ሶሻሊስታዊው የፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ መንግስት እና ቬንዙዌላዊያን ተፋጠዋል!

ሚስ ቱሪዝም ቬንዙዌላ በጥይት ከተመታች በኋላ በሞተር ሳይክል ወደ ሆስፒታል ስትወሰድ

ሚስ ቱሪዝም ቬንዙዌላ በጥይት ከተመታች በኋላ በሞተር ሳይክል ወደ ሆስፒታል ስትወሰድ

ሁጎ ቻቬዝን ወደ ስልጣን ካመጣው እና በ1989ዓ/ም ከተካሄደው ‘የካራካሱ አመጽ’ ወዲህ ቬንዙዌላ እንዳሁኑ  ሶሻሊስታዊውን የቬንዙዌላ ስርዓት  አጣብቂኝ ውስጥ የከተተ ትዕይንተ ህዝብ አይታ አታውቅም።  ቬንዙዌላዊያን ተማሪዎች እና ወጣቶች ህዝባዊ አመጹን የለኮሱት መንግስት ‘የቬንዙዌላዊያንን ወጣቶች ቀን እናክብር’ ብሎ ሰልፍ ካስወጣቸው በኋላ ነበር። ፈጽሞ ያልተጠበቀ ክስተት የሆነበት ሶሻሊስታዊው የቬንዙዌላ መንግስት የሚይዝ የሚጨብጠውን አጥቷል። አንዴ ‘ኒዎ ሊበራሎች’ ናቸው ሌላ ጊዜ ደግም ‘ፋሽቶች’ እንዲያም ሲል CIA እና አሜሪካ ላይ ጣቱን ከመቀሰር አልፎ ሶስት የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን ከሃገር እስከማባረር ደርሷል። አመጹ ግን ከዕለት ወደ ዕለት አድማሱን እያሰፋ ቬንዙዌላን እየናጣት ይገኛል።

1Xm9u44በሃገሪቱ ምዕራብ አንዲያን  የታችራ እና መሪዳ ግዛቶች ውስጥ አመጹ ስር የሰደደ ሲሆን ነዋሪዎች አካባቢውን ‘የጦርነት ቀጠና’ እያሉ መጥራት ጀምረዋል። ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ የአመጹ መስፋፋት ያሰጋቸው ሲሆን ‘በተለይ በተለይ’ አሉ ‘ለታችራ ልዩ ሃይል ተዘጋጅቶላታል።ታችራ እንደ ሊብያዋ ቤንጋዚ እንድትሆን ፈጽሞ አንፈቅድላትም!’በማለት ለምእራባዊቷ ቬንዙዌላ ግዛት ታችራ የደገሱላትን ሳያቅማሙ አሳውቀዋል።

የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ሁጎ ቻቬዝ ሞት ተከትሎ ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ የቬንዙዌላን ችግር ከመፍታት ይልቅ እንዳባባሱት የሚናገሩት ሰልፈኞች በሃገሪቱ ለሰፈነው ወንጀለኛነት፣ስራ አጥነት፣ከፍተኛ የኑሮ ውድነት፣እና ከፍተኛ የሆነ የመሰረታዊ እቃዎች እና የምግብ ፍጆታዎች እጥረት ሁሉ ተጠያቂ ያደርጓቸዋል።

በሚያዚያ ወር 2013ዓ/ም ወደ ስልጣን ከመጡ ጀምሮ የሃገሪቱ የዋጋ ንረት 56 በመቶ እስኪደርስ ድረስ ‘የሰዎችን ሃብት በመውረስ እና ሃብታም ያሏቸውን ሰዎች ንብረት በመቀማት ተጠምደው ምንም ያደረጉት ነገር የለም’ በማለትም ይከሷቸዋል። እስካሁን ድረስ ቬንዙዌላ ውስጥ 357,000 ሽሕ የንግድ እና የቢዝነስ ተቋማት ስራቸውን ለማቆም የተገደዱ ሲሆን በዚህ ምክንያት  አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሽሕ(1,7oo,000) የሃገሪቱ ዜጎች ስራ አጥ ሆነዋል።ከዚህ በተጨማሪም ሶሻሊስታዊው መንግስት መቶ ሃምሳ ሽሕ(150000) የንግድ እና የቢዝነስ ተቋማትን ወርሷል። ሰውዬው ስልጣን በያዙበት ወቅት አንድ የአሜሪካን ዶላር በ8 የቬንዙዌላ ብር(ቦሊቫር ፉርቴ) ሲመነዘር የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን አንድ የአሜሪካን ዶላር በ87 የቬንዙዌላ ብር ነው የሚመነዘረው።ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ለዚህም ዋና ተጠያቂ የሚያደርጉት ‘የቬንዙዌላዊያን ጠላት’ የሚሏትን አሜሪካ ነው። [ቬንዙዌላ ከደቡብ አሜሪካ ሃገራት በነዳጅ ሃብቷ አንደኛ ስትሆን በዋናነት ነዳጇን የምትገዛት ደግሞ አሜሪካ መሆኗ ይታወቃል።]  ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ወቅት ስኳር፣ጨው፣ቅቤ፣የልጆች ወተት፣ የዳቦ ዱቄት ወዘተ ቬንዙዌላ ውስጥ ለማግኘት መሞከር በቁም የመቃዠት ያህል ይቆጠራል።

