ሩሲያ በሶሪያ

ቅዱስሩሲያ በአረቡ ዓለም ያላት ብቸኛ አጋር ሶሪያ ናት። ይህን አማራጭ የሌለው ዝምድና መተው ማለት መካከለኛው ምስራቅን የተንተራሰ ጥቅሟን ሙሉ ለሙሉ ማጣት ማለት ነው። የዛሬ ሳምንት እሮብ ዕለት የሩሲያ ፓርላማ “በሶሪያ የሚገኙ ሽብርተኞችን ለማጥቃት ወታደራዊ እርምጃ ይወሰድ።” ብሎ ካጸደቀ ከሰዓታት በኋላ ነበር የሩሲያ ዲፕሎማቶች ባግዳድ ወደሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በማምራት “ሽብርተኞች ላይ የአየር ጥቃት ልንከፍት ስለሆነ የአሜሪካን የጦር ጀቶች ከሶሪያ ሰማይ ላይ መራቅ ይኖርባቸዋል።” የሚል መልክት አስተላለፉ። ይህ በሆነ በአንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ ሩሲያ በበሽር አል አሳድ ተቃዋሚዎች ላይ የመጀመሪያውን ጥቃት ሰነዘረች። የአሜሪካ መከላከያ ዲፓርትመንት ፔንታጎን የሩሲያን ጥሪ በመስማት በሶሪያ የሚያደርገውን የበረራ አቅጣጫ መለወጡን እና በሶሪያ ሰማይ ላይ በየቀኑ በረራ ማድረጉን እንዳላቋረጠ አስታውቋል።

አሜሪካ ለሶሪያ ሰላም የሚመጣው በሽር አላሳድን ከስልጣን በማስወገድ ብቻ ነው ብላ ታምናለች። የሩሲያ አቋም ደግሞ ከዚህ ተቃራኒ ነው። ከሁሉም በላይ የሶሪያ ጎረቤት የሆነችው ቱርክ በሽር አላሳድ ከስልጣን እንዲወገድ ትፈልጋለች። ። “ሩሲያ ሽብርተኞችን ሳይሆን ለዘብተኛ የሶሪያ ተቃዋሚዎችን እየደበደበች ነው።” ያሉት የቱርክ ጠቅላይ ሚንስትር በሶሪያ በመደብደብ ላይ ባሉት የኢድሊብ እና አሌፖ ከተማዎች ውስጥ አይሲስ እንደሌለ ተናግረዋል። ከሰማይ ላይ በሩሲያ የጦር ጀቶች በመታገዝ በእነዚሁ ከተሞች የምድር ጥቃት የከፈቱት በኢራን እና በኢራቅ ሽዓቶች የሚታገዙት የሶሪያ መንግስት ወታደሮች ብዙም መፈናፈኛ እንዳላገኙ ተሰምቷል። ትናንት በተካሄደው በዚህኛው ውጊያ ሩሲያ ከሰላሳ ሰባት በላይ የአየር ጥቃት ያካሄደች ቢሆንም በምድር ላይ ውጊያው ግን በኢራን አብዮታዊ ዘብ የሚታገዘው የሶሪያ መንግስት ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በተቃዋሚዎች ሲነዱ ታይተዋል። ምናልባትም ወታደራዊ ተሽከርካሪዎቹ በአሜሪካ ሚሳየል ሳይመቱ እንዳልቀረ ተገምቷል። በዚህ የተበሳጨችው ሩሲያ ተምዘግዛጊ ክሩስ ሚሳየሎችን ከካስፒያን ባህር ላይ በማስወንጨፍ 1500ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙትን የሶሪያን ከተሞች ደብድባለች።

