ኤድዋርድ ስኖውደን የግላስጎ ዩኒቨርስቲ ሬክተር ሆኖ ተመረጠ

ኤድዋርድ ስኖውደን

ኤድዋርድ ስኖውደን

የአሜሪካን መንግስት መጠነ ሰፊ የስልክ ጠለፋ እና የኢንተርኔት ክትትል ያጋለጠው ኤድዋርድ ስኖውደን በስኮትላንድ የግላስጎ ዩኒቨርስቲ ሬክተር ወይም የዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ጉዳይ ሃላፊ  ሆኖ መመረጡን Dailyrecord ዘግቧል።

የ30 ዓመቱ ኤድዋርድ ስኖውደን  ቀደም ሲል የአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ኤጀንሲ የኮንትራት ሰራተኛ እና የአሜሪካ የስለላ ድርጅት (CIA) ተቀጣሪ እንደነበር ይታወቃል። ሰኞ ዕለት በግላስጎ ዩኒቨርስቲ በተደረገው ምርጫ ያሸነፈው ኤድዋርድ ስኖውደን በአሁን ሰዓት ጊዜያዊ ጥገኝት ባገኘባት ሩሲያ ውስጥ ይገኛል።

የዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ጉዳይ ሃላፊ (ሬክተር) ሆኖ ለመመረጥ በተደረገው ምርጫ  ኤድዋርድ ስኖውደንን ጨምሮ  እንግሊዛዊው የቀድሞ ሳይክል ውድድር ሻምፒዮና ግራሜ ኦብሬ፣ ደራሲ አላን ቢሴት፣ እና አባ ኬቪን ሆስዎርዝ  ተወዳዳሪዎች ነበሩ። ተሸናፊዎቹ ተወዳዳሪዎች  ‘ኤድዋርድ ስኖውደን በአካል መገኘት ስለማይችል ችግራችሁን በቅርብ ሆነን የምንከታተለውን እኛን ምረጡ’ በማለት በየፊናቸው ሲቀሰቅሱ ቢሰነብቱም የተማሪዎቹን ይሁንታ እና ድምጽ ግን ማግኘት ሳይችሉ ቀርተዋል።

በግላስጎ  ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ዲግሪውን የሚያጠና ክሪስ ካሴልስ የተባለ ተማሪ ‘ኤድዋርድ ስኖውደንን እጩ አድርገን ወደ ውድድሩ ያስገባነው መንግስታት በየቦታው የሚያደርጉትን ኢሰብዓዊነት የተላበሰ እና ሞራላዊነት የጎደለው’ ያለውን ‘የስልክ ጠለፋ እና የኢንተርኔት ስለላ እንደምንቃወም ግልጽ ለማድረግ እና እንዲህ ያለውን አስነዋሪ ድርጊት ከሚያጋልጡ ሰዎች ጎን መቆማችንን ለማረጋገጥ ነው’ ብሏል። የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች  ስኖውደንን ለእጩነት ያቀረቡት ፍቃደኝነቱን በጠበቃው በኩል ካረጋገጡ በኋላ እንደሆንም ተናግሯል- ክሪስ ካሴልስ።

የግላስጎ  ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ካሁን በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በቦታው ተገኝተው መስራት የማይችሉትን ዊኒ ማንዴላን እኤአ በ1987 ዓ/ም እንዲሁም እስራኤላዊውን የስኖውደን አቻ ሞርዴቻይ ቫኑኑ እኤአ በ2005 ዓ/ም ሬክተር  አድርገው እንደመረጧቸው ይታወሳል።

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.