የፍላጎት ግጭት – በጨዋዎቹ ምድር (በማኦ ዩሺ)

ማኦ ዩሺ

ማኦ ዩሺ

በ18ኛውናበ19ኛውክፍለዘመናትመካከልቻይናዊውደራሲሊሩዜን “የመስታወትውስጥአበቦች” በሚልርእስ አንድ ልብወለድ ይጽፋል። በልብ ወለዱ ታሪክ ውስጥ አገሩን ጥሎ ወደ ‘ጨዋዎቹምድር’ ስለተሰደደ ታንግኦስለተባለሰውይተርካል፡፡ይህሰውበደረሰበት በዚያ ምድር ለማመን የሚያዳግት እንግዳ ነገር ይመለከታል። የጨዋወቹ ምድር ነዋሪዎች በሙሉ የሌሎችን ሰዎች ጥቅም ለመጠበቅ ሲሉ የራሳቸውን ጥቅም የራሳቸውን ጥቅም አሳልፈው ይሰጣሉ። በዚህም ምክንያት‘ጨዋዎቹ’ የመከራ ኑሮን ይገፋሉ። ታንግኦ ሸቀጦችን በሚገዙና በሚሸጡ ሰዎች መካከል የተመለከተውን የግብይት ሁኔታ እንዲህ ይገልጻል። ገዥ ወደአንድ መደብር ጎራ ይላል። በመደብሩ የሚገኙ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው እቃዎችንም ይመራርጣል። የእቃዎቹ ዋጋ ግን ዝቅተኛ ሆኖ ያገኛል። ገዥ ሻጭን “ጥቅምህን በዝቅተኛ ዋጋ ብወስድብህ ጥሩ ስሜት ሊኖረኝ አይችልም። እናም ዋጋ ካልጨመርክ ልንገበያይ የምንችል አይመስለኝም።” ይለዋል።

ሻጩም “ወደኔመደብርመምጣትህበራሱ ለኔትልቅፋይዳአለው፡፡የእቃዎቸ ዋጋ ሰማይ ነክቶ ሳለ አንተ ግን ዝቅተኛ ነው እያልከኝ ነው። ከዚህ በላይ ዋጋ እንድጨምር ፈልገህ ከሆነ በሃሳብህ ለመስማማት እቸገራለሁ። እኔ ዋጋ ስለማልጨምር ከሌላ መደብር ብትገዛ ይሻልሃል።” በማለት ይመልስለታል። ገዥውም “ከፍተኛ ጥራት ያላቸው እቃዎችህ ዋጋ ዝቅተኛ ነው። ይህ አንተን አያከስርህም እንዴ? በተረጋጋ መንፈስ እንነጋገር እንጅ።” ይለዋል።ገዥና ሻጭ ቢጨቃጨቁም ሻጭ የዋጋ ጭማሪ አላደርግም በሚለው አቋሙ ይጸናል። ገዥም ይናደድና ለመግዛት አቅዶ ከነበረው የእቃዎች መጠን ግማሹን ያህል ብቻ ለመግዛት ይወስናል። ድንገት ወደ መደብሩ የገቡ ሽማግሌዎች የገዥንና የሻጭን አታካራ ይሰማሉ።ኋላም በሽማግሌዎቹ አደራዳሪነት ገዥው ለመግዛት ካሰበው የእቃዎች መጠን ሰማንያ በመቶ(80%) ያህሉን እንዲወስድ ይደረጋል።

