ሶሻሊዝም በቬንዙዌላ እያጣጣረ ነው!

7782_10151924480553059_1274339347_n  9504350   venezuela

የደቡብ አሜሪካዊቷ ቦሊቫሪያን ሪፐብሊክ ቬንዙዌላ ሰሞኑን በህዝብ አመጽ ተናውጣለች። ‘የድሃ መንግስት’ እየተባለ ሲንቆለጳጰስ የቆየው በፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ የሚመራው የሶሻሊስት መንግስት በነዛው ድሆች ‘በቃን! አንፈልግህም! ስልጣን ልቀቅ!’ የሚል ድንገተኛ ህዝባዊ አመጽ ጋር ተፋጧል። ባለፈው ሳምንት ሃሙስ ዕለት ሁለት ተቃዋሚ ተማሪዎች እና አንድ የመንግስት ደጋፊ በጥይት ተገድለዋል።

በሃገሪቱ በነገሰው የወንጀል ድርጊት እና በከፍተኛ ሁኔታ የተከሰተው የመሰረታዊ እቃዎች እጥረት ቁጣው የገነፈለ ህዝብ ለዚህ ሁሉ ምክንያቱ  መንግስት ነው በሚል በአስቸኳይ ስልጣን እንዲለቅ ጠይቀዋል።

የቬንዙዌላ መንግስት ምን ሲሰራ ከረመ

ሶሻሊስታዊው መንግስት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሃብት አላቸው የሚላቸውንና ነጋዴዎችን ሲያሳድድ ንብረታቸውን ሲቀማ እና ሲወርስ ነው የቆየው። ከሚነጥቀውም ላይ ‘ድሆች’ ላላቸው ዜጎች መሰረታዊ የምግብ አቅርቦት ሲያደርግ ሌሎች ወጭያቸውንም ሲደጉም ‘የድሃ መንግስት’ እየተባለ ሲንቆለጳጰስ ኖሯል። ነገር ግን ድሆቹም ሆነ መንግስት ይህ የሚሆነው የሚዘረፉ ሰዎች እስካ ሉና ንብረታቸውም እስካለቀ ድረስ ብቻ መሆኑን አላስተዋሉም ነበር። እናም ያ ቀን ደረሰ። መንግስት የሚዘርፈው ነጋዴ ወይም ሃብታም የለም። ሁሉንም ቀምቶ ድሃ የሚላቸውን ረድቷል። ስለዚህ ለእነዚያ ድሆች ከአሁን በኋላ የሚሰጠው ነገር የለም። በርግጥ የትምህርት ቤት ክፍያን እና የዩኒቨርስቲ ትምህርትን ወጭ ከፍ ለማድረግ ብዙ ጊዜ ሞክሯል። በሃገሪቱ በሁሉም አቅጣጫ የተነሳው የተማሪዎች ተቃውሞ አስፈራው እንጅ።

እስካሁን ድረስ ቬንዙዌላ ውስጥ 357,000 ሽሕ የንግድ እና የቢዝነስ ተቋማት ስራቸውን ለማቆም የተገደዱ ሲሆን በዚህ ምክንያት  አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሽሕ(1,7oo,000) የሃገሪቱ ዜጎች ስራ አጥ ሆነዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ሶሻሊስታዊው መንግስት መቶ ሃምሳ ሽሕ የንግድ እና የቢዝነስ ተቋማትን ወርሷል።

እኤአ ከ1999 እስከ 2012 ዓ/ም ባሉት አስር ዓመታት ውስጥ ብቻ የቬንዙዌላ ኢኮኖሚ የዋጋ ንረት በ500% ጨምሯል። (ይህ ማለት በ1999ዓ/ም በ100 ብር ይገዙት የነበረውን እቃ በ2012 ዓ/ም 500ብር ሆኗል ማለት ነው።)

የቬንዙዌላ መንግስት ለአመጹ የሰጠው ምላሽ

PNC

ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ

ሶሻሊስታዊው መንግስት ለአመጹ የሰጠው ምላሽ ጥይት ከዛም አልፎ የውጭ ጣልቃ ገብነት በተለይም ሲአይኤ ላይ ጣቱን የቀሰረ ሲሆን በአገር ቤት የሚቃወሙትን ተቃዋሚወችም ‘የኒዎሊበራሊስቶች ተላላኪዎች’ በማለት እንደማይምራቸው አስታውቋል። ሶስት የአሜሪካ ዲፕሎማቶችም በፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ትዕዛዝ እንዲባረሩ ተደርጓል።በተለይምበተለይም የቀድሞው እጩ ፕሬዝዳንት እና ተቃዋሚው ሊዖፖልዶ ሎፔዝ ላይ የእስር ማዘዣ ቆርጦባቸዋል።

safe_imageCADBBTF7

ሊዖፖልዶ ሎፔዝ

የእስር ማዘዣውን ተከትሎ የቬንዙዌላ ማስታወቂያ ሚኒስትር በትዊተር ገጻቸው ላይ ‘ሊዖፖልዶ ሎፔዝ ፈሪ፣ወንጀለኛ፣እና የበሰበሰ የኒዮፋሽስታዊ አስተሳሰብ አራማጅ ነው’ ብለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው ሊዖፖልዶ ሎፔዝን ‘ሽብርተኛ ፣አሻጥረኛ፣ እና ነፍሰ ገዳይ ነው።’ ከማለታቸው በተጨማሪ ከእንግዲህ  ለእሱ የሚሆን ትዕግስት የለንም ብለዋል።

ሶሻሊስታዊው መንግስት አመጹን በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ዘግቧል ባለው NTN24 የተባለ የኮሎምቢያ ቲቪ ቻናል በውስጥ ጉዳዬ በመግባት ሉዓላዊነቴን ተዳፍሯል በማለት የጣቢያው ፕሮግራሞች በቬንዙዌላ እንዳይታይ አፍኖታል። ይህም እኤአ ከ1999ዓ/ም ጀምሮ መንግስት ያፈናቸውን የህትመት እና የድረገጽ ሚዲያዎች እንዲሁም የቴሌቪዥን ቻናሎች ቁጥር 500 ያደርሰዋል።

የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ‘ሂዩማን ራይትስ ፋውንዴሽን’(HRF) ዳይሬክተር ጋሪ ጋስፓሮቭ ከ ኒውዮርክ በሰጡት አስተያየት ‘የቬንዙዌላ መንግስት ባለስልጣናት ለህዝቡ ተቃውሞ የሰጡት ምላሽ ሁኔታውን ይበልጥ ከማባባስ ውጭ  ምንም ፋይዳ የለውም’ ያሉ ሲሆን ‘መንግስት ከተቃዋሚዎች ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ የጋራ መፍትሄ እንዲዘይድ’ በማለት ምክራቸውን ለግሰዋል። ‘በተረፈ የዲሞከራሲ ታጋይ የሆኑትን ሊዖፖልዶ ሎፔዝ የለጠፈባቸው ስም ለሳቸው ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ለሚገኙ የዲሞክራሲ ታጋዮች ላይ የተቃጣ የማያዛልቅ ፌዝ’ እንደሆነ በማስረገጥ ንግግራቸውን ቋጭተዋል።

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.