ለሰባት አስርት ዓመታት የዘለቀ የአና ፍራንክ ምትሃት

አና ፍራንክ (Anne Frank)

አና ፍራንክ (Anne Frank)

በየትኛውም ቅጽበት ከተደበቁበት ሊገኙ እንደሚችሉ፣ በኃይል ተጎትተው  በአቅራቢያው ወደሚገኝ የማጎሪያ ካምፕ እንደሚወሰዱ ከዚያም እንደሚገደሉ ልብዎ እያወቀ በአንድ  ሕንፃ መደበቂያ ተገን ውስጥ ለሁለት ዓመታት ያህል እያንዳንዷን ቀን መኖርን እስቲ ያስቡ? የሃያኛው ክፍለዘመን እጅግ ዝነኛ ደራሲ ተብላ መጠራት የቻለችው የ15 ዓመትዋ አና ፍራንክ ግለ-ማስታወሻዋን የጻፈችው ከላይ በተጠቀሰው ሁኔታ ውስጥ ሆና ነው። ጀርመን ኔዘርላንድን በወረራ በያዘችበት ወቅት ከናዚዎች ተሸሽጋ ሳለች  በጻፈችው ማስታወሻዋ “እያንዳንዱ ሰው ዓለምን የተሻለች ለማድረግ ከመንደርደሩ በፊት ለአንዲት ቅጽበት እንኳ መዘግየት ባያስፈልገው ምንኛ መልካም ነበር፡፡” ብላላች። በወርሃ ሐምሌ እኤአ 1944ዓ/ም እርሷ እና ቤተሰቦችዎ ከተሸሸጉበት ስፍራ ከመገኘታቸው በፊት በአስራዎቹ የእድሜ ክልል የምትገኘው አና የግል ማስታወሻዋን ጨምሮ ሌሎች በርካታ አነቃቂ የሆኑ ድንቅ ጽሁፎች መጻፍ ችላለች፡፡ አና የአስራ ስድስትኛ ዓመት የልደት በዓሏን ለማክበር ሶስት ወር ያህል ጊዜ ሲቀራት ከነቤተሰቦችዋ በተወረወረችበት የበርግን ቤልሰን ካምፕ ውስጥ በመጋቢት ወር እኤአ1945ዓ/ም ሕይወትዋን አጣች፡፡

በሰቆቃ እና በሽብር መካከል እንደዚያ ያለ እጅግ የላቀ ተስፋ እና የቀናነት መንፈስ በራስ ውስጥ ማለምለም እንዲሁም ጨለማ በዋጣት ዓለም ላይ ሁኖ ታላቅ ብርሃንን አሻግሮ ማየት ላንዲት ታዳጊ ወጣት እንደምን ይቻል ይሆን? ይህ በርግጥም ለሰባት አስርት ዓመታት የዘለቀ የአና ፍራንክ ምትሃት ነው፡፡

የአና ፍራንክ መልዕክት ይበልጥ ለቀጣዩቹ በርካታ አስርት ዓመታቶች ብቻ ሳይሆን እስከ ምንጊዜውም ሲታውስ ሊኖር እንደሚችል ይታሰባል፡፡ ይህ የሚነግረን  በምንም አይነት ሁኔታዎች ውስጥ ሳይቀር ልዩነት መፍጠር የምንችል መሆናችንን ነው፡፡ አመለካከታችን በራሱ የምግባራችን ተግባር መገለጫ ሆኖ ደረጃችንን ይወስናል፡፡ የተሻለች ዓለም መፍጠር ከፈለጉ ራስዎን የተሻለ በማድረግ ይጀምሩ። ይህ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ በዋነኝነት ሊመሩበት የሚገባ አንድ የስኬታማ ህይወት መንገድ ነው፡፡

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.