የሳንባ ቆልፍ ቢይዝዎ ምን ያደርጋሉ?

እነሆ ምክር ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን አንደበት!

የሳንባ ቆልፍ ቢይዝዎ ምን ያደርጋሉ?
»እነሆ ምክር፤ተይዘው ከዳኑት ኢትዮጵያዊያን አንደበት!
በዓለም ዙሪያ በሳንባ ቆልፍ ከተያዙ ሰዎች ውስጥ እስካሁን በተመዘገበው መረጃ ሆስፒታል መሄድ ሳያስፈልጋቸው በቤታቸው ውስጥ የሚድኑት 80በመቶ ናቸው። በሳንባ ቆልፍ ከሚያዙት ውስጥ 20 በመቶዎቹ ሆስፒታል የሚገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 5በመቶ ያህሉ በከፍተኛ ክትትል ክፍል (አይሲዩ) ውስጥ ሲገቡ ከነሱ ግማሹ(2•5 በመቶ) ደግሞ የኦክስጅን ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ታውቋል። ይህን ጽሁፍ እንድጽፍ ምክራቸውን የለገሱኝ ሰዎች በቤታቸው ውስጥ ከሚድኑት 80በመቶዎቹ ጎራ የሚመደቡ ናቸው። ኢትዮጵያዊያኑ በሳውዲ አረቢያ ሲሆኑ በሳንባ ቆልፍ የተያዙት ባል፣ሚስት፣ልጅ እና የሚስት ወንድም ናቸው። “የሳንባ ቆልፍ ቢይዝዎ ምን ያደርጋሉ?” የሚለውን ጽሁፍ አንብበው “ምናልባት ኢትዮጵያዊያንን ከጠቀመ እኛም አልፈንበታልና የምንነግርህ አለ።” ብለው ስልካቸውን ተውልኝ። እኔም ደወልኩና በየተራ አወራኋቸው። የኢትዮጵያዊያኑ እድሜ ከ15 እስከ 38 ዓመት ናቸው። መጀመሪያ ህመሙ የጀመራት ሚስት ናት። ከፍተኛ ትኩሳት ጋር ጉሮሮዋን እንደ መከርከር እና የማሳከክ ስሜት ይሰማት ነበር። ቶንሲል ይሆናል አሉ። ልጅቷ በምትሰራበት አውሮፓዊያን በሚበዙበት የስራ ቦታ ይሰሩ የነበሩ ሁለት ሰዎች ቀደም ሲል በሳንባ ቆልፍ ተይዘው ወደ ስፔን ተልከው እንደ ነበር እና በሃገሪቱ በሽታው መዛመቱን ተከትሎ የሳውዲ መንግስት በሃገሪቱ ባወጣው መመሪያ መሰረት ድርጅቱ ለጊዜው ተዘግቷል። በሶስተኛው ቀን የሚስት ህመም ሃይለኛ የማያቋርጥ ሳል አስከተለ። “ጉሮሮየን እንደ ሲሚንቶ ምርጊት የሚከብድ ነገር ሆነብኝ። ሳስል አክታ ሳይሆን ጉሮሮየ እራሱ የሚወጣ ነው የሚመስለኝ። ጉሮሮየ ባዕድ አካል መስሎ ተሰማኝ። ሳሉ ፋታ አይሰጥም።” ከዚያ ባል ሲጨንቀው ኢትዮጵያ ቤተሰቦቹ ጋር ይደውላል። ከዚያም የተለያዩ ምክሮችን ያገኛል። በሪያድ የሚያውቃቸው አንድ ኢትዮጵያዊያ ጋር ይሄዳል። ጭንቀት ነው። በኔ ጽሁፍ ምክሩን ሁሉ ሳይሆን ተግብረው የዳኑበትን ነገር ብቻ ነው የምጽፈው። 

የመጀመሪያው ምክር ለሶስት ቀናት ጧት በባዶ ሆድ አንድ ፍንካች ብቻ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት አላምጦ መዋጥ ወይም በአንድ ኩባያ ውሃ በጥብጦ መጠጣት ወይም ነጭ ሽንኩርቱን ከወተት ጋር አፍልቶ መጠጣት ነው። ጉሮሮ በማንኛውም ሰዓት መድረቅ የለበትም።” ጉሮሮ መድረቅ ሲጀምር ልክ ተቦክቶ ነፋስ እንደመታው ሲሚንቶ ድንጋይ ይሆናል ስለዚህ ሰዎች በቀላሉ ከበሽታው ሊድኑ የሚችሉት ጉሮሯቸው እንዳይደርቅ በማድረግ ነው።ስለዚህ በኢትዮጵያ ጉንፋን ሲይዘን እንደምናደርገው ትኩስ ነገር ቶሎ ቶሎ መጠጣት። ከዚህ በተጨማሪ የዝንጅብል ሻይም እንጠጣለን። አጥሚትም አለ። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የሚደረገው ሁሉ መድሃኒት ነው። እኛን መጀመሪያ የጎዳን ፍርሃቱ እና ድንጋጤው ነው።” ብለዋል። ወደ አመሻሹ ላይ ደግሞ ማታ ላይ ደግሞ አንድ ፍንካች ነጭ ሽንኩርት ከወተት ጋር ተፈልቶ በሻይ ማንኪያ ሩብ ፌጦ ጨምሮ መጠታት እና ይሄንኑ ለአንድ ሳምንት አድርገን አልፎ አልፎ ከማሳል ውጭ ያለው ህመም ቀርቶልናል። ግን ማድረግ አላቆምንም። ጨጓራ እንዳይነካ ትንሽ ህመም ሲሰማቸው መተው እና አንድ ቀን ሁለት ቀን መዝለል ይገባል። በዚህ ምክንያት አንድ ቀን ስንዘል ማታ ላይ በምትኩ *ማር ጋር የተለወሰ የተጨቀጨቀ ነጭ ሽንኩርት በትንሿ ማንኪያ ከመተኛታችን በፊት እንውጣለን። ይሄንንም እዚህ ሪያድ የሚኖሩ የምናውቃቸው ሰው ልከውልን ነው። ውሃ የምንጠታው ደግሞ ለብ ያለ ውሃ ውስጥ ሎሚ ቆራርጠን ከነልጣጩ በመጨመር ነው። ሎሚው ተዘፍዝፎ የሚውለው እዚያው ጆጉ ውስጥ ነው። ውሃ ሲያልቅ በላይ ላይ ለብ ያለ ውሃ መጨመር ነው። ቀዝቃዛ ነገር ፈጽሞ መጠጣት የለብንም ብለዋል። ሎሚ ከሌለ ለብ ያለ ውሃ ብቻውን መጠጣት ነው። ሚስት ለትኩሳቷ ፓራሲታሞል እና የጉንፋን ሹሮፕ ትወስድም ነበር። ከአምስት ቀናት በኋላ የሚስት ጉሮሮ እየተሻላት እና ሳሉም እየቀነሰ ሄዶ በ10 ኛው ቀን ላይ ባል ድንገት በጓደኛው መኪና ቤት ይደርሳል። 

ምክንያቱ ደግሞ ባል በሚሰራበት ቦታ ይወድቃል። **“ኤር ኮንዲሽነር አቅርባኢያ ሆኘስልክ ሳወራ ድንገት ዝልፍልፍ ብየ ወደቅሁ።” አለኝ። በተመሳሳይ ቀን የሚስት ወንድምም በቤቱ ታሞ መተኛቱን በስልክ ይረዳሉ። ከዚያ ልጅም ተከተለ። ለልጁ ከነጭ ሽንኩርት ጋር የተፈላ ወተት ብቻ በቀን አንድ ጊዜ እየሰጡ አዋቂዎቹ ግን ወ/ሮዋ ያደረገችን በማድረግ ጉሮሮአችው ቢያንስ እንደሷ ድንጋይ ሳይሆን(ስሜቱ እንደዚያ ነው) ትግላቸውን ፋታ ከማይሰጠው ጋር አደረጉ። “ይገርምሃል ቫይረሱ የሚቆየው 14 ቀን ነው የሚሉት ትክክል ነው። እሱን በራሳችን አረጋገጠናል። ይሄው በ13ኛ ቀኔ ነው ወደ ውስጥ የምስበው ኦክስጅን ወደ ሳምባየ ሲገባ እንኳ ስሜት የሚሰጠኝ።” አለኝ ባል። “ጉሮሮ ላይ እንደ ድንጋይ የሚከብደው ለምን እንደሆነ የሚገባህ ነጭ ሽንኩርት እና ፌጦ ከወሰድን በኋላ እየተጎለጎለ የሚወጣውን አክታ ስታይ ነው።” ብለውኛል። ጨጓራ ያለባቸው ሰዎች ነጭ ሽንኩርቱን በጧት ተነስተው ከመብላት በወተት ብቻ አፍልተው እንዲወስዱት መክረዋል። የሚስት ወንድም ጨጓራ እንዳለበት የመጀመሪያ ቀን አንድ ፍንካች ነጭ ሽንኩርት አላምጦ ከመዋጥ ይልቅ ከትፎ በውሃ በጥብጦ ቢጠጣውም ጨጓራው እንደነደደ እና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ንገራቸው ብሎኛል። ከዚያ በተረፈ አስራ አምስቱንም ቀን ማታ ማታ ነጭ ሽንኩርት መታጠን ደረት ላይ የሚሰማውን ጭንቀት አስቀርቶልናል። ስለዚህ ይጠቅማል ብለዋል።”በአጠቃላይ ህዝቡ ከበሽታው ቀድሞ ፈራ እንጅ በኢትዮጵያ ለጉንፋን በምናደርገው ህክምና ሊድን የሚችል በሽታ እንድሆነ ነግረውኛል። በስልክ በነበረን ከአንድ ሰዓት በላይ ቆይታ ሁሉም አልፎ አልፎ ከመሳል በቀር ደህና መሆናቸውን እና ህዝቡ መሸበሩን አቁሞ ሃገራዊ መፍትሄዎች ላይ በማተኮር ሊድን እንደሚችል ነግረውኛል። ሌላው የተገነዘብነው ነገር የእጅ ንጽህና ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ነው። ስለዚህ በተቻለ መጠን እጅ መታጠብ አስፈላጊ መሆኑንም አልደበቁኝም።ከላክ መረጃውን ያካፈሉኝ ሰዎች ተጠቂዎች እንጅ በሳይንስ ሊሞገቱየሚችሉ ሰዎች ስላልሆኑ ሁሉንም የተገበሩትን ምክር ጎጅ ይሆናል ብየ ስለማላስብ እና እኔም ራሴ እንደምጠቀመው እርግጠና ስለሆንኩ ለናንተ ጽፌዋለሁ። 

