(በዲት ሊ / By Dwight R.Lee) አንድ የመንግሰት አስተዳደር ምን ያህል ስኬት እንዳስመዘገበ ለማወቅ ምን ያህል የስራ እድል እንደፈጠረ በማየት መገመት ይቻላል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የመንግስት ህግጋት ወይም ፖሊሲዎች በብዛት የሚገመገሙት ምን ያህል ስራ እድል የመፍጠር ችሎታ አላቸው ከሚል አኳያ ነው፡፡ ምን ጊዜም ቢሆን አንድ የመንግስት አስተዳደር ስራ ፈጠራ ላይ ያልተመሰረተ ወይም ትኩረት ያላደረገ ነገር ወይም ፖሊስ ይዞ ውጤታማ መሆን አይችልም፡፡ ለዚህ ነው መንግስታት ሌላው ቢቀር ጦርነትን ከነአስከፊ ገፅታው ለስራ መፈጠር እንደ ወሳኝ ግብዓት የሚያዩት፡፡
መንግስታት ስራ ለመፍጠር በተለይም የሀገር ውስጥ ስራ ፈጠራን ለማበረታታት በሚል ከውጭ ገበያ የሚገቡ ሸቀጦች ላይ እቀባ መጣል ወይም ከውጭ የሚመጣው እቃ ላይ ተጨማሪ ታክስና ቁጥጥር ማከል የሚፈልጉትን እና ሊያሟሉ ያሰቡትን ምንፈልገውን የልማት እንቅስቀቃሴ ከግብ ለማድረስ ሲደክሙ ያታያሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ስራ ፈጠራ ስህተት ነው ብለን የምንወስድበት ምንም መንገድ የለም፡፡ ነገር ግን በሰዎች ዘንድ ያለው አመለካከት በቀላሉ ሀብትን መፍጠር እና ማከማቸት እንጂ ስራን መስራት ትክክለኛው የፈለግንበት ወይም ያቀድነው ቦታ መድረሻ ተደርጎ አይወሰድም፡፡ ስራ መፍጠር እና መስራት ወደ ትክክለኛው የሃብት መንገድ መድረሻ መሆኑን መርሳት በብዙ ሰዎች ላይ የሚንፀባረቅ የመከራከሪያ ነጥብ ነው፡፡ እነዚህ የተሳሳቱ ሀሳቦች በራሳቸው ወደ ሀብት የምናደርገውን እንቅስቃሴ ከመጨመር ይልቅ የሚያቀጭጩና የሚያጠፉ ናቸው፡፡ ምንም እንኳ ቀላል መስለው ቢታዩም በዚህ ፅሁፍ ላይም አንዳንድ የስራ ፈጠራ ሃሳቦቻችንን ሊገድቡብን የሚችሉ ምሳሌዎችን ጠቃቅሻለሁ፡፡
1- ስራ ፈጠራ ቀላልና ግሮች የሌሉት አድርጎ መገመት
የማንኛውም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አላማ የተቻለውን ያህል እሴት ባሉት ውስን ግብአቶች የሰው ሃልን ጨምሮ ማምረት ወይንም መፍጠር ነው፡፡ ምንም ያህል እንኳን ያለብንን ውሱን ግብአቶች ለመቅረፍ ብንሞክርም ጨርሶ ግን እክልነቱን ማጥፋት አንችልም፡፡ የግብአት እጥረት ወይንም ማነስ ሁልጊዜም ቢሆን ማድረግ የምንፈልጋቸውን ወይንም የምንመኛቸውን ነገሮች በፈለግናቨው መጠን ከማግኘት ይከለክለናል፡፡
ምን ጊዜም ቢሆን ከተስፋ ወይም ተግባር ላይ ከዋሉ ስራዎች በላይ የተለየ ተግባር ወይም ስኬት ማስመዝገብ ይቻላል፡፡ የስራ ፈጠራ ሃሳብ ቀላል ተደርጎ ይገመታል፡፡ ሆኖም ግን ሰው የትኛው ስራ የተለየ ወይም ብዙ ውጤት ሊያስገኝልኝ ይችላል ብሎ መወሰኑ ላይ ዳገት ይንበታል፡፡ይህን ሃሳብ ለማጠናከር አንድ ኢንጂነር ቻይና ሄዶ ያጋጠመውን አጋጣመሚ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይህ ኢንጂነር በቻይና ሳለ ሃገሬው በብዙ ሰራተኞች በባህላዊ መሳሪያ ማለትም አካፋና ዶማን በመጠቀም ግድብ ሲሰራ ይመለከት ነበር፡፡ ኢንጂነሩም ይህን በተመለከተበት ጊዜ ስራውን ይቆጣጠር ለነበረው ተቆጣጣሪ ይህን ግድብ ለመስራት ግድ የኮንስትራክሽን መኪና እንደሚያስፈልግና ስራውንም ሊያቃልል እንደሚችል ይነግረዋል፡፡ ነገር ግን ተቆጣጣሪው መሳሪያ ከተጠቀምን የብዙ ሠራተኞቻችን የስራ እድል ይዘጋብናል በማለት መልስ ይሰጠዋል፡፡ ኢንጂነሩም አሃ እኔ እኮ ያሰብኩት ግድብ የመስራት ፍላጎት አላችሁ ብዬ እንጅ ብዙ የስራ እድል መፍጠር አልመሰለኝም፡፡ ታዲያ ፍላጎታችሁ ብዙ የስራ እድል መፍጠር ከሆነ ሠራኞቹ አካፋና ዶማውን ጥለው ለምን ማንኪያ እና ሹካ እንዲጠቀሙ አታደርጉም ብሎ መለሰለት፡፡
