የዩክሬን የዛሬ ውሎ እና የኦሎምፒክ ጨዋታ

የነጻነት አደባባይ (ኬቭ-ዩክሬን)

የነጻነት አደባባይ (ኬቭ-ዩክሬን)

ዩክሬን ዛሬም በደም ስትጨቀይ ውላለች። ተቃዋሚዎች በተሰበሰቡበት ‘የነጻነት አደባባይ’ ላይ የፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች ወታደሮች በጫሩት እሳት ከመቶ የሚበልጡ ሰዎች ተገድለዋል። ከአምስት መቶ በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።   በነጻነት አደባባዩ አጠገብ የሚገኝ አንድ ትልቅ ሆቴል ውስጥ ጭንቅላታቸው ላይ በጥይት ተመተው የሞቱ  ሰልፈኞት እና ህክምና የሚደረግላቸው በርካታ ቁስለኞች  ታይተዋል።

ፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች  ‘ለዛሬው ትርምስ፣የሰው ህይወት መጥፋት እና የንብረት መውደም ተጠያቂዎቹ ሰልፈኞቹ ናቸው’ ብለዋል። እስካሁን ድረስ 25 ፖሊሶች እንደቆሰሉበት ያስታወቀው መንግስት 67 ፖሊሶች ደግሞ በሰልፈኛው ታግተውብኛል ብሏል።

ሆኖም ግን ‘ታግተዋል’ ከተባሉት የተወሰኑት ፖሊሶች መካከል አንዳንዶቹ በዩክሬን ብሃራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ የተቃውሞውን ጎራ ወደው ተቀላቅለው እንጅ ታግተው እንዳልሆነ ተናግረዋል።

KV (1)

የዩክሬንን 43 ያህል አትሌቶች እየመሩ ኦሎምፒክ ወደሚካሄድባት የሩሲያዋ ሶች ከተማ ያቀኑት የሃገሪቱ ብሄራዊ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ሰርጌ ቡብካ በእናት ሃገር ዩክሬን ስላለው ሁኔታ ሁለቱም ወገኖች በሰከነ መንፈስ በመነጋገር መፍትሄ እንዲፈጥሩ ተማጽነዋል።  የዩክሬን አትሌቶችም ከኦሎምፒክ ውድድሩ እና ጨዋታው ይልቅ የሃገር ቤቱ ጉዳይ ይበልጥ እንዳሳሰባቸው ከCNN ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።  እንደውም አንዳንዶቹ አትሌቶች የኦሎምፒክ ውድድሩን አቋርጠው ወደ ዩክሬን ተመልሰዋል።

ይህን አስመልክቶ ቦግዳና ማሶትስካ የተባለች የዩክሬን አትሌት ‘ያገሬ ልጆች እየተገደሉ እዚህ ለውድድር የምቆይበት ምንም ሞራል የለኝም’ በማለት ከውድድሩ ራሷን በማግለል ወደ ሃገሯ ለመመለስ መዘጋጀቷን አስታውቃለች።

የዋና ከተማዋ ኬቭ ከንቲባ ‘ከዛሬ ጀምሮ የገዥው ፓርቲ አባል አይደለሁም’ በማለት በከተማዋ አስተዳደር ድረ-ገጽ ላይ ራሳቸውን ከገዥው ፓርቲ  ማግለላቸውን በጽሁፍ አስታውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውሮፓ ህብረት የዩክሬን ባለስልጣናት በአውሮፓ ያከማቹትን ገንዘብ እንዳያንቀሳቅሱ የሚያደርግ እና ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ የሚከለክል የቪዛ እና የጉዞ ማዕቀብ ለመጣል በቤልጀም ብራሰልስ እየመከረ ነው። አሜሪካ በበኩሏ ተመሳሳይ እቀባ ለመጣል ጥድፊያ ላይ መሆኗን ኋይት ሃውስ አስታውቋል።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በተባበሩት መንግስታት የሩሲያ አምባሳደር ሚ/ር ቫይታል ቹርኪን አማካኝነት ዩክሬናዊያኑን ለመሸምገል ሃሳብ ቢያቀርቡም ተቃዋሚዎቹ ‘ከእንግዲህ መንግስት ጋር ድርድር አይኖርም’ በማለታቸው ጥረታቸው ሳይሳካ ቀርቷል።

ትናንት ወደዋና ከተማዋ ሲያቀኑ መንገድ ላይ የታገቱት የምእራብ ዩክሬን ነዋሪዎችም ለቪቭ በምትባለው  ከተማ ውስጥ የመንግስት ህንጻወችን በእሳት ሲያያይዙ ውለዋል።

ፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች አፍቃሬ አውሮፓ ዩክሬናዊያን ተቃዋሚዎቻቸውን እስከመቼ ይገዳደሩ ይሆን?

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.