ፌስቡክ እና ፊታውራሪዎቹ አስር የአፍሪካ ሃገራት

fb (1)በአፍሪካ ውስጥ ሃምሳ ሚሊዮን ያህል ፌስቡክ ተጠቃሚዎች አሉ። የሰሜን አፍሪካዊቷ ግብጽ ዜጎች ፌስቡክ በመጠቀም ከአፍሪካ የሚወዳደራቸው የለም።  አስራ ሶስት ሚሊዮን አስር ሽህ አምስት መቶ ሰማኒያ (13,010,580) ያህል ግብጻውያን ፌስቡክ ይጠቀማሉ። ይህ አሃዝ በአውስትራሊያ፣ በታይዋን፣ እና በጃፓን ከሚገኙት የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ጋር በቁጥር አቻ  ያደርጋታል። ግብጽ ከዓለም በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ብዛት 20ኛ ደረጃን ይዛለች። በግብጽ ውስጥ ከአራት የሚበልጡ ትላላቅ ዓለምአቀፍ የቴሌኮም ተቋማት ይገኛሉ።

ደቡብ አፍሪካ በዘጠኝ ሚሊዮን አራት መቶ ሽሕ(9,400,000) የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ከአፍሪካ 2ኛ ስትሆን በዓለም ደግሞ የ32ኛ ደረጃን ይዛላች።ደቡብ አፍሪካዊያን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በኢኳዶር፣በሮማኒያ፣ እና በሳውዲ አረቢያ ከሚገኙ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች  ጋር በቁጥር ይስተካከላሉ።

ናይጀሪያ ከአፍሪካ በሶስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን የፌስቡክ ተጠቃሚ ዜጎቿም ቁጥር አምስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሽሕ (5,300,000) ነው። ናይጀሪያ በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ከቤልጀማዊያን ጋር የሚወዳደር ቁጥር ሲኖራት ሃገሪቱም ከዓለም የ35ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ሰላሳ ሶስት ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሞሮኮ አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሽሕ(5,200,000) ዜጎቿ  ከከሶስት በሚበልጡ የቴሌኮም ኩባንያዎች አማካኝነት የፌስቡክ ተጠቃሚ ሊሆኑ ችለዋል።  ሞሮኮ ከአፍሪካ በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር 4ኛ ናት።

ሌላዋ ሰሜን አፍሪካዊት ሃገር አልጀሪያ ስትሆን ከአፍሪካ በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ብዛት 5ኛ ደረጃን ያገኘችው ከሰላሳ ሰባት ሚሊዮን ህዝቧ ውስጥ አራት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሽሕ(4,300,000) ያህሉ ከፌስቡክ ጋር ስለሚተዋወቁ ነው።

ወደ አራተኛዋ ሰሜን አፍሪካዊት ሃገር ስንሻገር ቱኒዚያ እናገኛለን። ቱኒዚያ ካላት አስራ አንድ ሚሊዮን ህዝቧ ውስጥ ሶስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሽሕ(3,300,000)ያህሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ነው። ይህም ሃገሪቱን ከአፍሪካ በፌስቡክ ተጠቃሚ ብዛት 6ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።78 በመቶ ያህሉ የቱኒዚያ ዜጎች ማንበብ እና መጻፍ ይችላሉ።

ኬንያ በፌስቡክ ተጠቃሚ ብዛት የ7ኛ ደረጃ ተርታ ላይ ተሰልፋለች። ኬንያ ከምስራቅ አፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ ያላት ሃገር ናት። የምስራቅ አፍሪካም ትልቁ ኤርፖርት የሚገኘው በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ውስጥ ነው።  አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰድሳ ሽሕ (1,860,000) ያህል ኬንያዊያን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ናቸው።

ጋና ሃያ አራት ሚሊዮን ህዝብ አላት።ከዚህ ውስጥ አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ስድሳ አምስት ሽሕ(1,465,000) ያህሉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ናቸው።ቮዳፎን የጋናን የቴሌኮም ቢዝነስ በቀዳሚነት ይመራል።

ስምንት መቶ ዘጠና አንድ ሽሕ አንድ መቶ አርባ (891,140) ያህል የፌስቡክ ተጠቃሚ ዜጎቿ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ከአፍሪካ የ9ኛ ደረጃን ለማግኘት አስችሏታል። ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ ቲጎ የቴሌኮም ገበያውን ሲመራ ቮዳፎን በሁለተኝነት ይከተላል።

ትንሿ ምዕራባዊ አፍሪካዊት ሃገር ሴኔጋል በፌስቡክ ተጠቃሚ ዜጎቿ ብዛት ከአፍሪካ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።3.3% ያህሉ የሴኔጋል ኢኮኖሚ በኢንተርኔት ቢዝነስ ላይ የተመሰረተ ነው።ቲጎ ሴኔጋል እና ኦሬንጅ የሴኔጋል የቴሌኮም ገበያው ተወዳዳሪዎች ናቸው። ሴኔጋል ካላት አስራ ሶስት ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ  ሰባት መቶ ስድሳ ሰባት ሽሕ ስምንት መቶ ሃያ(767,820) ያህሉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ናቸው።

[ምንጭ፡ www.itnewsafrica.com ነው።]

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.