የልቦለዱ ታሪክ ይቀጥልና ገዥ የእቃዎቹ ጥራት ከፍተኛ ስለመሆኑና ዋጋቸው ግን ዝቅተኛ ስለመሆኑ የሚያስብበትንና ሻጭ ደግሞ እቃዎቹ ተራና አሮጌ መሆናቸውን የሚናገርበት ሌላ ግብይት ይገልጻል። በዚህኛው ግብይት መጨረሻም ገዥ ካሉት እቃዎች መካከል መጥፎ[ጥራት የጎደላቸውን] የሆኑትን መርጦ ይወስዳል። ገዥ ሻጭ አግባብነት የጎደለው ስራ እየሰራ መሆኑን በግብይቱ ወቅት የነበሩ ሰዎችን እንዲመለከቱ በማድረግ ጥፋተኛ ያስብለዋል። በዚህም አካሄድ ገዥው ግማሹን እቃ ከፍተኛ ጥራት ያለው ቀሪውን ደግሞ ዝቅተኛ ጥራት ካለቸው እቃዎች የሚወስድበትን ሁኔታ ያሳያል። በሶስተኛው ግብይት ሁለቱም ወገኖች ለሽያጭ በቀረበ ነሃስ ክብደት እና ጥራት ፍተሻ ላይ ይጣላሉ። ገዥ በቁጣ የነሃሱን የጥራት ደረጃ ያጣጥላል። ክብደቱም በቂ አለመሆኑን ይገልጻል። ሻጭ በበኩሉ የነሃሱ ጥራት የላቀና ክብደቱም በቂ መሆኑን ይከራከራል። ገዥ መደብሩን ለቆ እንደወጣ ሻጭ አላስፈላጊ ናቸው ብሎ የሚያስባቸውን ነሃሶች ከባዕድ ሃገራት ለመጡ የኔ ቢጤዎች ለመስጠት መወሰኑን ይተርካል።

ከላይ ሊሩዜንስለ ‘ጨዋዎቹምድር’ ምድር ከተረከልን ልብ ወለድ ውስጥ ሁለት ቁምነገሮችን እናያለን። የመጀመሪያው ሁለቱም ወገኖች ለየራሳቸው ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅም እየተው ባለበት ሁኔታ ወይም ሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ ጥቅም ለማግኘት አቋም እየያዙ ባሉበት ሁኔታ መተማመን ላይ መድረሳቸውን ያሳያል። ይሁን እንጅ በገሃዱ ዓለም የሚያጋጥሙን፣የምንከውናቸውና በምክንያታዊነት ውሳኔ የምንሰጥባቸው አብዛኞቹ ነገሮች የየራሳችንን ፍላጎቶች ከማስቀደም የሚመነጩ ናቸው። ከራስ ይልቅ ለሌላው የመወገኑ ነገር ውዝግብ ያስቀራል ብለን የምናስብ ከሆነ ስህተት ውስጥ እንወድቃለን። ይህ በጨዋዎቹ ምድር ያለ የዘዎትር ስህተት ነው። እኛም የጨዋዎቹን ምድር ተሞክሮ በመመልከት የሌሎችን ፍላጎት ለውሳኔዎቻችን መሰረት የምናደርግ ከሆነ የዘወትር ንትርክ እናተርፋለን።ችግሮችም የማይፈቱ በመሆናቸው ያለማቋረጥ የተጣመመና የተቀናጀ ማህበረሰብ መፍጠር የሚያስችል ምክንያታዊ መሰረቶችን ፍለጋ ስንባዝን እንኖራለን።

ሁለተኛው ቁምነገር በገሃዱ ዓለም ያለውን የንግድ አሰራር ሁኔታ ይመለከታል። በግብይት ውስጥ ያሉ ሁለት ወገኖች የየራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር ባላቸው ፍላጎት መግባባት ይችሉ ዘንድ እንደ ዋጋ እና ጥራት በመሳሰሉ ነጥቦች ላይ ይደራደራሉ። ይህ ደግሞ ሁለቱም ወገኖች ከስምምነት የሚደርሱበትን ሁኔታ ይፈጥራል። በጨዋዎቹ ምድር ያለውን ተሞክሮ በተነጻጻሪነት ስናይ የዚህ አይነቱ ስምምነት የማይቻል ይሆናል። በልብወለዱ ውስጥ ጸሃፊው ግጭቱን ለመፍታት ሽማግሌዎቹን እና የኔቢጤዎቹን ለማስገባት የተገደደው በዚሁ ምክንያት ነው። እዚህ ላይ ጉልህ እና ወሳኝ እውነታን እናገኛለን። ሁለት ወገኖች የየራሳቸውን ጥቅም በመሻት የሚያደርጉት ድርድሮች ሚዛናዊነትን ያሰፍናል።በተቃራኒው ደግሞ አንደኛው ለሌላኛው ወገን ፍላጎት የሚቆም ከሆነ ስምምነት ላይ መድረስ አይቻልም። የዚህ አይነቱ አካሄድ ዘወትር ከራሱ ጋር የሚጣረስ የማህበረሰብ አባላትን ይፈጥራል። የጨዋዎቹ ምድር ሰዎች የግንኙነት ሚዛን ምን መሆን እንዳለበት ባለመገንዘባቸው ልውውጥን መቋጨት ይሳናቸዋል። ይህ ደግሞ አግባብ ባልሆነ አካሄድ ሰዎች ጥቅም የሚያገኙበትን ዕድል ይፈጥራል። በሌላ አገላለጽ ሥርዓት የለሽ ሰዎች እንዲፈጠሩ በር ይከፍታል ማለት ነው። በመጨረሻም ጨዋዎቹ ጠፍተው ሥርዓት የለሾች ይተካሉ።

