1645 የፕላኔታችን ቢሊየነሮች

channel_8_panel59_0_bigsquare-1393858531አሜሪካ በፕላኔታችን ላይ ብዙ ኢንተርፕርነሮች ያሉባት ሃገር በመሆኗ ከሁሉም የበለጠ ሃበታም ሃገር መሆን ችላለች። የፎርብስን  (Forbes) የ2014 ዓ/ም የቢሊየነሮችን ዝርዝር በምናይበት ወቅት የምናገኘው ይህንኑ ሃቅ ነው። ፎርብስ የሃብታሞችን የገንዘብ መጠን እና ደረጃ ላለፉት 28 ዓመታት ሲያወጣ የቆየ ሲሆን ዘንድሮም በፕላኔታችን መሬት ላይ የሚገኙ 1645 ቢሊየነሮችን ስም፣ የሃብት መጠን፣ እና ደረጃ ዘርዝሮ አውጥቷል። የእነዚህ 1645 ቢሊየነሮች ሃብት ጠቅላላ ድምር ስድስት ትሪሊዮን አራት መቶ ቢሊዮን(6.4 ትሪሊዮን) የአሜሪካ ዶላር ነው። ይህ አሃዝ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር በአንድ ትሪሊዮን ዶላር ይበልጣል። ፎርብስ 42 ሴቶችን ጨምሮ ዘንድሮ 268 አዳዲስ ቢሊየነሮችን ያካተተ ዝርዝር ያወጣ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ማለትም በኡጋንዳ እና በታንዛኒያ  ሁለት ቢሊየነሮችን ማገኘቱን ስማቸውን እና የሃብት መጠናቸውንም በማውጣት አሳይቷል።

ከ1 እስከ 5ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት የምድራችን ቱጃሮች

#1 ቢል ጌት

#1 ቢል ጌት

ላለፉት አራት ዓመታት በሃብት መጠኑ ከዓለም ሁለተኛ ሆኖ የቆየው የማይክሮ ሶፍት ኩባንያ መስራች ቢል ጌት ከዚያ በፊት ለ15ዓመታት ይዞት ወደ ነበረው የአንደኝነት ደረጃው በመመለስ በ76 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የፕላኔታችን አንደኛ ሃብታም ሰው ሆኗል። ሜክሲኰዊው ካርሎስ ሄሉ በበኩሉ የዛሬ አራት አመት ከቢል ጌት የወሰደውን የአንደኝነት ደረጃ መልሶ በራሱ በቢል ጌት ተነጥቆ በ72 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ስፔናዊው አማንሲዮ ኦርቴጋ በ64 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር፣ አሜሪካዊው ዋረን ቡፌት በ58.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር፣የORACLE መስራች አሜሪካዊው ላሪ አሊሰን በ48 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር፣አሜሪካዊያኑ ወንድማማቾች ቻርለስ እና ዴቪድ ኮች እያንዳንዳቸው በ40 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በተከታታይ ከሶስተኛ እስከ ስድስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

#2 ካርሎስ ሄሉ

#2 ካርሎስ ሄሉ

#3 አማንሲዮ ኦርቴጋ

#3 አማንሲዮ ኦርቴጋ

#4 ዋረን ቡፌት

#4 ዋረን ቡፌት

 

#5 ላሪ አሊሰን

#5 ላሪ አሊሰን

 

 አሊኮ ዳንጎቴ

አሊኮ ዳንጎቴ

የአፍሪካ ሃብታሞች

ፎርብስ ከዘረዘራቸው 1645 ቢሊየነሮች መካከል 29 ያህሉ አፍሪካዊያን ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ ገብጽ ውስጥ  8፣በደቡብ አፍሪካ ውስጥ 8፣ በናይጀሪያ 4 እንዲሁም በሞሮኮ 4 ቢሊየነሮች መኖራቸው የተካተተ ሲሆን በስዋዚላንድ፣በአልጀሪያ፣በአንጎላ፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ የሚገኙ ቱጃር ቢሊየነሮች በዝርዝሩ ተካተዋል።

ፎርብስ ከአፍሪካ እና ከጠቅላላው ጥቁር ህዝብ ውስጥ በሃብት መጠኑ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት አድርጎ ያስቀመጠው ናይጀሪያዊውን አሊኮ ዳንጎቴ ነው። የአሊኮ ዳንጎቴ የሃብት መጠን 25 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን የሃብቱ ምንጭም የስኳር፣ዱቄት እና ስሚንቶ ምርት እንደሆነ በዘገባው ተካቷል።  ከአፍሪካ እና ከጠቅላላው ጥቁር ህዝብ ውስጥ በሃብት ደረጃቸው ሁለተኛ የሆኑት በኢትዮጵያ የተወለዱት የሳውዲ አረቢያ ዜግነት ያላቸው ሼህ መሃመድ አላሙዲ ሲሆኑ  ያላቸው ሃብትም አስራ አምስት ቢሊዮን ሶስት መቶ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ነው። የሃብት ምንጫቸው ሜድሮክ ኢትዮጵያ፣ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ(70% ያህል ድርሻ አላቸው)፣ እንዲሁም በስዊድን እና በሞሮኮ ያሏቸው ድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያዎች (Refineries) ናቸው።ፎርብስ ሼህ መሃመድ አላሙዲንን በዓለም ላይ ከሚገኙ 1645 ቢሊየነሮች መካከል የ61ኛ ደረጃን ሰጥቷቸዋል። ፎርብስ ለመጀመሪያ ጊዜ በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ሁለት ቢሊየነሮችን ያገኘ ሲሆን ስም እነሱም ሱድሂር ሩፓሬሊዖ የተባለ ኡጋንዳዊ እና  ታንዛኒያዊው ሮስታም አዚዚ ናቸው። ኡጋንዳዊው ሱድሂር  የሃብት መጠኑ አንድ ቢሊዮን አንድ መቶ ሚሊዮን(1.1ቢሊዮን) የአሜሪካ ዶላር ነው። የሃብት ምንጩም የባንክ ቢዝነስ እና ሪል ስቴት እንደሆን የታወቀ ሲሆን ይህ ሰው ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ሃብታም ሆኖ ተመዝግቧል። ታንዛኒያዊው ሮስታም አዚዚ በአንድ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የምስራቅ አፍሪካ ቁጥር ሁለት ቱጃር ለመሆን በቅቷል። የሃብት ምንጩም የቴሌኮም ቢዝነስ እና ማዕድን መሆኑ ታውቋል።

