ነፃ ገበያ

MRነፃ ገበያ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚካሄዱ የተለያዩ የንግድ ልውውጦች ድምር ውጤት መገለጫ ሀሳብ ነዉ፡፡ነፃ ገበያ  በሁለት ገበያተኛ ሰዎችወይም ህጋዊ ውክልና በተሰጣቸውሁለት አካላትመሀከል በፍቃደኝነት ላይ ተመስርቶ የሚካሄድ የንግድ ልውውጥ እና ግብይት ሂደት ማለት ነዉ፡፡ በፍቃደኝነት የሚደረገው ግብይት ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባላቸው እና ለገበያ በቀረቡሸቀጦች ወይም አገልግሎቶች ላይ ሊሆን ይችላል።

ለምሳሌ ያህል እኔ ከአንድ የጋዜጣ አዟሪ ላይ  ጋዜጣ በ10 ብር ስገዛ ሁለት ነገሮች ለግብይት እንደቀረቡ ማየት እንችላለን። ይህም እኔ ለጋዜጣ አዟሪው የምሰጠው 10 ብርእና እሱ ለኔ የሚሰጠኝ ጋዜጣ ነው።አንድ ምሳሌ ልጨምር። የሆነ ድርጅትዉስጥ ተቀጥሬብሰራ ልክ እንደ ጋዜጣው ሁሉ በእኔ እና በቀጣሪዬ መካከል የሁለትዮሽ ልውውጥ ይካሄዳል። ይህም የሚሆነው እኔ ጉልበቴን እና ችሎታየንበአገልግሎት መልክ የምሰጠው ቀጣሪ ድርጅት እሱ ደግሞ በልዋጩ በደመወዝመልክ ገንዘብስለሚሰጠኝ ነው። ታዲያ በጋዜጣውም ሆነ በጉልበት ልውውጡ ወቅት የሁለቱም ወገን ስምምነት እና ፈቃደኝነት ወሳኝ ነዉ፡፡

የስራ ቅጥሩ የሚካሄደው ድርጅቱን እንዲያስተዳድሩ በተወከሉ የስራ ሃላፊዎች በኩል በመሆኑ እና የቅጥር ውሉ የሚፈረመው ከሚቀጥሩት ሰው የሚጠብቁት የስራ ችሎታ ስላለ እና ተቀጣሪውም ለዛ ችሎታው በልዋጩ ገንዘብ ለመቀበል ሲስማማ ነው።  ሁለቱም ወገኖች በስራ ሂደት ላይ የሚፈልጉትን እና የሚጠብቁትን ጥቅም ካላገኙእንደሁኔታዉ የስራ ውሉ ሊቋረጥ የሚችልበት እድል አለ፡፡ስምምነቱ የሚጸናው ሁለቱም ተጠቃሚ እስከሆኑ ድረስ ብቻ ሲሆን ከሁለቱአንዱ ይጠቅመኛል ብሎ ካላሰበ ልውውጡን የመተውመብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ገበያ እና ግብይት በዘመነ መርካንቲሊስ

ይህ ቀላል የነፃ ግብይት ፅንሰ ሀሳብ በአውሮፓ ከ16ኛውእስከ 18ኛውክፍለ ዘመን በተለምዶ በMercantilist Period  የነበረውን መሰረታዊ የነፃ ገበያ ፅንሰ ሀሳብ እና በፈረንሳዊው ጸሃፊ ሞንታጋቢን በ16ኛዉ ምእተ አመት የቀረበዉን አስተሳሰብ ለማፍረስ በቂ ሆኖ ተገኝቷል፡፡እንደ ሞንታጋቢን እና መርካንቲሊስቶች አመለካከት በማንኛዉም ንግድ አንዱ በሌላዉ መጠቀም አለበት ወይም አንዱ ሌላውን እስካልጎዳ ድረስ መጠቀም አይችሉም፡፡እሱ መጠቀም ካለበት ሌላዉ መጎዳት አለበት እናም በእያንዳንዱ ግብይት አሸናፊ እና ተሸናፊ ወይም በዝባዥና ተበዝባዥ ይኖራል፡፡

በዘመናዊዉ የገበያ አስተሳሰብ የንግድ ልውውጥ ሁለቱም ወገኖች ተጠቃሚ የሚሆኑበት እንጅ የዜሮ ድምር፤የፖሰቲቭ(አንዱ ይበልጥ የሚጠቀምበት)ወይም የኔጋቲቭ( አንዱ ወገን የሚጎዳበት)ድምር ጨዋታ አይደለም፡፡ታዲያ ሁለቱ ወገኖች እንዴት እኩል ተጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ? እያንዳንዳቸውለግብይት የቀረቡትን ሁለት እቃዎች ወይም አገልግሎቶች በተለያየ መንገድ ዋጋቸውን ሊመዝኑ ይችላሉ፡፡ይህ የዋጋ ምዛኔ ልዩነት የልውውጡን መልክ ይወስነዋል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ልውውጡ የሚፈጸመው በገዥ እና በሻጭ መካከል በሚፈጠር እና ሁለቱም ይበልጥ ዋጋ የሰጡትን ነገር ለማግኘት በሚፈጥሩት ስምምነትይሆናል ማለት ነው።

