ፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች እና የዩክሬናዊያኑ ዚቅ

መሄጃ  ያጡት ፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች

መሄጃ ያጡት ፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች

‘ፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች አፍቃሬ አውሮፓ ዩክሬናዊያን ተቃዋሚዎቻቸውን እስከመቼ ይገዳደሩ ይሆን?’ የሚለው የዘወትር ጥያቄያችን ዛሬ መልስ አግኝቷል። ፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች ትናንት አርብ በአውሮፓ ህብረት ሸምጋይነት አመፁን ያስቆማል የተባለ ስምምነት ከተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጋር ቢፈራረሙም ‘ሁለቱንም ወገኖች አናምናቸው’ ባሉት አፍቃሬ አውሮፓ ዩክሬናዊያን ሰልፈኞች በቀጠለው አመጽ ምክንያት ፕሬዝዳንቱ ድምጻቸውን ሳያሰሙ ቤተመንግስቱን እና ዋና ከተማዋን ጥለው እንዲሄዱ አስገድዷቸዋል። እጅግ በጣም ፈታኝ ሆኖ ላለፉት ሶስት ወራት ሲካሄድ የከረመው  ህዝባዊ አመጽም በዩክሬናዊያን ድል አድራጊነት ተጠናቋል።

የዩክሬን የትናንት እና የዛሬ ውሎ እንኳን ለውጭ ተመልካች ይቅርና ለዩክሬን ባለስልጣናት እና በፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች ፓርቲ አባላት ለተሞላው ፓርላማ ሳይቀር ሳይቀር ዚቅ ሳይሆንባቸው አይቀርም። የዩክሬን ፓርላማ ትናንት የቀድሞዋን ጠቅላይ ሚንስተር ከእስር ለመፍታት ያስችላል የተባለ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ማሻሻያ አዋጅ በከፍተኛ ድምፅ ህግ ሆኖ እንዲወጣ አሳልፏል። ሆኖም ይህ አዲስ አዋጅ ተግባራዊ የሚሆነው በፓርላማው አፈ ጉባዔ እና በፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች ተፈርሞበት በበሃገሪቱ የነጋሪት ጋዜጣ (Holos Ukrainy) ታትሞ ከወጣ በኋላ ነበር።

ዚቅ 1:ፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች በቦታቸው የሉም።  ነጋሪት ጋዜጣውም አልታተመም።

የቀድሞዋ የዩክሬን ጠቅላይ ሚንስተር ወ/ሮ ዩሊያ ቲሞሽንኮ

የቀድሞዋ የዩክሬን ጠቅላይ ሚንስተር ወ/ሮ ዩሊያ ቲሞሽንኮ

ዚቅ 2: የቀድሞዋ የዩክሬን ጠቅላይ ሚንስተር ወ/ሮ ዩሊያ ቲሞሽንኮ ከሁለት ዓመታት በላይ በእስር ሲማቅቁበት ከነበረው ወህኒ ዛሬ ተለቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሯ ስልጣንን ያላግባብ ተጠቅመዋል የሚል የውሸት ክስ አሁን በተባረሩት ፕሬዝዳንት ተቀነባብሮባቸው ሰባት አመት በወህኒ ቤት እንዲቆዩ ተፈርደባቸው ነበር።  ዛሬ ከእስር ቤት የተለቀቁት ወይዘሮ ‘በዩክሬን አምባገነንነት ተገረሰሰ’ ብለዋል። ወ/ሮ ዩሊያ ቲሞሽንኮ በ2010 በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተባራሪው ፕሬዝዳንት ዋነኛ ተፎካካሪ የነበሩ አፈቃሬ ምእራባዊያን ፖለቲከኛ ናቸው።

ዚቅ 3: የዩክሬን ፓርላማ ትናንት በራሳቸው ጊዜ እግሬ አውጭኝ ያሉትን ፕሬዝዳንት ዛሬ ቅዳሜ ተሰብስቦ ከስልጣን ማባረሩን ማስታወቁ ሌላው ዚቅ ነው። በተያያዘም ፓርላማው የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትሩን ከስልጣን አባሯል።

ዚቅ 4: ህዝቡ ላለፉት ሶስት ወራት እጅግ በጣም ፈታኝ በሆነ ቅዝቃዜ እና በረዶ ሳይቀር ሲፋለማቸው የቆየውን ፕሬዝዳንት ፓርላማው ዛሬ አበረርኩላችሁ ማለቱ ደግሞ አራተኛው ዚቅ ነው።

ዚቅ 5: የተባረሩት ፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች አመሻሹን ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ‘ስልጣን አለቀኩም። ህዝብ የመረጠኝ ህጋዊ የዩክሬን ፕሬዝዳንት እኔ ነኝ ።የዩክሬንን ሰላም ወደቀድሞው ለመመለስ የሚቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ::’ ብለዋል። ባሁኑ ሰዓት ያኑኮቪች የት እንዳሉ በግልጽ የሚታወቅ ነገር የለም። ሆኖም ትናንት ወደ ሰሜን ምስራቅ ዩክሬን ሩሲያ ድንበር አቅራቢያ ወደምትገኘው ካሃርኪቭ ከተማ እንደሄዱ ቢነገርም በዚያ በጠበቃቸው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ድግስ ተደናግጠው ወደ ሩሲያ ለመግባት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆኑ ተሰምቷል። ሲንፈላሰሱበት የከረመው ቤተ መንግስት ግን ላለፉት ሶሶት ወራት ከስልጣን እንዲወርዱ ሲለምኗቸው፣ሲወተውቷቸው፣ ሲደሙ እና ሲቆስሉ በከረሙት ዩክሬናዊያን ክፍት ሆኖ እየተጎበኘ ነው።

የሌኒን ሃውልት ከመፍረሱ በፊት

የሌኒን ሃውልት ከመፍረሱ በፊት

በሌኒን ሃውልት የተተካው ወርቃማ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ

በሌኒን ሃውልት የተተካው ወርቃማ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች  ላይ በአውሮፓ ህብረት አሸማጋይነት ከተደረሰው ስምምነት ውጭ መፈንቅለ መንግስት ተካሄዶባቸዋል ያሉ ሲሆን ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሰርጌይ ላቭሮቭ በበኩላቸው የተቃዋሚዎቹ ወደ ስልጣን መምጣት የራሽያን ሉአላዊነት አደጋ ላይ ይጥላል ብለዋል።  ሩሲያ ከተባራሪው ፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች ጋር ያላትን የጠበቀ ወዳኝነት በመቃወም ዩክሬናዊያን ሰልፈኞች በዋና ከተማ ኬቭ የሚገኘውን የቀድሞውን የሶቬት ህብረት አምባገነን መሪ ቭላድሚር ሌኒን ሃውልት በታህሳስ ወር ማፍረሳቸው ይታወሳል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ዜና ዛሬ ቅዳሜ ዩክሬናዊያን ተማሪዎች በፈረሰው የ ሌኒን ሃውልት ቦታ ላይ በወርቅ አምሳያ የተሰራ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ አስቀምጠውበታል። ተማሪዎቹ ይህን ያደረጉት በሃገሪቱ የተንሰራፋውን ሙስና ለመቃወም ሲሆን ከስልጣን የወረዱትም ፕሬዝዳንት መጸዳጃ ቤት መቀመጫ ወርቅ እንደሆነ እና የተሰራውም ከህዝብ በተዘረፈ ገንዘብ እንደሆን ለማሳየት እንደሆን ተናግዋል።

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.