በጆርጂያ ዩኒቨርሲቲ ለሚገኙ ተማሪዎቼ እንደነገርኳቸው ዩኒቨርሲቲያችን በሚገኝበት አቴንስ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን በሙሉ የሚስማሙ ከሆነ በወር አንድ ሳንቲም እቀጥራቸዋለሁ፡፡ ከዚያ ደግሞ ባነሰ ዋጋ ከቀረበልኝ እንዳለ የጆርጂያን ግዛት ህዝብ ሁሉ ልቀጥራቸው እችላለሁ፡፡ይህንን ሀሳብ ለተማሪዎቼ መግለፅ ያስፈለገኝ የስራ እድል ፈጠራን በደንብ እና በጥራት እንዲረዱት ካለኝ ምኞት አንፃር ነው፡፡የትኛውም የኢኮኖሚ እድገት እና ውጤት የተመሰረተው በርካሽ ዋጋ በሚሰሩ ብዙ ሰራተኛች ሳይሆን በትንሽ ምርታማ እና ለስራቸው የሚመጥን ክፍያ የሚከፈላቸው ሰራተኞች በሚያስመዘግቡት ውጤት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
2-የትኩረት አቅጣቻችንን ወደ ብዙ ስራ እድሎች የመፍጥር ላይ መተኮር
በ1840ዎቹ ፈረንሳይ ውስጥ የነበሩ ፖለቲከኞች ለዜጎቻቸው የስራ እድልን ለመፍጠር የተጠቀሙበት አንዱ መንገድ ከፈረንሳዩ ቡርድዩዥ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን እና ፈረንሳይንና ስፔንን የሚያገናኛውን የባቡር መንገድ የቀጥታ ጉዞ እንዲቆራረጥ በማረግ እና የባቡር መስመሩ ላይ እክል በመፍጠር ተሳፋሪዎች ለመኝታ ዓገልግሎት ክፍያ እና የምግብ ወጭዎች በመዳረግ ተጨማሪ የስራ እድልና ገቢን መፍጠር ነበር፡፡ ይህ ሀሳብ ምንም እንኳን በ19ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩ ኢኮኖሚስቶች እና መንግስት ቢያስቀሩትም ቀድሞ ብሎ ስራ ፈጠራን ቀለል አድርጎ ከመገመት አንጻር ከተመለከትንበት ሀሳብ ትንሽ ወጣ ያለና ጠንከር ያለ ነው፡፡
ከውጭ የሚገቡ አገልግሎቶችን በመገደብ የሀገር ውስጥ የስራ እድልን ማስፋፋት ይቻላል ብንል እንኳ የባቡር መንገድ በማበላሸት ተጨማሪ ገቢም ማግኘት እንደሚቻል ብንስማማ ሁሉ፡እንዴት አድርገን ነው መንገድ ሰብረንና ከውጭ የሚገቡ እቃዎች ላይ ገደብ አርገን በአገራችን ውስት እነዚን እቃዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት የምንችለው? መቼም አንድ አገር ከውጭ እቃዎችንና አገልግሎቶችን የሚስገባው አገር ውስጥ አምርቶ ከመጠቀም ቀላል ሆኖ ስለሚያገኝ ነው፡፡የውጭ ገበያን መገደብ ባቡር መንገድ ማበላሸት ፋብሪካዎችን ማቃጠል እና ውድመት ማስከተል ለስራ መፈጠር ምክንያት በሚል አዳዲስ እና የተሸሻሉ መሳሪያዎችን ከመጠቀም እንደታቀቡት ቻይናውያን ጋር የሚነፃፀር ነው፡፡ ቁምነገሩ እና እዚህ ልናሰምርበት የሚገባን ነገር ስራ ፈጠራ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ግብ የሆነውን ሀብት ፈጠራ የምንደርስበት መንገድ መሆኑን ነው፡፡