የኢትዮጵያዊው ፈርዖን የኢኮኖሚ መርሆች እና የአስተዳደር ጥበብ

(By Kidus Mehalu)በግብጽ ባለ ሙሉ ስልጣን የነበረው የ26ኛው ስርዎመንግስት ኢትዮጵያዊ ፈርኦን ለየት ያለ የግብር አሰባሰብ መርህ  ነበረው። “ያ መርህ በኔ ዘመን የተሻለ ከሚባለው ከእንግሊዝ የግብር አሰባሰብ ስርዓት የተሻለ ነበር።” ፈረንሳዊው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ሊቅ እና ፈላስፋ ቻርለስ ሉይስ ሞንቴስኪዩ በኢትዮጵያዊያኑ ፈርኦኖች የታሪክና አስተዳደር ድርሳን መመሰጡን ቀጥሏል። “ሰው እንደቤቱ እንጅ እንደ ጎረቤቱ አይኖርም።” የሚባለው ኢትዮጵያዊ ብሂል ከኢትዮጵያዊው ፈርኦን የአስተዳደር መርህ የመነጨ የአባቶቻችን ቅጅ ሳይሆን አይቀርም። የታላቋ ሮማን ሃብት ከኢትዮጵያ ሃብት ሃብት ጋር ማነጻጸር አይገባም። የአንተንም ሃብት ከጓደኛህ ወይም ከጎረቤትህ ሃብት ጋር ማነጻጸር የተገባ አይደለም። በዚህ ረገድ መልስ የምትሻ ከሆነ ማወዳደር ያለብህ “ሃብትህን ከሌላ ሃገር የሃብት ምንጭ ወይም ከጓደኛህ/ከጎረቤትህ የሃብት ምንጭ ጋር ነው። ያ የሃብት ምንጭ ከሌለህ ሃብቱ ሊኖርህ አይችልም።”  ሲል ያጠናውን ድንቅ ጥበብ በማስታወሻው ላይ አስፍሯል። Montesquieu556[1779] ቻርለስ ሉይስ (ሞንቴስኪዩ) መደመሙን ይቀጥላል። የሃብት ምንጩ ከሌለህ እና ሃብቱ እንዲኖርህ ከፈለክ ምን ማድረግ እንዳለብህ ማወቅ ይኖርብሃል። ሃብት ለመፍጠር “የንግድ ድንበርን ማስፋት እና የሚሰሩ ሰዎችን ማብዛት” የግድ መሆኑን በመግለጽ ‘ታላቋ ኢትዮጵያ’ ከታላቋ ሮማ ጋር የነበራትን ጥልቅ የገበያ ትስስርም እጅግ አስደናቂ ነበር። ይሄንንም “በዓለም ላይ በራሳቸው ዘመናዊ የብር(ሲልቨር) ገንዘብ ሲገበያዩ የነበሩ የመጀመሪያዎቹ ኢምፓየሮች ሳይሆኑ አይቀርም።” በማለት ይገልጠዋል-ፈረንሳዊው ፈላስፋና የፖለቲካ ሊቅ ቻርለስ ሉይስ (ሞንቴስኪዩ)!

የንግድ ድንበርህን እና የሰው ሃይልህን ሳታሰፋ ‘ሃብት እንዲኖርህ’ ከፈለክ ያን ማድረግ የምትችለው በዘረፋ እና በጉልበት ብቻ መሆኑንም በግልጥ የተረዳው ፈላስፋ “ኢትዮጵያዊያኑ ፈርኦኖች ያን መንገድ  ያልተከተሉት ሕግና ስርዓት እንደሚያፈርስ ስለተረዱ ሳይሆን አይቀርም።”በማለት “ከኢትዮጵያ አልፈው ግብጽ ላይ የነገሱበት ምክንያትም ይሄው ሳይሆን አይቀርም።” ሲል  ኢትዮጵያዊያኑ ፈርኦኖች ከሕግና ስርዓትም በላይ ኢኮኖሚክስ የገባቸው እንደነበሩ ጥፏል።የሃገርህን ንግድና የሚሰራ ሃይል ስታሰፋ የሃገርህም ሆነ የሕዝብህ ኑሮ እንደሚሻሻል ዛሬ ድረስ ዕውነት ነው። የሃገርህን ንግድና የሚሰራ ሃይል ሳታስፋፋ ለሃገርህ ሃብት ለመፍጠር መሞከር ግን “ብዙ ሽዎችን ካላደኸየህ በቀር አንድ ባለጸጋ(ሃብታም) እንኳ መፍጠር የማትችልበትን ስርዓት ትፈጥራለህ።” ያነግስብሃል።  