የጎግል የስራ ቅጥር መመዘኛ-ምሁራዊ ትህትና እና ምግባር!

በቅርቡ ከኒውዮርክ ታይምሱ ቶም ፍሪድማን ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የጎግል የሰው ሃይል አስተዳደር ሃላፊ ድርጅታቸው ዝነኛ ከሆኑ ትላላቅ ዩኒቨርስቲወች የሚመረቁ ተማሪዎችን ብዙ ጊዜ ለመቅጠር እንደሚቸገር ገልጸዋል። “ከዚህ በተጨማሪ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የሚመረቁ ተማሪዎችም የጎግልን የስራ ቅጥር መመዘኛ ብዙ ጊዜ አያሟሉም” ያሉት ላዝሎ ቦክ “ለጎግል ትልቁ የቅጥር መስፈርት የተቀጣሪው አይምሮ (IQ)ትልቅ መሆን ወይም ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው  የሚያስመዘግቡት ትልቅ ውጤት(GPA) ሳይሆን ምሁራዊ ትህትናን የተላበስ እና ምግባር ያለው ሰው ሆኖ መገኘት” እንደሆን ተናግረዋል።  ምሁራዊ ትህትና እና ምግባር ያላቸው ሰዎች በስራ ላይ ከባልደረቦቻቸው ወይም ከስህተታቸው ለመማር ተነሳሽት እንዳላቸውም አስረድተዋል። ይህን ተነሳሽነት ደግሞ በከፍተኛ ውጤት ከዩኒቨርስቲ የተመረቁ ተማሪዎች ላይ እና የ IQ መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑት ጋር ለዓመታት ባካሄዱት ቅጥር እና ክትትል ማግኘት እንዳልቻሉ ገልጸዋል።

“እነዚህ ሰዎች ሁልጊዜ ከሁሉም እንበልጣለን የሚሉ ‘ጂኒየስ’ ነን ባዮች ስለሆኑ ከሌላው ጋር ተግባብተው እንደማይሰሩ እና ከስህተታቸውም ለመማር  ጨርሶ ፍላጎቱ የላቸውም::” ያሉት ሃላፊው  “ከነዚህ ሰዎች ጋር ለዓመታት ባሳለፍንበት ወቅት የተማርነው ነገር ቢኖር በትምህርት ዓለም ስኬታማ ሆኖ ማለፍ በስራ ላይም ተመሳሳይ ውጤት ይገኛል ማለት እንዳልሆነ ነው።” በማለት አባባላቸውን አጠናክረዋል።

ጎግል በስራ ላይ ሳሉ ከሚሳሳቱት ስህተት እንዲሁም ከባልደረቦቻቸው ጭምር ሁልጊዜ ለመማር ዝግጁ የሆኑ እና የዩኒቨርስቲ ወይም የኮሌጅ ምሩቃን ባይሆኑም ስለሚሰሩት ስራ ምንነት እስካወቁ እና ችሎታው እስካላቸው ድርስ ሰዎችን እንደሚቀጥር ያብራሩት የሰው ሃይል አስተዳደር ሃላፊው ላዝሎ ቦክ “ሁልጊዜ እንደነዚህ አይነት ሰዎችን ለማግኘት ከባድ ቢሆንም ለሁሉም ዓይነት የስራ መስክ በአንደኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጥነውን መስፈርት ማለትም  ‘ምሁራዊ ትህትናን መላበስ እና ምግባር ያለው መሆን’  የሚለውን ስለሚያሟሉ የሚቻለንን ሁሉ እናደርጋለን::” ብለዋል።

እጅግ በጣም ስኬታማ የምግባር ሰው  የሆነው ዋረን ቡፌት በበኩሉ ከስራ ቀጣሪዎች መመዘኛ አኳያ  የሚከተሉትን ሶስት ነጥቦች ያስቀምጣል፡፡ እነርሱም ምግባር ፣ የላቀ ችሎታ እና የመስራት ተነሳሽነት ናቸው፡፡ ከነዚህ ከሶስቱ እጅግ ወሳኝ የሆነው እና ለሰራተኛው(ለተቀጣሪው) ምሉዕነትን የሚያጎናጽፈው ምግባር መሆኑንም አስምሮበታል። ዋረን ቡፌት ለዚህ እንደምክንያት ያቀረበው “ሠራተኞች(ተቀጣሪዎች) ምግባር የሌላቸው ከሆነ ፣ የተቀሩት ሁለት መመዘኛዎች ማለትም የላቀ ችሎታ እና የመስራት ተነሳሽነት የቀጣሪውን ድርጅት ህልውና ሊፈታተኑ ወይም ሊያከስሩ ይችላሉ፡፡” የሚል ነው። ዋረን ቡፌት ባለው የሃብት ክምችት ከዓለም በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ግማሽ ያህል ሃብቱን ማለትም ሰላሳ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያህል ‘ቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን’ ለሚባል አንድ በጎ አድራጎት ድርጅት የለገሰ ድንቅ ሰው ነው።

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነንን የእንግሊዝኛ ሊንክ እዚህ ያገኙታል።

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.