ፑከሳውዲ አረቢያ በመቀጠል በሽር አል አሳድን በመቃወም የምትታወቀው ቱርክ ትናንት በድጋሚ የአየር ክልሏ በሩሲያ የጦር ጀት መጣሱን አስታውቃለች። ቱርክ ወደ ግዛቷ የገባውን የሩሲያ ጀት በኤፍ 16 ጀቶቿ በመክበብ በተነገረው አቅጣጫ ብቻ በመብረር የአየር ክልሏን ለቆ እንዲወጣ አድርጋለች። ጠቅላይ ሚንስትር አህመት ዳቮትግሉ “ቱርክ ሉዓላዊነቷን ለማንም አታስደፍርም።በዚህ ዙሪያም ድርድር አይኖርም።” በማለት ሩሲያ ድንበራቸውን እንድታከብር በሃገራቸው ለሚገኘው የሩሲያ አምባሳደር ትንናት አስታውቀዋል። የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር አሽ ካርተር በበኩላቸው “የሩሲያ ስትራቴጂ የውድቀት ስለሆነ ከእርሷ ጋር አንተባበርም። ሩሲያ በሽር አላሳድን ከውድቀት አታድነውም!” ብለዋል።ሩሲያ በሽር አላሳድን ለጊዜው በስልጣን ላይ እንዲቆይ ከማድረግ ውጭ የተበታተነችውን ሶሪያ ግን በፍጹም አንድ ማድረግ እንደማትችል የብዙዎች እምነት ነው።

ከሳውዲ አረቢያ በመቀጠል በሽር አል አሳድን በመቃወም የምትታወቀው ቱርክ ትናንት በድጋሚ የአየር ክልሏ በሩሲያ የጦር ጀት መጣሱን አስታውቃለች። ቱርክ ወደ ግዛቷ የገባውን የሩሲያ ጀት በኤፍ 16 ጀቶቿ በመክበብ በተነገረው አቅጣጫ ብቻ በመብረር የአየር ክልሏን ለቆ እንዲወጣ አድርጋለች። ጠቅላይ ሚንስትር አህመት ዳቮትግሉ ቱርክ ሉዓላዊነቷን ለማንም አታስደፍርም።በዚህ ዙሪያም ድርድር አይኖርም።” በማለት ሩሲያ ድንበራቸውን እንድታከብር በሃገራቸው ለሚገኘው የሩሲያ አምባሳደር ትንናት አስታውቀዋል። የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር አሽ ካርተር በበኩላቸው “የሩሲያ ስትራቴጂ የውድቀት ስለሆነ ከእርሷ ጋር አንተባበርም። ሩሲያ በሽር አላሳድን ከውድቀት አታድነውም!” ብለዋል። ለነገሩ ሩሲያ በሽር አላሳድን ለጊዜው በስልጣን ላይ እንዲቆይ ታደርግ እንደሆን እንጅ የተበታተነችውን ሶሪያ አንድ ማድረግ እንደማትችል ግን የብዙዎችም እምነት ነው።

የሩሲያ ኢኮኖሚ በአውሮፓ እና አሜሪካ ማዕቀብ እንዲሁም በነዳጅ ዋጋ ማሽቆልቆል ምክንያት ቁልቁል መውረድ ከጀመረ ከራርሟል። በ2015ዓ/ም ብቻ 3ነጥብ 8በመቶ የወደቀው የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በቀጣዩ ዓመት ይሄን የቁልቁለት ጉዞ በማጠናከር 4ነጥብ 4በመቶ ይወድቃል ተብሎ ይጠበቃል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ፖሊሲ ካውንስል ሃላፊ ፊዮዶር ሉክያኖቭ “በሶሪያ የሩሲያ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ይበልጥ የሚያፈራርስ ነው።” በማለት ተችተዋል።

የሩሲያ ትላልቅ ባንኮች እና ኩባንያዎችም መንግስት ከምዕራባዊያን ጋር ያለውን ግንኙነት በእልህ ሳይሆን በድርድር መፍታት ካልቻለ እዚህ ያለውን የኢኮኖሚ ምስቅልቅል ሶሪያ በመሄድ አንሸፍነውም በማለት ለቭላድሚር ፑቲን በግልጽ ተናግረዋል። ከ1985ዓ/ም እስከ 1991ዓ/ም ድረስ የሶቬት ሕብረት መሪ የነበሩት የ82ዓመቱ አዛውንት ሚኻየል ጎርባቾቭ ባለፈው ወር ታትሞ ገበያ ላይ በዋለው “ዘ ኒው ሩሲያ: አፕሄቭል ኤንድ ዘ ፑቲን ሲስተም” በሚለው መፅሃፋቸው ቭላድሚር ፑቲንን “እልኸኛ፣ግልፍተኛ እና ለሩሲያ ብቻ ሳይሆን ለዓለምም አደገኛ የሆነ ሰው ነው።” በማለት ገልጸውታል።

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.