የስደተኞች እጣ-ፈንታ እና የአንጌላ ሜርክል ፈተና

አንጌላ መርክል

የጀርመን ህዝብ ይሰጣቸው የነበረው ድጋፍ በየቀኑ እያሽቆለቆለ መሆኑን የተረዱት የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አንጌላ መርክል ትናትን ምሽት ባልተለመደ ሁናቴ በቴሌቪዥን ብቅ ብለው ስደተኛ መቀበላቸው ትክክለኛ አቋም መሆኑን ለማስረዳት ሞክረዋል። ይሁን እንጅ የሴትየዋ አቋም ለአብዛኛው ጀርመናዊ የሚዋጥ አልሆነም። ባለፈው ሳምንት ደች ላንድ ትሬንድ በሰበሰበው የህዝብ አስተያየት ቻንስለሯ ያላት የህዝብ ድጋፍ በ54በመቶ ቀንሷል። ይህም ጀርመንን ለሶስተኛ ጊዜ በጠቅላይ ሚንስትርነት የሚመሩት አንጌላ መርክል ቀጣይ የፖለቲካ ጉዟቸው አደገኛ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን ያሳያል።

‘ፎርሳ’ የሚባለው የጀርመን የህዝብ አስተያየት መሰብሰቢያ ይፋ እንዳደረገው መረጃ ሁለት ሶስተኛው የሃገሪቱ ህዝብ የዘንድሮውን የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁትን የሃገራቸው ጠቅላይ ሚንስትር “ሽልማቱ አይገባቸው!” ብሎ ያምናል።የጀርመን ህዝብ አቋም ምንም ይሁን ሴትየዋ ግን ሽልማቱን ሳያገኙ እንደማይቀር ተገምቷል። የ2015ዓ/ም የሰላም የኖቤል ሽልማት አሸናፊ በነገው ዕለት ኖርዌይ መዲና ኦስሎ ይፋ ይደረጋል።

ቻንስለር አንጌላ መርክል በአውሮፓ ህብረት ህግ መሰረት የአውሮፓ ሃገራት ባላቸው የህዝብ ብዛት አንፃር ስደተኞችን በቁጥር መከፋፈል የሚለውን ህግ የቀድሞዎቹ የምስራቅ አውሮፓ ሃገራት ተቃውመዋል። ሃንጋሪ እና ክሮሽያ “ለአንድም ስደተኛ የሚሆን ቦታ የለንም።” ብለዋል።የጀርመን እና የፈረንሳይ መሪዎች 28ቱ የአውሮፓ ሃገራት ስደተኞችን ለመከፋፈል የቀረበውን አዲስ ዕቅድ እንዲቀበሉትዕ ትናንት ለአውሮፓ ፓርላማ በጋራ ንግግር አድረገዋል።እንግሊዝ በበኩሏ “ጥሪው እኔን አይመለክትም።”ብላለች። በነገራችን ላይ እንግሊዝ እና ዴንማርክ ከኢምግሬሽን ጋር ተያያዥ የሆኑ የአውሮፓ ህብረት ህጎችን የመተግበር ግዴታ የለባቸውም። ይህን ስምምነት የፈረሙት ሲፈልጉ ሊቀበሉ ያልተመቻቸው ጊዜ ደግሞ እንዲወጡ ሆነው ነው።ለምን? መጀመሪያውኑ እንዲህ ያለ ውሳኔ ሉዓላዊነታችንን አሳልፎ ከመስጠት አይተናነስም በማለት በመቃወማቸው ነው።

ብብብብየአውሮፓ ፓርላማ አባል እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ቀንደኛ ተቀዋሚ መሆናቸው የሚታወቀው ወይዘሮ ማሪን ሌ ፔን ፕሬዝዳንት ሆላንዴ በፓርላማው ውስጥ የጀርመንን አቋም በማንጸባረቃቸው “የጀርመን ምክትል ቻንስለር” ሲሉ አላግጠውባቸዋል። በዚህ የተበሳጩት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት “ያንች አቋም ፈረንሳይን ወደ ድሮው ብሄርተኛነት በመመለስ ከሌሎች ጋር ለማቃቃር ነው” ሲሉ በንዴት ምላሽ ሰጥተዋል።

የጀርመን ባቫሪያ ክልል አስተዳዳሪ በበኩላቸው አንጌላ መርክል አቋሟን ካልፈተሸች ክልሉ ስደተኞችን መቀበል እንደሚያቆምና ወደ ግዛቱ እንዳይገቡም እራሱ መከላከል እንደሚጀምር አስታውቋል። የአንጌላ መርክል የክርስቲያን ዴሞክራቲክ ዩኒየን ጋር በጥምር መንግስት ያዋቀረው የባቫሪያን ክርስቲያን ሶሻል ዩኒየን ፓርቲ መሪ ቻንስለሯ አቋሟን እንድትቀይር በግልፅ ጠይቀዋል።

ሰላሳ አራት የክርስቲያን ዴሞክራቲክ ዩኒየን አባላት ትናንት ለቻንስለሯ በፃፉት ግልጽ ደብዳቤ “የምትከተይው አቋም የጀርመናዊያንን እሴት፣ባህል እና የአኗኗር ዘይቤ አደጋ ላይ የሚጥል ነው።”በማለት ፓርቲውን መሰናበታቸውን አስታውቀዋል። በፓርቲው አባላት እና በየክፍለ ሃገሩ ያሉት ባለስልጣናት ከሴትየዋ አቋም ጋር በተቃራኒው ፓርቲውን አደጋ ላይ እንደሚጥለው ያመነው የክርስቲያን ዴሞክራቲክ ዩኒየን  የአንጌላ መርክል አቋም ከፓርቲው ፖሊሲ ጋር የሚጋጭ እና ፓርቲውን የማይወክል መሆኑን አስታውቋል።

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.