የኢኮኖሚ ነጻነት ምድር-ሆንግኮንግ!

ሆንግኮንግ

ሆንግኮንግ

የ2013ዓ/ም የዓለም የኢኮኖሚ ነጻነት ሪፖርት እንደሚያሳየው ሆንግኮንግ በሪፖርቱ  ከተካተቱት 152 ሃገራት አንደኛ ስትሆን ሲንጋፖር ደግሞ ሁለተኛ ለመሆን በቅታለች። ሆንግኮንግን አንደኛ ያሰኟት መስፈርቶች ነጻነትን ለሚወዱ የሰው ልጆች ሁሉ እንደ ምርጥ ሙዚቃ ይደጋገማል። በዚሁ ሪፖርት አሜሪካ 17ኛ፣ቻይና 123ኛ ደረጃን ሲይዙ ምስራቅ አፍሪካዊያኑ ሃገራት ኡጋንዳ 64ኛ፣ኬንያ 87ኛ እንዲሁም የእኛዋ ኢትዮጵያ 142ኛ ደረጃን ይዘዋል።

ሆንግኮንግ ከሌሎቹ ሃገራት ሁሉ በኢኮኖሚ ነጻነቷ በልጣ የተገኘችው:-

1ኛ: በአንጻራዊነት ምንም ሙስና የሌለባት ምድር መሆኗ፣

2ኛ: ብቃት ያለው እና ገለልተኛ የፍትህ ሥርዓት ስላላት፣

3ኛ: ለግለሰቦች ሃብት እና ጥረት ህጋዊ ከለላ የምትሰጥ የሕግ የበላይነት የሰፈነባት ምድር መሆኗ፣

4ኛ:  ያልተወሳሰበ፣ግልጽ፣ እና አነስተኛ የግብር ስርዓት ተግባራዊ ማድረጓ፣

5ኛ፡ በሆንግኮንግ ውስጥ የሽያጭ ታክስ(ግብር) እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከነጭራሹ አለመኖሩ፣

6ኛ: የሆንግኮንግ ዜጎች ከቋሚ ንብረታቸው ላይ ከሚያገኙት ጥቅም ምንም አይነት ግብር አለመክፈላቸው(ለምሳሌ ቤት ሲሸጡም ሆነ ሲያከራዩ ለመንግስት የሚከፍሉት ግብር የለም) እና በውርስ ከሚገኝ ሃብት ላይም ምንም አይነት ግብር  አለመከፈሉ፣

7ኛ: በአንጻራዊነት ሆንግኮንግ ምንም አይነት የውጭ ሃገር እዳ ወይም ብድር የሌለባት ሃገር በመሆኗ  እና

8ኛ: በሆንግኮንግ የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ወደሃገር ቤት የሚገቡም ሆነ ከሃገር የሚወጡ ሸቀጦች እና ሌሎች እቃዎች ላይ በአንጻራዊነት ቀረጥ የሚባል ነገር ባለመኖሩ ነው።

ይህ ደግሞ የሆንግኮንግን ህዝብ እጅግ በጣም ሃብታም ያደረገው ሲሆን በዓለም ላይ ዜጎቻቸው የተሻለ ገቢ ያገኛሉ ከሚባሉ ሃገራት  የሆንግኮንግ ሰዎች ገቢ በአማካይ 264% ይበልጣል። ሆንግኮንግ የቻይና ኮሚንዝም ሥርዓት የማይተገበርባት የቻይና ራስ ገዝ ናት። ሰባት ሚሊዮን ያህል ሰዎች ሆንግኮንግ ውስጥ ይኖራሉ። የእነዚህ ሰዎች አማካይ የመኖሪያ እድሜ ከ80ዓመት የሚበልጥ ሲሆን ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢያቸውም ሰላሳ ሽሕ የአሜሪካን ዶላር ወይም ስድስት መቶ ሽሕ የኢትዮጵያ ብር ገደማ ነው። በኮሚኒስት ስርዓት ስር የሚገኙት አንድ ቢሊዮን ሶስት መቶ  ሚሊዮን ያህል ቻይናዊያን ያህል ቻይናዊያን ግን  ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢያቸው ሶስት ሽሕ የአሜሪካን ዶላር ወይም ስልሳ ሽሕ የኢትዮጵያ ብር ገደማ ነው።

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.