ስራ ፈጠራ እና ሀብት ፈጠራ

(በዲት አንድ የመንግሰት አስተዳደር ምን ያህል ስኬት እንዳስመዘገበ ለማወቅ ምን ያህል የስራ እድል እንደፈጠረ በማየት መገመት ይቻላል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የመንግስት ህግጋት ወይም ፖሊሲዎች በብዛት የሚገመገሙት ምን ያህል ስራ እድል የመፍጠር ችሎታ አላቸው ከሚል አኳያ ነው፡፡ ምን ጊዜም ቢሆን አንድ የመንግስት አስተዳደር ስራ ፈጠራ ላይ ያልተመሰረተ ወይም ትኩረት ያላደረገ ፖሊስ ይዞ ውጤታማ መሆን አይችልም፡፡ እንዲያውም አንዳንዴ መንግስታት በአስቸጋሪ ወቅት እንኳ ሳይቀር ጦርነትን ከነአስከፊ ገፅታው እንደ ሁነኛ የስራ ምንጭ የሚያዩት፡፡

መንግስታት ስራ ለመፍጠር በተለይም የሀገር ውስጥ ስራ ፈጠራን ለማበረታታት በሚል ከውጭ ገበያ የሚገቡ ሸቀጦች ላይ ገደብ ያደርጋሉ። ተጨማሪ ግብር ይጥላሉ። እንዲሁም ቁጥጥር ያደርጋሉ። ሆኖም ማንኛውም ሃገር ከውጭ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን የሚስገባው ሃገሩ ውስጥ አምርቶ ከመጠቀም ቀላል ሆኖ ስለሚያገኘው ነው፡፡ቁምነገሩ እና እዚህ ልናሰምርበት የሚገባን ነገር ስራ ፈጠራ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ግብ የሆነውን ሀብት ፈጠራ የምንደርስበት መንገድ መሆኑን ነው፡፡በአሁኑ ጊዜ ‘ስራ ፈጠራ’ ስህተት ነው ብለን የምንወስድበት ምንም መንገድ የለም፡፡ ነገር ግን በሰዎች ዘንድ ያለው አመለካከት በቀላሉ ሀብትን መፍጠር እና ማከማቸት እንጂ ስራን መስራት ትክክለኛው የፈለግንበት ወይም ያቀድነው ቦታ መድረሻ ተደርጎ አይወሰድም፡፡ ስራ መፍጠር እና መስራት ወደ ትክክለኛው  የሃብት መንገድ መድረሻ መሆኑን መርሳት በብዙ ሰዎች ላይ የሚንፀባረቅ የመከራከሪያ ነጥብ ነው።እነዚህ የተሳሳቱ ሀሳቦች በራሳቸው ወደ ሀብት የምናደርገውን እንቅስቃሴ ከመጨመር ይልቅ የሚያቀጭጩ እና የሚያጠፉ ሆነው ይታያሉ፡፡ ቁምነገሩ እና እዚህ ልናሰምርበት የሚገባን ነገር ስራ ፈጠራ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ግብ የሆነውን ሀብት ፈጠራ የምንደርስበት መንገድ መሆኑን ነው፡፡ምንም እንኳ ቀላል መስለው ቢታዩም በዚህ ፅሁፍ ላይም አንዳንድ የስራ ፈጠራ ሃሳቦቻችንን ሊገድቡብን የሚችሉ ምሳሌዎችን ጠቃቅሻለሁ፡፡

