የግለሰብ ነፃነት እና ብልፅግና!

abraየግለሰብ ነፃነት ማለት ሰው በወደደው መንገድ ኑሮውን እንዲመራ፣ ህይወቱን ወደፊት እንዲያራምድ፣ ፍላጎቱን ለማሟላት እንዲጥር፣እንዲፈጥር፣እንዲሰራ፣እንዲነግድ ወይም ከሌሎች ጋር በሚያደርገው ትብብር እና ማህበረሰባዊ ትስስር ሁሉ በፍቃዱ ብቻ ይሁን ማለት ነው። ይህ ግን ዝም ብሎ ባዶ ሜዳ ላይ ሊሆን አይችልም። ስለዚህ ለዚህ ስኬት የሚያስፈልጉ ሌሎች ተቋማት አሉ። ከነዚህ ውስጥ መንግስት አንዱ ነው። መንግስት አስፈላጊ የሚሆንበት ዋነኛ ምክንያት የሰዎችን የግለሰብ ነፃነት በሕግ እንዲያስጠብቅ፣ሰዎች በሚያደርጉት ግንኝነት የማጭበርበር ነገርን ሲፈፅሙ በሕግ እንዲቀጣ፣ሲሰርቁ ወንጀለኛውን ሌባ ለፍርድ እንዲያቀርብ፣ የንግድ ውል ላይ አለመስማማት ሲኖር በሕግ እንዲዳኝ፣ የህዝብና የግለሰብ ንብረቶችን ከዘራፊዎች እንዲጠብቅ ነው።ስለዚህ ይህ ሁሉ እንዲሆን ጠንካራ የሕግ ስርዓት ወሳኝ ሲሆን መንግስት በተሰጠው ስልጣን ላይ አላግባብ እንዳይወሰልት ደግሞ በሕገመንግስት አማካይነት ስልጣኑ ገደብ እንዲበጅለት ይደረጋል።

የመፍጠር ችሎታ እና የላቀ አስተሳሰብ መኖርም ብቻውን ዋጋ የለውም።እንደዚያ ዓይነት ሰዎች በኛም ሃገር ሞልተዋል። ይህን ችሎታቸውን እና አስተሳሰባቸውን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩበት፣ ወደ ምርት ቀይረው ለህዝብ የሚያቀርቡበት በነፃነት የሚገበያዩበት እና የምርት ውጤታቸውን የሚያቀርቡበት ነፃ ገበያ ያስፈልጋቸዋል። ይህን ሲያደርጉ ፈጠራየን መንግስት ቢቀማኝስ እያሉ አሊጨናነቁ አይገባም። የፈጠራ ሃሳባቸውን ገንዘብ ላለው ኢንቨስተር ወስደው ያስዩታል። ከፈለገም በሃሳቡ ላይ አንተ ገንዘብህን አዋጣና አብረን እንስራ ይሉታል። እሱም ፈጠራውን አዋጭ መሆኑን በባለሙያወች አስጠንቶ ገንዘቡን የሰውየው ሃሳብ ላይ ኢንቨስት ያደርጋል። በዚህም ሁለቱም ተያይዘው የሃብት ማማ ላይ ይሰቀላሉ ማለት ነው። በዚህ መሃል ታዲያ የሰዎቹን ሃሳብ የሚያጣጥሉ እና የሚያራክሱ ብዙዎች ሞልተዋል። የሲኤንኤን ባለቤት ቴድ ተርነር፣ የማይክሮ ሶፍት ቢልጌትም እና የፌስቡኩ ዙከርበርግ ዛሬ በምናውቃቸው ደረጃ የሃብት ማማ ላይ ከመንጠላጠላቸው በፊት የብዙ አዋቂዎች፣ቢዝነስ ተንታኞች፣የኢንቨስት መንት አናሊስቶች፣እና ሌሎች በርካቶች መሳቂ የነበሩበት ወቅት ነበር።እነዚህ ሰዎች ግን ከዚያ በፊት አለም የማታውቀውን ነገር ከአይምሯቸው ውስጥ አምጠው እንደወለዱ እርግጠኞች ስለነበሩ ተስፋ በመቁረጥ ፋንታ ከአንዱ ኢንቨስተር ወደ ሌላው እየሄዱ ለማሳመን በመቻላቸው፣አንዱ ጋር በዋጋ ሲጣሉ ሌላው ጋር ሄደው በመደራደር እና በማወዳደር ህልማቸውን እውን አድርገዋል። እኛም የነሱ ፈጠራ ውጤት ተጠቃሚ ሆነናል። እነዚህ ሰዎች ይሳካላቸው ዘንድ ሙያቸውን እና የፈጠራቸውን ውጤታቸውን ተመርቶ በገበያ ላይ ይወጣ ዘንድ ማንም ጫናም ሆነ ጣልቃ አልገባባቸውም።

