አዳም ስሚዝ በግለሰቦች ሚና ዙሪያ በዶ/ር ቶም ፓልመር

አዳም ስሚዝ

አዳም ስሚዝ

አዳም ስሚዝ “ስግብግብ ዓለምን ያሾራታል!” በሚለው አባባል ዕምነት ነበረው እየተባለ ሲነገር ዘወትር ይደመጣል፡፡ ይሁን እንጂ አዳም ስሚዝ ራስ ወዳድነት ላይ ብቻ መመስረቱ ዓለምን የተሻለች ስፍራ ያደርጋታል የሚል ዕምነት አልነበረውም፡፡ የራስ ወዳድነት ባሕርያትንም አላስፋፋም ፤ አላበረታታምም፡፡ The Theory of Moral Sentiments በተባለ ስራው ውስጥ የተሰጠው ሰፊ ማብራሪያ ለዚህ ዓይነቱ የአረዳድ ስህተት ሙሉ ምላሽ የሚሰጥ ነው፡፡ አዳም ስሚዝ የራስ ወዳድነት አራማጅ ያልነበረ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ደህንነት ራስን መስዋዕት ማድረግ ለዚህች ዓለም አይበጃትም ብሎ የሚያምን ሰው ነበር፡፡ ስቴቨን ሆልምስ “The Secret History of Self-Interest” በተባለ ጥናታዊ ፅሑፉ ውስጥ እንዳሰፈረው ብዙዎቹ እንደ ቅናት ፣ ሌሎችን የማሰቃየት መንፈስ ፣ በቀልና በስሜት መቸኮል እንዲሁም የፍላጎት ማጣት የመሳሰሉት የሚያስከትሉትን የውድመት ውጤቶች አዳም ስሚዝ በጣሙኑ ጠንቅቆ ያውቃል ይላል፡፡ ሌላው ቀርቶ ከፍተኛ የግለኝነት ፍላጎት መኖር በራሱ ሌሎችንም ሊጠቅም እንደሚችል መረዳቱን በጥናቱ ላይ አስፍሯል።

ለምሳሌ ስሚዝ በሚነግረን አንድ ታሪክ ውስጥ አንድ የድሃ ልጅ ሐብት ለማካበት በነበረው ጥልቅ ፍላጎት ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይል እንዲሰራ ይገደዳል፡፡ ዕድሜ ልኩን ሲለፋ ከኖረ በኃላ ያገኘው ደስታ ግን መንገድ ዳር ተቀምጦ ፀሐይ ከሚሞቅ ተራ ለማኝ ያልተሻለ ሆኖ ያገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ የድሃ ልጅ ስራውን ከመስራት ባሻገር በውስጡ ከፍተኛ ውስጣዊ የግል ፍላጎት ተነሳሽነት እና ሃብት የማሳደድ ትጋት ማሳደር መቻሉ የብዙ ሌሎች ሰዎችን ህልውና ዕውን ማድረግ ያስቻለ ሐብት እንዲያፈራና እንዲያካብት እንዳደረገው መረዳት ችሏል።

አዳም ስሚዝ ሰፊ በሆነ የኢኮኖሚ መዋቅር ውስጥ ከመንግስት ተቋማት ወይም ከፖለቲከኞች ጋር የተሳሰረ የግል ፍላጎት አዎንታዊ ውጤቶችን የማይፈጥር መሆኑን ይጠቁማል። ለምሳሌ የነጋዴዎች ፍላጎት የማምረቻ ወጪ እንዲቀንስና የመሸጫ ዋጋ እንዲጨምር የሚወስኑ ሕብረቶች (cartels) እንዲፈጠሩ ፣ ጥቅሞቻቸውና ፍላጎቶቻቸው እንዲጠበቅላቸው መንግስትን ወደ ማሳመን ሊያመራ ይችላል። “በርግጥ በዚህ አካሔድ ዘወትር የሚኖር ንግድ በታላቋ ብሪታኒያ ሙሉ በሙሉ ዳግም ይገነባል ብሎ ተስፋ ማድረጉ ተምኔታዊ ዓለም በአገሪቱ ላይ ይመሰረታል ብሎ ተስፋ የማድረግን ያህል ቂልነት ነው።” በማለት ነበር የገለጸው-አዳም ስሚዝ።