በዚህ መንገድ መቀጠሉ ሌላው አደገኛ ጎኑ ደግሞ “እጅግ የናጠጡ ጥቂት ሃብታሞችን እና እጅግ በጣም የደኸዩ ብዙ ሰዎችን” መፍጠር መሆኑን በግልጽ ያስቀምጥና “ሕግና ስርዓት” ለምን እንደሚፈርስ መረዳቱን እንዲህ ያትታል። እጅግ በናጠጡ ጥቂት ሃብታሞች እና እጅግ በጣም ደሃ በሆኑ ሰዎች መሃል ላይ የሚያያይዝ ሌላ መሃከለኛ ሃብታም ወይም መሃከለኛ ደሃ ስለማይኖር እጅግ በሚራራቁት ሃብታሞች እና ድሃዎች መሐል “የሚነግሰው ተስፋ መቁረጥ፣ችጋር፣ረሃብ፣ግጭት፣ ኋላቀርነት፣ድንቁርና እና ስርዓት አልበኝነት ስርዓቱን ጠልፎ ይጥለዋል።” Montesquieu39[1751]  ልብ በሉ! የዘመናዊ ኢኮኖሚክስ ሳይንስ አባት አዳም ስሚዝ ይሄን አስተምህሮ የተረዳው ኢትዮጵያዊው ፈርኦን በተግባር ስራ ላይ ካዋለው  በ 720ዓ/ዓ ግድም ማለትም ከ2000ዓመታት በኋላ ነበር።የሆነ ሆኖ የዛሬዋ ኢትዮጵያ በዚያ መስመር ላይ አይደለችም። ይልቁንስ የዛ አስተምህሮ አሉታዊ ውጤት ማሳያ ሕያው ምሳሌ ናት። የዛሬዋ ኢትዮጵያ ከሕግ፣ከሞራል እና ከኢኮኖሚ መርሆች ሐዲድ ላይ አፈንግጣለች።ኢትዮጵያን ወደ ሃዲዱ ለመመለስየኢትዮጵያ መንግስት ግብጽን የመራውን  ኢትዮጵያዊ ፈርኦን የግብር እና አስተዳደር መርህ ሊከተል ይገባል። ይሄ መርህ “የአፍሪካ ሃገራት ከአመታዊ አጠቃላይ ምርታቸው በአማካይ 17በመቶ ግብር ስለሚሰበስቡ ኢትዮጵያም 17በመቶ ግብር መሰብሰብ አለባት።”ከሚለው የመንግስት አዲስ የግብር ዘመቻ ጋር የሚጻረር ነው። በመርሁ መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያን ግብር ከሌሎች ሃገራት ግብር ጋር ሳይሆን ከሃገራቱ የግብር ምንጭ ጋር ማወዳደር ይኖርበታል። የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያን ግብር ከኬንያ ግብር ጋር ሳይሆን የኢትዮጵያን የግብር ምንጭ ከኬንያ የግብር ምንጭ ጋር ማወዳደር ይኖርበታል። የኬንያዊያን አመታዊ አማካይ ገቢ 3500ዶላር ሲሆን የኢትዮጵያዊያን ደግሞ 800ዶላር ግድም ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ማወዳደር ያለበት የኢትዮጵያዊያንን ገቢ እና የኬንያዊያን ገቢ ሳይሆን የሁለቱን ሃገራት ዜጎች የገቢ ምንጭ፣የንግድ ድንበር ስፋትና ተደራሽነት፣ጥቅም ላይ የዋለ የሰው ሃይል  ብዛትና ጥራት ፣ለቴክኖሎጅ ያላቸውን ቅርበት ወዘተ ሚዛን ላይ በማድረግ ነው። ሃገራችን ኢትዮጵያ ላለባት መጠነ ሰፊ ችግር ወደ መፍትሄ የሚወስደን አቅጣጫም በሚዛኑ የጎደለብንን ለማሟላት በምናደርገው ጥረት ይወሰናል። ፈረንሳዊው የፖለቲካ ሊቅ እና ፈላስፋ ቻርለስ ሉይስ(ሞንቴስኪዩ) ከኢትዮጵያዊው ፈርኦን የታሪክ ድርሳን እንዳጠናው በአጭሩ ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር ተመሳሳይ የገቢ ምንጭ ከሌላት በቀር ተመሳሳይ የግብር ተመን ወይም ገቢ ሊኖራት አይችልም። ከሃገርህ የገቢ ምንጭ በላይ በግብር ገቢ ማግኘት የምትችለው “ሕዝብህን  በጉልበት በማስገደድ ብቻ ነው።” የሚለው ቻርለስ ይህን ማድረግ ግን በኢትዮጵያዊው ፈርኦን መርሕ መሰረት‘ሕግና ስርዓት’ አፍራሽ መሆኑን ያስታውሰንና ይዞን ወደ ቻይና ይዘልቃል። የታላቁ የዢያን ዲ ስርዎመንግስት ኢምፓየር ‘የሎ ተርባንስ’ተብሎ በሚታወቀው ሕዝባዊ አመጽ የፈረሰበትን ምክንያት ካዎ ፒ ይናገራል። “ስልጣንህን ለማስፋት እና መንግስታዊ ጡንቻህን ለማግዘፍ ግብር መጨመር የምትችለው የገዛ ቆዳህን ከሰውነትህ ላይ ስበህ መለጠጥ እስከምትችለው ድረስ ብቻ ነው።” ይህ የካዎ ፒ የግብር መርህ ከኢትዮጵያዊው ፈርኦን አስተምህሮ ጋር ተቀራራቢ መሆኑን በመታዘብ “ምናልባትም ተቀራራቢ መርህ የሚከተሉት እንደ ታላቋ ሮማ ሁሉ ኢትዮጵያዊያኑ ፈርኦኖች ከታላቁ የሃን(ቻይና) ኢምፓየር ጋርም በንግድ ተሳስረው እንደኖሩ አመላካች ነው።” በማለት ቻርለስ ሉይስ የቻይናን ድርሳናት ገላልጦ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ210ዓ/ዓ ጀምሮ የዘለቀው እና የታላቁን የቻይና ግምብ የገነባው የሁዋን ኢምፓየር በከፍተኛ ግብር ጫና በተማረረ ሕዝብ አመጻ ፍጻሜውን እንዳገኘ ይነግረናል። Montesquieu723[1734] “ቆዳችንን የቻሉትን ያህል ለጥጥው ግብር አስከፈሉን። ኢምፓየሩ የኛን የተራበ ሰውነት ቆዳ መለጠጡን አላቆመም።  አቃተን። ግብር የተቆፈረ የመቃብር ጉድጓድ መስሎ ታየን፤ ኢምፓየሩ በየቀኑ እየገፈተረ ወደ መቃብር ይከተናል። በመጨረሻም ምርጫው በሕይወትና በሞት መሃል እንደሆነ ገባን።እናም ሕይወትን መረጥን። እኛ አለን።ኢምፓየሩን ግን ወደ መቃብር ሸኝተነዋል።” ሲል የአዲሱ ኢምፓየር አዲስ ገዥ ካዎ ፒ በድርሳኑ ካሰፈረው ላይ  በመቅዳት ፈላስፋው ቻርለስ ሉይስ(ሞንቴስኪዩ) ለፈረንሳዊያን እንዲህ ትቶላቸው አልፏል። ለፈረንሳዊያን ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያዊያንም እንዲህ ተርፏል። ከታሪክ ለሚማሩ  የሰው ልጆች ሁሉም እንዲህ ተመዝግቦ በክብር ተይዟል።ምክንያቱም የቀደመውን ዘመን ጠንቅቀህ ካልመረመርክ እና ካልተረዳህ ከፊት የሚመጣው ዘመን ምንነት አይገባህም! የሚመጣውን ዘመን ምንነት ከኋላ ታሪክ የማይማር ሕዝብ የኋለኛውን ቃኝቶ ወደፊት በሚገሰግስ ሕዝብ መዳፍ ላይ ይወድቃል። የኋላውን ታሪክ የጣለ ወይም ያልመረመረ ሕዝብ ምርጫው ሁለት ነው።አንዱ ባለፈው ታሪክ ሲጣላ ባለበት ሲረግጥ ይኖራል። ሁለተኛው ምርጫ የኋላውን ባልመረመሩ ግን ወደፊት መራመድ ለሚሹ ሲሆን እነዚህም ታዲያ ሌሎች በቃኙት የስልጣኔ ዑደት ተጣጥሞ መራመድ ቢከብዳቸውም በዚያ አልፈው ነጋቸውን ለማሳመር ተስፋ ሰንቀው የሚጓዙ ናቸው።

Advertisement

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.