#የኔ ጭማሪ !
**በዚህ ጽሁፍ የተጠቀሱትን መድሃኒቶች ጥቅም ላይ ከማዋላችሁ በፊት ከሳንባ ቆልፍ ሌላ የተጠቀሱት ነገሮች ጉዳት የማያስከትልባችሁ ሌላ ህመም እንደሌለባችሁ ማወቅ ይገባችኋል። ለምሳሌ ስኳር ያለበት ሰው ማርን ያካተተውን ምክር መቀበል ያለበት አይመስለኝም። ሁላችንም ልብ ልንል የሚገባው ቁልፍ ነገር የሳንባ ቆልፍን ለመከታተል እና ሳይብስብን ቶሎ በአጭሩ ለመቅጨት ማንኛውም የጉንፋን ስሜት፣ ከፍተኛ ትኩሳት እና የጉሮሮ ህመም (መከርከር ወይም ማሳከክ) ሲሰማን እራሳችንን የሳንባ ቆልፍ እንደያዘን አድርገን በማሳመን ከላይ የተጠቀሱትን እርምጃዎች መውሰድ መጀመር ነው። ምክንያቱም ያን ባለማድረጋችን እንጎዳ እንደሆን እንጅ በማድረጋችን የምናጣው ወይም የምንጎዳው ነገር አይኖርም።ሁላችንንም ግን ፈጣሪ ይጠብቀን፤ ከመጣም ደግሞ የምንችለው ያድርገን። አሜን!
* ማር በነጭ ሽንኩርት ሁሌም ቢሆን አልፎ አልፎ እጠቀማለሁ።ትንሽ የማቃጠል ስሜት እንዳለው እወቁ!  
**በቤታችሁ ኤር ኮንዲሽነር ያላችሁ ሰዎች የቅዝቃዜውን መጠን መቀነስ ይኖርባችኋል። አለዚያ ቫይረሱ ያለበት ሰው ካለ የማሰራጭት እና የማዳረስ እድሉ በጣም ሰፊ መሆኑን የስነ ቫይረስ ጥናት ባለሙያዎች ያስረዳሉ።
***ኢትዮጵያዊያኑ ነጭ ሽንኩርት ብቻ የሚታጠኑት በኢትዮጵያ የሚገኙ እና ጥቅም ላይ የሚውሉ ቅጠሎችን በአቅራቢያቸው ስለማያገኙም ጭምር እንደሆነ መረዳት ይቻላል። ስለዚህ ነጭ ሽንኩርት ስለተባላ እነ ዳማከሴ፣ሃረግ ሬሳ፣ ሰንሰል፣ የአህያ ጆሮ(ቅጠል ነው)፣ ነጭ ባህር ዛፍ ወዘተ መዘንጋት የለባቸውም!

Advertisement

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.