እንደ አዳም ስሚዝ ትንታኔ ከሆነ ገበያ ራስ ወዳድነትን ወይም ስግብግብ መሆንን ያስፋፋል ብሎ ለማሰብ አሳማኝ ምክንያት የለም፡፡ ይልቁንስ ገበያ ለራስ ወዳዶች ብቻ ሳይሆን ሃብታቸውን በማካበት ሌሎችን ለመርዳት ለሚጥሩት ሰዎችም አቅማቸውን ያጎለብትላቸዋል። የዚህ አይነት ዓላማ ካላቸው ውስጥ ጆርጅ ሶሮስ እና ቢል ጌትስ በምሳሌነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እነኚህ ሃብታሞች እጅግ ከፍተኛ ከሆነ ገቢያቸው ውስጥ ቢያንስ ከፊሉን ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሌሎችን ለመርዳት ይለግሱታል። በአትራፊ ድርጅቶቻቸው አማካይነት የሚሰበስቡት ገንዘብ እና ሐብት እነርሱን ለጋስ መሆን አስችሏቸዋል።

አንዲት የበጎ አድራጎት መንፈስ የሰረጻት ሴት ሐብቷን በሙሉ ሰዎችን ለመመገብ ፣ ለማልበስና ኑሮአቸውን ለማመቻቸት ተግባር እንዲውል ትፈልጋለች እንበል፡፡ ዕርዳታዋን ለሚጠባበቁ ሰዎች በዝቅተኛ ዋጋ አልባሳትን ፣ ምግብንና መድኃኒቶችን ማግኘት የሚያስችላት ገበያ ነው፡፡ ገበያ የለጋሾችን አቅም ያሳድጋል። የበጎ አድራጊዎችንም ሥራ እውን እንዲሆን መንገድ ይጠርጋል።

በእርግጥ ሰዎች በገበያ ውስጥ ያላቸው አላማዎች ራስን ያማከሉ እና ትርፍ ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ ይህ ማለት ግን የሌሎን ፍላጎትና ደህንነት ለምሳሌ የቤተሰብ አባላት ፣ የጓደኞች ፣ የጎረቤቶችና ጨርሶ የማናውቃቸው ሰዎች ጉዳዮች ጭምር አያሳስብም ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ምክንያቱም ሌሎችን አሽቀንጥሮ በመጣል የሚዘልቅ ንግድ በገበያ ላይ አይቆይምና! ወደ ኢንዱስትሪና የንግድ ስራ ከመግባት ይልቅ ወደ ፖለቲካው መግባትን የሚያወድሱ ሰዎች ፣ ፖለቲካ እጅግ የበዛ ጉዳትን እንጂ መልካም ነገርን ሲፈጥር ማየቱ እጅግ የጠበበ መሆኑን ቢያስታውሱ ጠቃሚ ነው፡፡

ገበያ የፖለቲካን ያህን በሰዎች ራስ – ወዳድ መሆን ላይ የተመሰረተ አይደለም ወይም ራስ – ወዳድ መሆንን በቅድመ ሁኔታነት አይጠይቅም፡፡ በገበያ ውስጥ የሚካሄድ ልውውጥ የራስ – ወዳድነትን ባሕርይ አያጎለብትም። ከፖለቲካው በተቃራኒ በፈቃደኛ ተሳታፊዎች መካከል በሚካሔድ የነፃ ገበያ ሥርዓት ሐብትንና ሰላምን መፍጠር ያስችላል። ልግስና ፣ ጓደኝነትና ፍቅር የሚጎለብቱበትን ሁኔታዎች ይከሰታል፡፡

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.