አቅርቦት፣ፍላጎት እና ዋጋ

ለምሳሌ እኔ ገንዘብ ይዤጋዜጣ ለመግዛት ስፈልግ ጋዜጣ የሚባል መንገድ ላይ ላይኖር ይችላል። በአንፃሩ የጋዜጣ አዟሪው በርካታ የሚሸጡ ጋዜጦች ኖሮት ቶሎ ገንዘብ ለማግኘት ገዥን በጉጉት ይጠባበቃል፡፡እናም ሁለታችን ስንገናኝ በአንድ ጊዜግብይት ለመፈፀም ቁርጥ ዉሳኔ ላይ እንደርሳለን፡፡ እነዚ ሁለት ነገሮች ማለትም የገዥ ፍላጎት እና የሻጭ ጉጉት ማንኛውንም የንግድ ልውውጥ ስምምነት   ይወሰወናሉ፡፡እያንዳንዱ ወገን ለልውውጥ የቀረቡትን ሸቀጦች የሚመዝንበት መንገድ እና የሁለቱ ወገኖች የመደራደር ክህሎት ምን ያህል ብር አንድን ጋዜጣ ለመለወጥ ወይም ለመግዛትበቂ ነውየሚለውበጋዜጣ ገበያውላይ ተዋናይ በሆኑት ተገበያዮች ሁኔታ የሚወሰን ነዉ፡፡ይህም ማለት ጋዜጣውን የሚገዛው ሰው ከሌሎች እቃዎች አንፃር ግምት ውስጥ አስገብቶ ዋጋቸውን እንዴት ይመዝናቸዋል የሚለውጉዳይ ወሳኝ ነዉ፡፡ ይህ ደግሞ ዋጋ/price/ወደሚባለው የግብይትነጥብ ይወስደናል፡፡ዋጋየሚወሰነውበጋዜጣ አቅርቦት እና ጋዜጣውን ለመግዛት አቅምም ፍላጎቱም ኑሯቸውእቃውን ከሌላ እቃ አንፃር አስተያይተውዋጋውን ለመመዘን ክህሎት ባላቸዉ የገበያ ተዋንያን ነዉ፡፡በአጭሩ አቅርቦት/supply/ እና ፍላጎት /demand/በምንላቸዉ ሁለት ሀይሎች የሚወሰን ነዉ፡፡

የእቃዉ አቅርቦት እንዳለ ሆኖ ስለ እቃውየሚሰነዘሩ በጎ አስተያየቶች /ማስታወቂያ እና የንግድ ማብራሪያ/የቀረበዉን ነገር ጥቅም በሸማች ዋጋ ስለሚያቀርበዉ የሰውየመግዛት ፍላጎት ይጨምራል፡፡ይህን ተከትሎም ዋጋውከፍ ይላል። በተቃራኒ ለሽያጭ በቀረበዉ ዋጋ ላይ የሚሰነዘሩ አሉታዊ አሰተያየቶች ለእቃዉ ተፈላጊነት መውረድ እና ለዋጋውማሽቆልቆል ምክንያት ይሆናሉ፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ የአቅርቦት ማነስ እና መብዛት ለአንድ እቃ ዋጋ መውረድ ወይምመውጣት እንደ ዋና መሰረታዊ ምክንያት ሊጠቀሱ ይችላሉ።

የገንዘብ አፈጣጠር እና ዘመናዊ የገበያ ስርዓት

እናም ግብይት ስንል ዝም ብሎ ልውውጥ አይደለም።እጅግ የተወሳሰበ የተለያዩ ነገሮችን የያዘሂደት ነዉ፡፡በጥንታዊውማህበረሰብ ግብይት ማለት የአይነት ለዉጥ ማለት ነዉ፡፡ ለምሳሌ በቆሎን በማሽላ መለወጥ ማለት ነው። ምናልባት የበቆሎ ዋጋ ከማሽላ ከበለጠ 3 ኪሎ በቆሎን በ5 ኪሎ ማሽላ መለዋወጥ ማለት ነው። ሆኖም በዚህም ጊዜ የሁለቱም ወገኖች ፍላጎት እና ጉጉት የልውውጡን ሂደት ይወስናል። ይህ እቃን በእቃ የመቀያየር(BARTER) ልማድ የማህበረሰብንንቃትእና የግብይት ፅንሰ ሀሳብ እድገት ተከትሎ መቅረት ሲጀምር ሁለት ጥቅም ያላቸውን እቃዎች ወክሎ በግብይት መሳሪያነት የሚያገለግል እና የልውውጥ መሳሪያ የሚሆን ዋጋ ያለዉ ነገር ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆነ።ይህም ገንዘብ/money commodity/የምንለውን ነገር ፈጠረ።ለዚህ ደግሞ በተለምዶ ወርቅ እና ነሀስ ተመራጭ ሆኑ።ከገንዘብ መፈጠርጋር ተያይዞም  አሁን የምናየውዘመናዊ የንግድ ልውውጥ እና የገበያ ስርዓት እውን ሆነ።

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.