የጀርመን ፖለቲካ እና የስደተኞች ጉዳይ

ጀርምበመስከረም ወር ብቻ 200ሽህ ሶሪያዊያን ወደ ጀርመን የገቡ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2014ዓ/ም ወደ ጀርመን ከገቡ ጠቅላላ ስደተኞች ቁጥር ይበልጣል። አምና የስደተኞች የጥገኝነት ጥያቄ ማመልከቻዎችን ለመመልከት የሚፈጀውን ጊዜ ከ7 ወራት ወደ 3 ወራት ለመቀነስ ሲንቀሳሰቅ የቆየው የፌደራል ማይግሬሽን እና ሪፊዩጅ ቢሮ ገና በዘንድሮው የስድተኞች ጎርፍ ምክንያት እቅዱን ማሳካት እንዳልቻለ በማስታወቅ “ባለፉት ስድስት ወራት የተላኩ እና ገና ያልተመለከትኩት ከ300ሽህ በላይ ማመልከቻዎች አሉ።” ብሏል።  አብዛኞቹ የሶሪያ ስደተኞች ከጀርመን ውጭ በሌላ የአውሮፓ ሃገራት እንኳ መኖር የማይሹ ሲሆን ይህንንኑ ፍላጎታቸውን እውን እንዲያደርግ እና በተለይ የሶሪያ ስደተኞችን በልዩ ትኩረት በማየት የጥገኝነት ማመልከቻቸውን ሁሉ ውድቅ ሳያደርግ እንዲቀበል ከጀርመን መንግስት ልዩ ደብዳቤ የደረሳቸው የጀርመን የፌደራል ማይግሬሽን እና ሪፊዩጅ ቢሮ ሃላፊ ማንፍሬድ ሽሚት ይህንን በመቃወም ባለፈው ሳምንት ስራቸውን ለቀዋል። የጀርመን የስለላ እና የደህንነት መስሪያ ቤት ሃላፊም “የሶሪያን ስደተኞችን ዝም ብላችሁ ተቀበሏቸው የሚለው አካሄድ ለውስጥ ደህንነታችን አደጋ አለው።”በማለት የጀርመን መንግስት አቋሙን እንዲመረምር ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

“ስደተኛን እንቀበል!” በሚለው ፖሊሲያቸው በዓለም ዓቀፍ ደረጃ መልካም ዝናን ያተረፉት የጀርመን ቻንስለር በሃገር ቤት የፖለቲካ ድጋፍ እየከዳቸው መሆኑ አሳስቧቸዋል። የስደተኞቹን ጉዳይ የሚመለከት ልዩ ቡድን በጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት እንዲቋቋም ያደረጉት አንጌላ ሜርክል በትናንትናው ዕለት ለወትሮው የስደተኞችን ጉዳይ ከሚመለከተው የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ቶማስ ዴ ማዜር ስልጣን ላይ ይህንኑ ጉዳይ የሚመለከተውን  ሃላፊነታቸውን በልዩ ሁኔታ በጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት(በፌደራል ቻንስለሪ) ወደ ተቋቋመ አዲስ ቡድን መሪ እና የፅ/ቤቱ ሃላፊ ፒተር አልትማየር ተዛውሯል። ቀደም ሲል የሃገሪቱ መከላከያ ሚንስትር የነበሩት እና የአንጌላ መርክል ቀኝ እጅ ተደርገው የሚታዩት ቶማስ ዴ ማዜር በፌደራል መንግስቱ ጣልቃ ገብነት የማይግሬሽን እና ሪፊዩጅ ቢሮ ሃላፊ ማንፍሬድ ሽሚት ከስራ መልቀቅ የተቀየሙ ሲሆን እሳቸውም ይህንኑ በመቃወም እሳቸውም  ስልጣናቸውን ሊለቁ ይችላሉ ተብሏል።

የአንጌላ መርክል የክርስቲያን ዴሞክራቲክ ዩኒየን እና የባቫሪያን ክርስቲያን ህብረት እህት ፓርቲያቸው ሴትየዋ የስደተኞቹን ጉዳይ ቀለል ተደርጎ እንዲታይ ማድረጋቸውን ወቅሰዋል።  59በመቶ የጀርመን ህዝብ ቻንስለሯ ስደተኞችን በሃንጋሪ በኩል እንዲገቡ መፍቀዳቸው ትልቅ ስህተት ነው ብለው ያምናሉ። የስደተኞቹ ጉዳይ የጀርመንን ፖለቲካ ማመሱን የቀጠለ ሲሆን ይህን በአግባቡ ማስኬድ ካልተቻለ የአንጌላ መርክል የፖለቲካ ህይዎት መቋጫም ሊሆን ይችላል። በርግጥ ጉዳዩ ለአውሮፓ ህብረትም ፈተና ሆኗል። ለዚህም ይመስላል የጀርመን እና የፈረንሳይ መሪዎች በጉዳዩ አሳሳቢነት ላይ ለአውሮፓ ፓርላማ ዛሬ በጋራ ንግግር ያደረጉት። የሁለቱ ሃገር መሪዎች በጋራ ለአውሮፓ ፓርላማ በጋራ ንግግር ያደረጉት ከ25ዓመታት በፊት በ1989ዓ/ም የበርሊን ግምብ ከፈረሰ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነበር።

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.