
በኢትዮጵያ ለመጣው ለውጥ በዋነኛነት የተገረፉ፣የተሰቃዩ፣የታሰሩ፣የተገደሉ፣ በየበረሃውን እና ባህሩ ነፍሳቸውን የገበሩ ኢትዮጵያዊያን እና የተገፋው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለያየ መንገድ ያደረገው ትግል ውጤት ነው። የኛም የዲያስፖራዎች ድርሻ አለ። ይህን ለውጥ ለሌሎች ጸረ ኢትይጵያ ዓላማ እየተጠቀመበት ያለው በሚኒሶታ መቀመጫውን ያደረገው ጃዋር መሐመድ ከተለያዩ የባህረሰላጤው ሃገራት በሚደረግለት የገንዘብ እና ሎጅስቲክስ ድጋፍ የፕሮፖጋንዳ እና የጥላቻ ማሽን የሆነውን ኦኤምኤን በመጠቀም ሃገሪቱን ከዚህም በላይ ለማመስ እየሰራ ነው።ጃዋር መሐመድ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ እና በብዙ ሽህወች የሚቆጠር የእጅ ስልኮችን ለተከታቶቹ በነጻ አድሏል። ይህም ከተከታዮቹ ጋር ያለውን ግንኙነት በማቅለል ከ1ሚሊዮን በላይ ተከታዮች እንዲኖሩት በማድረግ እና መልዕክቱን በቀላሉ ለማሰራጨት ረድቶታል። በአንድ መልክት ተከታዮቹ ለማመን የሚከብድ ጭፍጨፋ እና የኢሰብዓዊነት ተግባር ፈጽመዋል። በዚህ ሰሞኑን ከ86 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከ400በላይ ቆስለዋል። ይህ ግን ለሚመጣው አሰቃቂ ጭፍጨፋ እንደ ቀብድ ነው። ጃዋርን እና ወንጀል የፈጸሙት ተከታዮቹ ዛሬ ለፍትህ ካልቀረቡ እና ድርጊታቸውን ማስቆም ካልቻልን የባሰው እልቂት እየመጣ ነው። ጃዋር መሀመድ አንድና አንድ ዓላማ ብቻ ነው ያለው። የጃዋር መሐመድ አላማ በኢትዮጵያ የእስላም መንግስት ማቋቋም ነው። ለዚህም ኦሮሞን እንደ መደበቂያ እና መጠቀሚያ ሃይል እያደረገ ነው። ኢትዮጵያን በአፍሪካ ብቸኛ ለወራሪዎች ያልተገዛች ሃገር ያደረጋት እስላም እና ክርስቲያኑ በጋራ ተዋግቶ ደሙን አፍስሶ ነው። ጃዋር ሶማሊያን ያፈረሳትን አጀንዳ ወደ ኢትዮጵያ ወስዷል። ብሄርን እና ሃይማኖትን መጠቀሚያ በማድረግ የፍጅት በር እየከፈተ ያለው ጃዋር ለሃገራችን ዋነኛ ስጋት ሆኗል።
ለአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጃዋር የፈጸመውን እልቂት በማስረጃ አስደግፈን ጠንካራ ደብዳቤ ጽፈናል። ደብዳቤውም ትኩረት አግኝቶ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፒዮ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ስልክ ደውለው በጉዳዩ ላይ ተወያይተዋል። የአሜሪካ ሴኔት በኢትዮጵያ ላይ ባረቀቀው ሪዞልሽን 168 ላይም አሁን በኢትዮጵያ ያለው ቀውስን የሚመለከት ማሻሻያ እንዲካተት ለማድረግ ጠይቀናል። ለሰብዓዊ መብት ግድ የሚሰጣቸው ኢትዮጵያዊያንም በዚህ ረገድ ከኛ ጎን እንዲሰለፉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። በኢትዮጵያዊያኑ ሰልፍ ላይ የተገኙት ኮንግረስ ማን ጄሴን ክሮው ለጥላቻ እና ለክፍፍል አጀንዳ እንዲሁም ሃገሪቱን ለከፋፈላት የጎሳ ፖለቲካ ድጋፍ አናደርግም። ኮምግረስ ማን ማይክ ኮፍማን በበኩላቸው “በኢትዮጵያ የኦሮሞ ክልል ውስጥ አክራሪዎች ክርስቲያኖችን እየጨፈጨፉ መሆኑን እናውቃለን።