የዶ/ር አቢይ ዕቅድ እና የኢኮኖሚ ነጻነት

 

This image has an empty alt attribute; its file name is 49188508_2559486090746748_861805979879079936_n.jpg

ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንትን ሊስቡ የሚችሉ አሰራሮችን ለማስፋፋት እና እንቅፋቶቹን ለማንሳት የሚረዳ ዕቅድ ነድፈው ወደ ስራ መግባታቸውን ነግረውናል። እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ በትክክል ተጠንቶ ስራ ላይ የሚውል ከሆነ ይህ ዜና ሳይሆን ለኢትዮጵያ ብስራት ነው። ምክንያቱም የኢትዮጵያን አብዛኛው ችግሮች የሚፈታበት ቁልፍ ያለው እዚህ ነው። ቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት የተቋቋሙ ድርጅቶችን(ቢዝነሶችን) ያስፋፋል። አዳዲስ የንግድ ድርጅቶ እና ቢዝነሶች እንዲቋቋሙ በር ይከፍታል። ቢዝነሶች ሲስፋፉም ሆነ አዳዲስ ድርጅቶች ሲከፈቱ በርካታ ስራዎች ይፈጠራሉ። የኢትዮጵያ ህዝብ እና ኢኮኖሚ የሚጠቀሙት በዚህ መንገድ በሚፈጠር ስራ ብቻ ነው። ኢንቨስትመንት ምርምርና ጥናት እንዲሁም ምርታማነት እንዲያድግ ስለሚያደርግ ለሃገር ኢኮኖሚ እድገት እና ለዜጎች ብልጽግና ትልቅ አስተዋጽዖ ያደርጋል።የዓለም ባንክ ‘ኢዝ ኦፍ ዱይንግ ቢዝነስ’ የሚለው በአንድ ሃገር ወደ ቢዝነስ የሚያስገቡ ምቹ ሁኔታዎችን እና ኢንቨስትመንትን የሚያቀላጥፉ አሰራሮችን ደካማነት እና ጠንካራነት እንዲሁም መኖር እና አለመኖራቸውን ጭምር ከሌላው ሃገር ጋር የሚያወዳድርበት መለኪያ ነው። የዓለም ባንክ ይህንኑ መለኪያ በመጠቀም ሃገራትን እያወዳደረ ዓመታዊ ሪፖርት ያወታል። ይህንኑ ሪፖርት የሄሪቴጅ ፋውንዴሽን እና የዋል ስትሪት ጆርናል በጋራ እንዲሁም የፍሬዘር ኢንስቲትዩት በመላው ዓለም ካሉት የፍሪደም ኔትዎርኮቹ ጋር በመተባበር በየዓመቱ ‘የኢኮኖሚ ነጻነት’ ሪፖርት በሚል መጠሪያ ያወጡታል።ሁለቱ ዓለማቀፍ ተቋማት እና የዓለም ባንክ ‘ኢዝ ኦፍ ዱይንግ ቢዝነስ’ ሃገራትን መዝነው በሚያወጡት ዓመታዊ ሪፖርት ውጤት ላይ ብዙም ልዩነት የለም። ለምሳሌ ያህል ብናይ የዓለም ባንክ በሚያወጣው እና ሁለቱ ተቋማት በሚያወጡት ሪፖርቶች ለ21ዓመታት ያህል የአንደኛነቱን ቦታ የያዘችው ሆንግ ኮንግ ነበረች።