ሴት ቢሊየነሮች

ፎርብስ ከዘረዘራቸው 1645 ቢሊየነሮች መካከል 172ቱ ሴቶች ሲሆኑ ያላቸው ሃብት ጠቅላላ ድምርም 510ቢሊዮን ዶላር ወይም ከኖርዌይ ኢኮኖሚ አመታዊ ጠቅላላ ምርት(GDP) ጋር ይስተካከላል።

ወጣት ቢሊየነሮች

ማርክ ዙከርበርግ

ማርክ ዙከርበርግ

ላሪ ፔጅ

ላሪ ፔጅ

ሰርጌ ብሪን

ሰርጌ ብሪን

በ13 ቢሊዮን ሶስት መቶ ሚሊዮን (13.3ቢሊዮን) የአሜሪካ ዶላር በማስመዝገብ የፌስቡክ መስራች የሆነው የ29ዓመቱ ማርክ ዙከርበርግ ከወጣት ቢሊየነሮች ውስጥ የአንደኛ ደረጃን ሲይዝ የ39ዓመት እድሜ ያላቸው ጓደኛሞቹ የጎግል መስራቾች ላሪ ፔጅ በ23 ቢሊዮን ዶላር ሁለተኛ እንዲሁም ሰርጌ ብሪን በ22.8ቢሊዮን ዶላር ሶስተኛ ሆኗል።

የከሰሩ ቢሊየነሮች

ሮበርት ፍሪድላንድ

ሮበርት ፍሪድላንድ

ኢኬ ባቲስታ

ኢኬ ባቲስታ

ኦላቭ ትሮን

ኦላቭ ትሮን

ቪክቶር ኑሴንኪስ

ቪክቶር ኑሴንኪስ

ማኖጅ ባርጋቫ

ማኖጅ ባርጋቫ

ፎርብስ መቶ ያህል ቢሊየነሮች አምና ይዘውት ከነበሩበት ደረጃ መውረዳቸውን የገለጸ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 16ቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ከቢሊየነርነት ደረጃ ዝቅ ካሉት መካከል ብራዚላዊው ኢኬ ባቲስታ ሃብቱ ከ10.6 ቢሊዮን ዶላር

ግርሃም ዌስተን

ግርሃም ዌስተን

ወደ 300 ሚሊዮን ዶላር ያሽቆለቆለ ሲሆን በተመሳሳይም ኖርዌያዊው ኦላቭ ትሮን ከ6 ቢሊዮን ዶላር ወደ 250ሚሊዮን ዶላር፣ ሩሲያዊው ቪክቶር ኑሴንኪስ ከ 2.2 ቢሊዮን ዶላር ወደ 350ሚሊዮን ዶላር፣አሜሪካዊው ሮበርት ፍሪድላንድ ከ1.8ቢሊዮን ዶላር  ወደ 950 ሚሊዮን ዶላር ፣አሜሪካዊው ማኖጅ ባርጋቫ ከ1.5 ቢሊዮን ዶላር ወደ 800ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ሌላው አሜሪካዊ ግርሃም ዌስተን ከ1.25 ቢሊዮን ዶላር ወደ 650ሚሊዮን ዶላር መውረዳቸው ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፎርብስ ከዘረዘራቸው 1645 ቢሊየነሮች ውስጥ 492ቱ አሜሪካዊያን ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ የ400ው አሜሪካዊያን ቢሊየነሮች ጠቅላላ ሃብት ድምር ሁለት ትሪሊዮን ዶላር ወይም የሩሲያ ኢኮኖሚ በዓመት የሚያመርተውን ጠቅላላ ምርት(GDP) ያክላል። ፎርብስ በዝርዝሩ 152 የሩሲያ ቢሊየነሮችን እና 111 የቻይና አቻዎቻቸውን በማስፈር በቢሊየነሮች ብዛት ከአሜሪካ ቀጥለው በተከታታይ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ለመያዝ በቅተዋል።

በመጨረሻም ፎርብስ የንጉሳዊያን ቤተሰቦችን ሃብት እና ስልጣናቸውን ተገን በማድረግ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ያከማቹ አምባገነኖችን ስም ዝርዝር በሪፖርቱ አለማካተቱን ገልጿል። በዚህ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት ሃብታቸውን በስራ እና በጥረት ያከማቹ ሰዎች እንደሆኑም ፎርብስ አስታውቋል።

ምንጭ:- ፎርብስ [http://www.forbes.com/billionaires]

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.