1- ስራ ፈጠራ ቀላል ግሮች የሌሉት አድርጎ መገመት

የማንኛውም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አላማ የተቻለውን ያህል እሴት ባሉት ውስን ግብአቶች የሰው ሃይልን ጨምሮ ማምረት ወይንም መፍጠር  መቻል ነው፡፡ የግብአት እጥረት ወይንም አነስተኛ ሆኖ መገኘት ሁልጊዜም ቢሆን ማድረግ የምንፈልጋቸውን ወይንም የምንመኛቸውን ነገሮች በፈለግናቸው መጠን ከማግኘት ይከለክለናል፡፡ የኢኮኖሚ ሳይንስ መነሻ መሰረትም ይኽው ከሰው ልጅ ፍላጎት ጋር ተመጣጣኝ ያልሆነ ውስን ሃብት ነው። ማንኛውም ሃገር ከህዝቡ ፍላጎት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ሃብት የለውም። ስለዚህ የሌለውን ለማግኘት ካለው ላይ መግዛት እንዲሁም ያለውን ለሌሎች መሸጥ እና ሃብቱንም ለብክነት እንዳይዳረግ ተንከባክቦ መያዝ ይኖርበታል።

የስራ ፈጠራ ሃሳብም በጣም ውስን እና ወሳኝ የሆነውን ሃብት ማለትም የሰው ሃይልን ወደ ኢኮኖሚው ውስጥ በማስገባት አምራች እንዲሆን ማድረግ ቢሆንም ብዙ ጊዜ በብዙዎች ቀለል ተደርጎ ይታያል፡፡ ቢሆንም የሰው ሃብትን ወደ ኢኮኖሚው ማስገባት በራሱ ሌሎች በርካታ ውስን ሃብቶችን በተገቢው እና በተቀናጀ መንገድ ተግባር ላይ ማዋል ይጠይቃል። የስራ ፈጠራን ቀለል አድርገው የሚያዩ ሰዎች ‘ቀድሞ ከተፈጠረ ስራ ይልቅ ሁልጊዜም ቢሆን አዲስ እና ልዩ የሆነ ስኬታማ ስራ መፍጠር ይቻላል።’ የሚል ተስፋ ተሞልተው መሆኑ የታወቀ ነው። በርግጥም እውነት ነው‘ ቀድሞ ከተፈጠረ ስራ ይልቅ ሁልጊዜም ቢሆን አዲስ እና ልዩ የሆነ ስኬታማ ስራ መፍጠር ይቻላል። ሆኖም ግን ችግሩ ያለው ሰዎች የትኛው ስራ ጥሩ ጥቅም ወይም ብዙ ውጤት ሊያስገኝልኝ ይችላል የሚለውን ውሳኔ በቀላሉ መወሰን አለመቻላቸው ላይ ነው፡፡  ስራ ፈጠራ ሌሎች ውስን የሆኑ ሃብቶቻችንን በአግባቡ እና ውጤት ሊያስገኝልን በሚችል መልኩ ከመጠቀም ጋር እንደሚያያዝም መዘንጋት የለብንም።  ሆኖም ብዙ ጊዜ መንግስታት ዜጎች ወደ እንዲሰማሩ ብቻ በማሰብ የሃገርን ኢኮኖሚ ሊጎዳ የሚችል ዘለቄታ የሌለው ውሳኔ ይወስናሉ።

ይህን ሃሳብ ለማጠናከር አንድ ኢንጂነር ቻይና ሄዶ ያጋጠመውን አጋጣሚ መጥቀስ ይቻላል፡፡ይህ ኢንጂነር በቻይና ብዙ ሰራተኞች በባህላዊ መሳሪያ ማለትም አካፋና ዶማን በመጠቀም ግድብ ሲሰራ ይመለከታል:: ኢንጂነሩም ይህን በተመለከተበት ጊዜ ስራውን ይቆጣጠር ለነበረው ተቆጣጣሪ ይህን ግድብ ለመስራት የግድ የኮንስትራክሽን መኪና እንደሚያስፈልግና ስራውንም ሊያቃልል እንደሚችል ይነግረዋል:: የሥራው ተቆጣጣሪ በምላሹ ‘አንተ ያልከውን ዘመናዊ ማሽነሪዎች ከተጠቀምን የብዙ ሠራተኞቻችንን የስራ እድል ይዘጋብናል’ ይለዋል:: ኢንጂነሩም ‘አሃ! እኔ እኮ ያሰብኩት ግድብ የመስራት ፍላጎት አላችሁ ብዬ ነው፡፡ፍላጎታችሁ ብዙ የስራ እድል መፍጠር ከሆነ ለምን ሠራኞቹ አካፋና ዶማውን ጥለው በማንኪያና በሹካ እንዲጠቀሙ አታደርጉም’ ብሎ መለሰለት፡፡