ከ86 በላይ ንጹሃን መገደላቸውን እና በሞቶዎች የሚቆጠሩ መቁሰላቸውንም እናውቃለን። ከእናንተ ጎን ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፈውን የተሻለች ኢትዮጵያ እንድትመጣ አብሬአችሁ እሰራለሁ።” ብለዋል። በሃይማኖት የሚደርስ አድሏዊነት እና በብሄር ላይ ያነጣጠረ ግድያ ለወደፊቷ ኢትዮጵያ አደጋ ነው። የናንተ ስሜት ብዙ ነገር ይናገራል። አቅምም አለው። ለኢትዮጵያ እንጸልያለን። እግዚአብሄር ይባርካችሁ።
በኮሎራዶ የዴሞክራት ፓርቲ የኢትዮ-አሜሪካዊያን ቻፕተር ሊቀመንበር በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከተናጋች ምስራቅ አፍሪካ ትናጋለች። ኢትዮጵያ አንድ ከሆነች ምስራቅ አፍሪካ ሰላም ትሆናለች ብለዋል። አቶ ሳሙኤል ደግሞ “ጠላቶቻችን አይተኙም። ከዚህ በኋላ ወደኋላ አንልም።የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመብን ነው። እምነታችንን የማጥፋት ዘመቻ እየተደረገብን ነው። በምን ጥፋት እንደምንቀጣ አላውቅም? ሰዎች ተጨፍጭፈው የሚሰጡትን መግለጫ እንኳ እያየን ነው።”በማለት በእንባ ምክንያት ንግግራቸውን መቀጠል አልቻሉም። የሪዞልሽን 168 ማሻሻያ በቀጣዩ ሳምንት እንልክላቸዋለን። ከዚህ በፊት ይህን ሪዞልሽን ይቃወም የነበረው የኦክላሆማው ሴናተርም አሁን ድጋፍ እንደሚሰጡን ተረድተናል።ከዚህ በፊት አገር ሰላም ሆኗል ይሄን የሴኔት ጉዳይ ተውት ይሉን የነበሩ ሰዎች አሉ። እንኳንም አልተውነው። ይሄው አሁን ልንጠቀምበት ነው። ሴናተሮችን በምናነጋግርበት ጊዜ ያገኘነው መረጃ ሌላ ነው። እኛ በብሄር ምክንያት ሰዎች እየተለዩ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው ስንላቸው “እሱን ተውት። በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ሃይማኖት ዘመቻ እየተደረገ ነው። እናንተን ሊያሳስባችሁ የሚገባው ይህ ነው። ለመሆኑ ይህን ታውቃላችሁ ወይ?” ብለው ጠይቀውናል። ሴናተሮቹ “ከመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ መጠን ወደ ኢትዮጵያ እየገባ እንደሆነ እናውቃለን። አክራሪ የሆኑ ሃይሎች በኢትዮጵያ ላይ ዘምተዋል። ይህን ያሉን ከ10ወራት በፊት ነው። የአሜሪካ የደህንነት፣ የጸጥታ እና የስለላ ሰራተኞች የገንዘብ እንቅስቃሴውን መከታተል ከጀመሩ ቆይተዋል።እዚያው ሪጅን ውስጥም ስራ እየሰሩ መሆኑን ተረድተናል። ስለዚህ ከጎሳው ይልቅ የሃይማኖቱ ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርጉ።” ተብለናል።
You must be logged in to post a comment.