በኢኮኖሚ ነጻነቷ ዛሬም ድረስ የበላይነቷን ያስጠበቀችው ሆንግ ኮንግ ከሁሉም በልጣ የተገኘችበት ሚስጥሩ ከሃገራት ሁሉ የበለጠ ኢንተርፕርነሮችን የሚያበረታታ፣ ለቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ አሰራር ተግባራዊ ማድረጓ ነው። ሰሞኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ የኢትዮጵያን የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ሁኔታ ምቹ ለማድረግ የጀመሩት ኢኒሽየቲቭ ይሄንኑ ለኢዝ ኦፍ ዱይንግ ቢዝነስ እንቅፋት የሆኑ ህግና መመሪያዎችን በማስወገድ እና አዳዲስ ምቹ አሰራሮችን መተግበር ላይ እንደሚሰራ ይጠበቃል። ይህ ኢኒሽየቲቭ ሙሉ ለሙሉ ሊሰራ የሚችለው ግን ሃገሪቱ በሌላ አውድ የጀመረችው ብቃት እና ገለልተኛ የሆነ የፍትህ ሥርዓት ለማዋቀር የምታደርገው ጥረት ከሰመረ እና የሕግ የበላይነት ሲሰፍን እንደሆነ መረዳት አስፈላጊ ነው።እንግዲህ ጠቅላይ ሚንስትሩ በዚህ ጉዳይ ላይ ወገባቸውን ጠበቀው አድርገው ከሰሩ እና ኢትዮጵያ ካለባት የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት እንቅፋቶች ውስጥ በትንሹ የ5በመቶ እንኳ ማሻሻያ ቢያደርጉ በድሆች ብዛት ከዓለም ሶስተኛ ከሆነችው ሃገራችን ላይ ድህነትን 1 በመቶ ይቀንሳሉ። ይህ እንደኛ በድህነት አረንቋ ውስጥ ላለ ሃገር ትልቅ እርምጃ ነው። የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት እንቅፋቶችንለማንሳት እና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚያስችሉ አሰራሮችን ለማሻሻል የሚደረገው ጥረት ይበልጥ በሰፋ ቁጥር የኢኮኖሚ እድገት እና የድህነት መጠን ቅነሳውም በዚያው መጠን ይጨምራል። ከ2013ዓ/ም ጀምሮ የኢኮኖሚ ነጻነት ሪፖርት በሚዳስሰው ሪፖርት ላይ ባለኝ ተሳትፎ እና ልምድ መሰረት የሚከተሉት ሃሳቦች ቢካተቱ የታሰበው ኢዝ ኦፍ ዱይንግ ቢዝነስ ኢኒሽየቲቭ ለሕዝቡ የሚታይና የሚዳሰሰ ዕውነተኛ ለውጥ ያመጣል ብየ አስባለሁ። እነዚህም የግብር ስርዓቱን ያልተወሳሰበ እና ግልጽ ማድረግ ከተቻለ እንዲሁም የቀጥተኛ ግብር ተመን ላይ ቅናሽ ካደረገ፣ዜጎች ከቋሚ ንብረታቸው ላይ ከሚያገኙት ጥቅም ላይ የሚሰበሰበው ግብር ቢያንስ በግማሽ ሲቀንስ(ለምሳሌ በውርስ ከሚገኝ ሃብት፣ቤት ሲሸጥ እና ሲከራይ ለመንግስት የሚከፈለው ግብር)፣ በሃገሪቱ የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ መንግስት እጁን ከሰበሰበ(ለምሳሌ የዋጋ ተመን ማውጣትም ሆነ ግብር ከፋይ ነጋዴ ጋር አብሮ መነገድ ካቆመ)፣ ወደሃገር ቤት የሚገቡና የሚወጡ ሸቀጦች ላይ የቀረጥ ቅናሽ ከተደረገ(ቢያንስ የዓለም ንግድ ድርጅት በሚጠይቀው መስፈርት መሰረት)፣ መንግስት ወጭዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ከወሰነ(ይህ አማራጭ የለውም፤ ካለም ገና ያልተወለዱትን ልጆቻችንን ባለዕዳ ማድረግ ነው)፣ አብዛኛውን (ከተቻለ ሁሉንም) ለንግድ እንቅስቃሴ እንቅፋት የሚሆኑ ህጎች/መመሪያዎች ሲሰረዙ እና የማይዋዥቅ እና የተረጋጋ የገንዘብ አስተዳደር ፖሊሲ በስራ ላይ ማዋል ሲቻል ነው።

ልክ የአንድ ወይም የሁለት ኳስ ተጨዋቾች መዳከም የጠቅላላ የቡድኑ ብቃት እና ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚፈጥረው ሁሉ ከላይ ከተዘረዘሩት ነገሮች ውስጥ ያንዱ መጓደል ወይም እንቅፋት መሆን ወይም ተገቢውን ያህል ማሻሻያ ሳያደርጉ መቅረት የጠቅላላ ኢኮኖሚውን እድገት ወደኋላ ይጎትታል ማለት ነው። በግሌ ይህን የዶ/ር አቢይ አህመድ ኢኒሽየቲቭ 100% እደግፋለሁ። ሆኖም ግን ኢኒሽየቲቩን እንዲያሳኩ ከመረጧቸው ሰዎች አብዛኞቹ የኢሕአዴግ አመራሮች/ሚንስትሮች ናቸው። የታሰቡት የቢዝነስ ዱይንግ መርሆዎች ደግሞ ከኢሕአዴግ የፖለቲካ ፍልስፍና ጋር ይጋጫሉ። ባለፉት ዓመታት እንዳየነው ለኢሕአዴግ ‘ኢዝ ኦፍ ዱይንግ ቢዝነስ’ ማለት ለዘመድ አዝማድና ለተመረጠ ቡድን የሃገርን ሃብት ማቀራመት ማለት ነው።ጠቅላይ ሚንስትሩ ኢኒሽየቲቩን ሲያቋቁሙ የነበረውን ሁኔታ ለመቀየር እንዳሰቡ ብረዳም ያዋቀሩት ቡድን አባላት ላይ ከኢኮኖሚያዊ እውነታዎች ጋር በሚጣረሰው ኢሕአዴጋዊ የፖለቲካ ፍልስፍና ምክንያት በሚደርስባቸው ጫና የታሰበለትን ለውጥ ሊያዘገዩ ወይም ጭራሽ ላያመጡም ይችላሉ። በዚህ ረገድ የዕቅዱ ስኬታማነት የሚረጋገጠው የኢኒሸቲቩ አባላት ከኢኮኖሚያዊ ዕውነታዎች ጋር የሚጋጨውን የፖለቲካ ፍልስፍናቸውን ለመቀየር ወይም ሪፎርሙን አካሂደው እስኪጨርሱ ድረስ ወደጎን ለመተው ባላቸው ፍላጎት/ተነሳሽነት ልክ ነው። ስለዚህ ዕቅዱ እውን ይሆን ዘንድ ይህ ጉዳይ በደንብ ቢታሰብበት/ትኩረት ቢሰጠው መልካም ይሆናል ባይ ነኝ!!!

Advertisement

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.