STANDARD AND POOR የሚባለው በኒውዮርክ ወልስትሪት የሚገኝ ግዙፍ ባንክ የቬንዙዌላን የመንግስት ቦንድ ‘ዋጋ የማያወጣ’ በማለት ደረጃውን ዝቅ አድርጎታል። በፕላኔታችን እጅግ በጣም አደገኛ ‘የወንበዴዎች ዋሻ’ ከሚባሉ አገሮች ውስጥ ቬንዙዌላ አንዷ ስትሆን በ21 ደቂቃው አንድ ሰው ይገደልባታል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ብቻ ሃያ አራት ሽህ ሰባት መቶ(24,700) ሰዎች ቬንዙዌላ ውስጥ በወንበዴዎች ተገድለዋል።

_73102571_31d32db1-aa48-4e65-9879-9ca24840e64eየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ሜክሲኮ ውስጥ በሰጡት መግለጫ ‘መንግስት ሊዖፖልዶ ሎፔዝን ጨምሮ ያሰራቸውን ተቃዋሚዎች እንዲፈታ እንዲሁም ትኩረቱ የህዝቡን ጥያቄ መመለስ’ ላይ እንዲያደርግ አሳስበዋል።  የዋናው ተቃዋሚ ጥምረት መሪ የሆኑት ሊዖፖልዶ ሎፔዝ በፖሊስ የተያዙት በቬንዙዌላ ዋና ከተማ ካራካስ ውስጥ ይመሩት ከነበረው  የሰላማዊ ተቃውሞ ሰልፍ መሃል ነው። በአሁኑ ወቅት የ42 ዓመቱ የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ምሩቅ በዋና ከተማዋ ካራካስ ‘ራሞ ቬርዴ’ ተብሎ በሚጠራው እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ። የሊዖፖልዶ ሎፔዝ ባለቤት ወ/ሮ ሊሊያን ቲንቶሪ በበኩላቸው ለህዝቡ ‘ለውጥ በእያንዳንዳችን እጅ ይገኛል። ተስፋ እንዳትቆርጡ!’ የሚል መልክት በትዊተር ገጻቸው ላይ አስተላልፈዋል።

የካቲት 12 ቀን 2006ዓ/ም እሮብ እለት በፔሩ ዋና ከተማ ሊማ፣በስፔን ማድሪድ፣በሆንዱራስ እና በጓቲማላ ቬንዙዌላዊያን ያገር ቤቱን ህዝባዊ አመጽ በመደገፍ ሰልፍ ወጥተዋል። እስካሁን በቬንዙዌላ ከስድስት የሚበልጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች የተገደሉ ሲሆን ከመሃከላቸውም የ22ዓመቷ የኮሌጅ ተማሪ እና ሚስ ቱሪዝም ቬንዙዌላ ወ/ት ጀነሲስ ካርሞና ትገኝበታለች። ሚስ ቱሪዝም የተገደለችው በማዕከላዊ ቫሌንሽያ ጭንቅላቷ ላይ በሶሻሊስታዊው ልዩ ዘብ አልሞ ተኳሾች በጥይት ተመታ ነው። ቬንዙዌላዊያን መሞታቸው  እና የተቃዉሞ ሰልፉም ቅርጹን ወደ አብዮትነት እየቀየረ መስተጋባቱን ቀጥሏል።

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.