እላይ ከተገለጸው ልንረዳው የምንችለው የሰው ልጆች ተባብረው መስራት የሚችሉት የየራሳቸውን ፍላጎቶች በሚሹበት ጊዜ ብቻ መሆኑን ነው።ይህ ነው ለሰብአዊነት ፅኑ መሠረት በመሆን መልካም የሆነች ዓለምን መገንባት የሚያስችለው።የራስን ጥቅም ሙሉ በሙሉ በመተው እና በቀጥታ ለሌሎች ጥቅም በመቆም ሠናይነት ሊታሰብ አይችልም፡፡በእርግጥ ከነባራዊ ሁኔታ በመነሣት ሁላችንም ግጭትን መቀነስ የሚያስችሉንን መንገዶች ማወቅ በተለይም ለሌላው ትኩረት መስጠት እና የራስ ወዳድነት ፍላጎታችንን መቆጣጠር ይኖርብናል። ነገር ግን የሁላችንም ግብ ለሌሎች ሰዎች ፍላጎት አትኩሮት መስጠት ከሆነ በጨዋዎቹ ምድር ሊ ሩዜን የገለፀው ዓይነት ግጭት ይፈጥራል፡፡መጽሐፉ ቀስ በቀስ የሚያቀርበው ማስረጃ በገሀዱ ዓለምና በጨዋዎቹ ምድር ያሉት ችግሮች ተመሳሳይ መንስኤዎች ያላቸው መሆኑን ነው፡፡በሌላ ዓይነት አገላለፅ የግል ፍላጎትን የማሳደድ መርህ በገሀዱ ዓለምም ሆነ በጨዋዎቹ ምድር ግልፅነት እንደሚጎድለው ያሳያል።

በጥንት ዘመንም ሆነ በዘመናዊው ዓለም ዕቃዎችን በገንዘብ ከመለዋወጥ በስተጀርባ ያለው አላማ የሰውን ልጅ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል፣አኗኗሩ ይበልጥ ምቹና የተቃና እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡የሰዎች ፍላጎት ይህ ካልሆነ፣ለምንድ ነው ግለሰቦች ራሳቸው ጥረው ግረው ከማግኘት ይልቅ የገበያ ልውውጥን የሚመርጡት ብለን ልንጠይቅ ይገባል።ከመርፌና ከክር አንስተን እስከ ማቀዝቀዣና ባለቀለም ቴሌቪዥን ያሉትን ቁሶች ሁሉ የምናገኘው በልውውጥ አማካይነት ነው፡፡በገበያ አማካይነት መለዋወጥ ባይኖር ኖሮ እያንዳንዱ ሰው ወደገጠር ወጥቶ ለቀለቡ እህልና ለልብሱ ጥጥ ማምረት ይገደድ ነበር። ቤቱንም ለመገንባት ሸክላዎችን ከአፈር መስራትና ለህልውናው አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ከመሬት ውስጥ ማውጣት ግዴታው በሆነ ነበር።

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.