አዳጋች የሆኑ ህዝባዊ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን (ፐብሊክ ጉድስ) ለዜጎች … Continue reading ግብር እና ሞት

የመንግስት ወጭ እና የኢትዮጵያዊያን ኪሳራ

የአንድ ሃገር መንግስት የገቢ ምንጭ ከሃገር ውስጥ የሚሰበስበው ግብር ነው። ሆኖም መንግስት በሚሰበስበው ግብር ልክ ዕቅዶችን አውጥቶ ተፈጻሚ ማድረግ ካልቻለ ልክ አንድ ግለሰብ ከገቢው በላይ የሚፈልገውን ወይም የሚያምረውን ነገር ለማድረግ ሲሞክር ችግር እንደሚደርስበት ሁሉ ችግር ይገጥመዋል። ይህን ጊዜ መንግስት ሌላ ገንዘብ ማግኛ ዘዴ ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ወደ አበዳሪዎች ይሄዳል ማለት ነው። መንግስት ብድር ከሃገር ውስጥ … Continue reading የመንግስት ወጭ እና የኢትዮጵያዊያን ኪሳራ

(By Redeat Bayleyegn)ኢትዮጵያ እና የመንግስት ግዝፈት!

(By Redeat Bayleyegn)ኢትዮጵያ እና የመንግስት ግዝፈት! ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ ከአራት ወራት በፊት ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርገው ነበር:: ስልጠና ቢባል በሚሻለው ስብሰባ ላይ የሚከተለውን ገልፀው ነበር:: እንደ ጠቅላይ ሚንስቴር የመጀመሪያ የስራ ቀናቸው ዕለት ጠረጴዛቸው ላይ የ120 ሰዎች ውጭ ሃገር ሄዶ ለመታከም ማመልከቻ ጠብቋቸዋል:: የመጏጏዣ ቲኬትን አያጠቃልልም:: የነዚህ 120 ሰዎች ጥያቄ ብቻ ሂሳቡ ወደ 6 … Continue reading (By Redeat Bayleyegn)ኢትዮጵያ እና የመንግስት ግዝፈት!

(By Redeat Bayleyegn) የመጀመሪያው መሬት ለአራሹ እና መዘዙ

(By Redeat Bayleyegn) የመጀመሪያው መሬት ለአራሹ እና መዘዙ ደርግ ለአመታት የቆየውን የ"መሬት ለአራሹ" ጥያቄ በታህሳስ 1967 በአዋጅ "መፍትሄ" ሰጠሁበት አለ:: መፍትሄውም የኢትዮጵያ መሬትን ከግል እና መንግስታዊ ካልሆነ ባለቤትነት ወደ መንግስት ወይም በተለምዶ የህዝብ ባለቤትነት ለወጠው:: ኢትዮጵያ በዘመኗ (ሺዎች) አይታው የማታውቀው ይህ የመሬት ይዞታ 44 አመት ሊሆነው ነው:: በኔ አመለካከት ውጤቱም ኪሳራ ነው! ያ አዋጅ በኢትዮጵያ … Continue reading (By Redeat Bayleyegn) የመጀመሪያው መሬት ለአራሹ እና መዘዙ

የአማራ ክልል የጫት ቃሚወችን ቁጥር ለመቀነስ የያዘው ዕቅድ:- ከፍተኛ ቀረጥ መጣል!

(ናይሮቢ) ሰዎች በግል የሚፈጽሙትን ጎጅ የሚባሉ ነገሮች እንዳይጎዳቸው ለማቆም ወይም ሰዎች ሌሎች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ለማድረግ እና ድርጊቱን ለመቀነስ መንግስታት የክልከላ ሕግ ማውጣታቸው የተለመደ ነው። ይሁን እንጅ መንግስታት ጎጅ ድርጊቶችን ለመቀነስ ወይም ለማስቀረት የሚያወጧቸው ሕጎች ብዙ ጊዜ ውጤታቸው ተቃራኒ ሲሆን ይስተዋላል።ይህን ጽሁፍ የምጽፈው ሰሞኑን በአማራ ቴሌቪዥን ዜና ላይ የአማራ ክልል በክልሉ የሚገኙ ጫት ቃሚዎችን ቁጥር … Continue reading የአማራ ክልል የጫት ቃሚወችን ቁጥር ለመቀነስ የያዘው ዕቅድ:- ከፍተኛ ቀረጥ መጣል!

ነፃነት እና ምግባር፡-የራስ እና የማህበረሰብ ለውጥ ሂደት ቁልፎች 2

ፋኒ ክሮዝቢን ላስተዋውቅዎ! በአሜሪካ ኮንግረስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ንግግር ያደረገች ሴት ናት። ስለዚች ሴት ብዙም ሰምታችሁ ላታውቁ ትችሉ ይሆናል። ይህች ሴት ታዋቂውን ‘ብሌስድ አሹራንስ’ ጨምሮ በርካታ ፈጣሪን የሚያመሰግኑ መዝሙሮችን እና ውዳሴዎችን በመጻፍ ተወዳዳሪ የላትም። የካቲት ሁለት ቀን አስራ ዘጠኝ አስራ አምስት ዓ/ም ዘጠና አምስተኛ ዓመት የልደት በዓሏን ለማክበር ከሁለት ወር ያነሰ ጊዜ ሲቀሯት ከዚህ ዓለም … Continue reading ነፃነት እና ምግባር፡-የራስ እና የማህበረሰብ ለውጥ ሂደት ቁልፎች 2

ነፃነት እና ምግባር፡-የራስ እና የማህበረሰብ ለውጥ ሂደት ቁልፎች

ነፃነት ተድላ ወይም ተወዳጅ ሐሳብ ብቻ አይደለም። የሰው ልጅ ያለ ነጻነት ከቶውንም ሙሉ ‘ሰው’ ነኝ ማለት አይችልም። ነጻነት ደስታን ከሚሰጥ ኹነት እና ጥብቅና ሊቆሙለት ከሚገባ ፅንሰ-ሐሳብ ሁሉ እጅግ ይልቃል። በነፃነት አለመኖር የሚያስገኘው መልካም ነገር ቢኖር መራራ ሕይወት ነው። በነፃነት አለመኖር የሚያስገኘው እጅግ መጥፎው ነገር ደግሞ ሰብዓዊ ክብርን መገፈፍ ነው። መራራ ሕይወት እና ሞት የባርነት ፍሬዎች … Continue reading ነፃነት እና ምግባር፡-የራስ እና የማህበረሰብ ለውጥ ሂደት ቁልፎች

የነጻ ንግድን አስፈላጊነት:የጽሁፍ እና የቪዲዮ ውድድር

የነጻ ንግድን አስፈላጊነትን የሚያሳይ የጽሁፍ እና የቪዲዮ ውድድር የነጻ ንግድን አስፈላጊነት እና ጥቅም ከ2ገጽ ባላነሰ እና ከ3 ገጽ ባልበለጠ ጽሁፍ በመግለጽ ወይም ደግሞ ከ1 ደቂቃ ባላነሰ እና ከ2 ደቂቃ ባልበለጠ ቪዲዮ በመግለጽ ለሽልማት ይወዳደሩ።በሁለቱም ዘርፍ ከ1 እስከ 3 የሚወጡ ተወዳዳሪዎች በአዲስ ዓመት ዋዜማ ይሸለማሉ። ተወዳዳሪዎች እድሜያቸውከ18 እስከ 35 የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ይሆናሉ።  በውድድሩ መሳተፍ የሚፈልጉ ሰዎች … Continue reading የነጻ ንግድን አስፈላጊነት:የጽሁፍ እና የቪዲዮ ውድድር