የቬንዙዌላዊያን ትዕይንተ ህዝብ አሁን ያለበት ሁኔታ

ሊዖፖልዶ ሎፔዝ በፖሊስ ሲያዙ

ሊዖፖልዶ ሎፔዝ በፖሊስ ሲያዙ

ሶሻሊስታዊው የቬንዙዌላ መንግስት የህዝቡን ዓመፅ ተከትሎ በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ገብተውብኛል ያላቸውን ሶስት የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን ከሃገሩ ያባረረ ቢሆንም የህዝቡ ተቃውሞ ግን ተጋግሞ ቀጥሏል። አሜሪካ የቬንዙዌላ መንግስት ውሳኔን በማጣጣል ‘የሚሰራውን የማያውቅ’ ብለዋለች። ከዚህ በተጨማሪም በፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ የሚመራው የቬንዙዌላ  ሶሻሊስታዊ መንግስት የዴሞክራሲ ታጋዩን እና የተቃዋሚዎች ህብረት መሪ ሊዖፖልዶ ሎፔዝን ቀደም ሲል እንደዛተው አስሯቸዋል። ሊዖፖልዶ ሎፔዝ በፖሊስ የተያዙት በቬንዙዌላ ዋና ከተማ ካራካስ ውስጥ ይመሩት ከነበረው  ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ መሃል ነው።

የተቃዋሚውን መሪ መንግስት ‘በሽብርተኛነት እና በነፍሰ ገዳይነት’ እንደሚፋረዳቸው ያስታወቀ ቢሆንም በዚህ ኢ ዴሞክራሲያዊ አድራጎቱ የተቆጡ የምእራባዊያን ሃገራት በመንግስት ላይ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እየፈጠሩበት ይገኛሉ።

የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ‘ሂዩማን ራይትስ ፋውንዴሽን’(HRF) ዳይሬክተር ሚስተር ጋሪ ጋስፓሮቭ የቬንዙዌላን መንግስት በማውገዝ የዴሞክራሲ ታጋዩን ሊዖፖልዶ ሎፔዝ በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈታ ጠይቀዋል። መንግስት ያቀረበባቸውን ክስም ‘በዴሞክራሲ እና በመላው ዓለም በሚገኙ የዴሞክራሲ ታጋዮች ላይ የተቃጣ በትር’ ከማለታቸው በተጨማሪ  የክሱ ዋና ዓላማም ህዝቡን ማስፈራራት እንደሆን  ገልጠዋል።

በአሁኑ ወቅት መሰረታዊ የምግብ ፍጆታዎች ማለትም ስኳር፣ጨው፣ቅቤ፣የልጆች ወተት፣ ዱቄት ወዘተ በቬንዙዌላ  ምድር አይገኙም። ልብ በሉ፡ ቬንዙዌላ ከደቡብ አሜሪካ ሃገራት በነዳጅ ሃብት አንደኛ ናት። ነዳጇን በዋናነት የምትገዛት አሜሪካ ናት። ሆኖም በቬንዙዌላ ሶሻሊስታዊ መንግስት ብልሹ ስርዓት ምክንያት ህዝቡ ለማመጽ ተገዷል። መልካም አስተዳደር ለአንድ ሃገር የሚያስገኘው ጥቅም በተፈጥሮ ሃብት ከሚገኝ ጥቅም ይበልጣል።

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.