ተጨማሪ ምሳሌ ለማንሳት ያህል ይችን ልጨምር።በአንድ ወቅት በጆርጂያ ዩኒቨርሲቲ ለሚገኙ ተማሪዎቼ ‘በዚህ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች  የሚስማሙ ከሆነ ሁሉንም በወር አንድ ዶላር እቀጥራቸዋለሁ፡፡’ አልኳቸው። ‘ከአንድ ዶላር ባነሰ ዋጋ የሚስማሙ ከሆነ ደግሞ የጆርጂያን ግዛት ህዝብ በሙሉ ልቀጥራቸው እንደምችል ነገርኳቸው።’  ለተማሪዎቼ ይህን ያልኩበት ምክንያት የስራ እድል ፈጠራ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በደንብ እንዲረዱ ካለኝ ምኞት አንፃር ነው፡፡ ይህን ሁሉ ህዝብ በርካሽ ዋጋ ወደ ስራ ባሰማራም ውጤታማ ስራ ይሰራሉ ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ውጤታማ ስራ ካልሰሩ ደግሞ በርካሽ ዋጋ በቀጠርኳቸው ሰዎች ያለኝ ውስን ሃብት እየባከነ ነው ማለት ነው። ሰራተኞቹ ውጤት ያለው ስራ ካልሰሩ እኔ ለነሱ ደመወዝ ከመክፈል ባለፈ ተጨማሪ ገቢ አላገኝም ማለት ነው። ይህ ደግሞ ዘላቂ ሆኖ አይቀጥልም።ምክንያቱም የኔ ሃብት ውስን እና አላቂ በመሆኑ ነው። እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን የትኛውም የኢኮኖሚ እድገት እና ውጤት የተመሰረተው በርካሽ ዋጋ በሚሰሩ ብዙ ሰራተኛች ሳይሆን በትንሽ ምርታማ እና ለስራቸው የሚመጥን ክፍያ የሚከፈላቸው ሰራተኞች በሚያስመዘግቡት ውጤት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

 2-የትኩረት አቅጣችንን ብዙ ስራ እድሎችመፍጥር ላይ ተኮር

እኤአ በ1840ዎቹ ፈረንሳይ ውስጥ የነበሩ ፖለቲከኞች ለዜጎቻቸው የስራ እድልን ለመፍጠር የተጠቀሙበት አንዱ መንገድ በፈረንሳይ ቡርድዩዥ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን እና ፈረንሳይ እና ስፔንን የሚያገናኛውን የባቡር መንገድ ሆን ብሎ ማበላሸት ነበር። የባቡር መስመሩ ላይ እክል በመፈጠሩ ምክንያት ቀደም ሲል በአንድ ቀን ጉዞ ይገባባቸው የነበሩ አካባቢዎች ጭምር  መንገድ ላይ ሳያድሩ መግባት ቀረ። በዚህ ምክንያት ተሳፋሪ መንገደኞች ለተጨማሪ የመኝታ አገልግሎት ክፍያ እና የምግብ ወጭዎች ተዳረጉ። አላማውም መንገደኞችን ለወጭ በመዳረግ ተጨማሪ የስራ እድል እና ገቢን መፍጠር  ነበር፡፡ ምንም እንኳን ይህን አስተሳሰብ  በ19ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩ ኢኮኖሚስቶች እና መንግስታት ቢያስቀሩትም ቀደም ብለን ከላይ ስራ ለመፈጠር  በሚል ምክንያት አዳዲስ እና የተሸሻሉ መሳሪያዎችን ከመጠቀም የታቀቡት ቻይናውያን ጋር ግን የሚነፃፀር ነው፡፡

 

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.