ሰዎች በፈጠራ ውጤታቸው እና በንብረታቸው ላይ በነፃነት ማዘዝ የሚያስችላቸው ስርዓት ባለበት ሃገር ሁሉ ብልፅግና አለ። ሰዎች በንብረቱ ላይ  ሙሉ ስልጣን እንዳለው ካተረዳ አዳዲስ ፈጠራዎችን፣የምርምር ስራዎችን፣በገበያ ላይ የሚቀርቡ ምርትና አገልግሎቶቹን ወዘተ እያሻሻሉ በመስራት እና ኑሮን የሚያቃልሉ የህይዎት መንገዶችን በመቀየስ የተሻለ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ያደርጋሉ። እነዚህ ሰዎች ግን አሁንም የተሟላ ነፃነት እንዲያገኙ መሬትን ጨምሮ የግለሰብ ንብረት ባለቤትነትን የሚጠብቅ ጠንካራ ሕግ ይፈልጋሉ። ይህ ሕግ ሰዎች ዛሬ ጥረው ግረው፣አውጥተው አውርደው፣ለፍተውና ደክመው ያገኙት ሃብት ነገ በማናቸውም ሰው ሰራሽ ምክንያት እንደማያጡት እርግጠኛ ስለሚያደርጋቸው ይበልጥ እንዲሰሩ፣ይበልጥ እንዲለፉ እና ሃብት እንዲያስፋፉ ያደርጋቸዋል።ሃብት መስፋፋቱ ደግሞ ለማህበረሰቡ ስራ እና ተጨማሪ እሴት ስለሚፈጥር ለሃገር እድገት ወሳኝ ነው። በአሜሪካ ከንብረት ባለቤቱ ፍቃድ እና ፍላጎት ውጭ በግለሰብ ንብረት ላይ መወሰን የሚችል፣ለልማታዊ ስራ፣ለመንገድ ስራ ወዘተ ብሎ ማፍረስ የሚችል አንድም የመንግስት ተቋም የለም። የአሜሪካ ኮንግረስም ሆነ ፕሬዝዳንት ግለሰቦች ለፍተው በሚያገኙት ንብረት ላይ የመወሰን ቀርቶ በጉዳዩ ላይ የመሰብሰብም ስልጣን የላቸውም። በዚህም ምክንያት በየትኛውም ዓለም መስራት የሚችሉ፣መፍጠር የሚችሉ እና ሃብት ማፍራት የሚችሉ ሰዎች ሁሉ ተመራጭ የስደት ሃገር አድርጓታል። አሜሪካ ዛሬ ድረስ ልዕለ ሃያል የሆነችው ከየትኛው ዓለም በበለጠ በነፃነት ማሰብ የሚችሉ  ብዙ ኢንተርፕርነሮች ያሉባት ሃገር በመሆኗ ነው። ዘ ላንድ ኦፍ ኦፖርቹኒቲ የምትባለውም ለዚሁ ነው።

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.