ኢንተርፕርነር-2/ Entrepreneur-2

nnnnከጦር መሳሪያ ንግድ በመቀጠል ሁለተኛ የነበረውን የአፍዝ አደንግዝ ንግድ በመግፋት ስፍራውን ያስለቀቀው ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር በተደራጁ ወንበዴዎች የሚፈጸም ወንጀል ነው፡፡አምስት ዓመት ያልሞላቸው ህጻናት ለወሲብ ባርነት ከአስር ዶላር ያነሰ ዋጋ ይቸበቸባሉ፡፡በየዓመቱ ከሁለት እስከ አራት ሚሊዮን የሚደርሱ ሴቶችና ህጻናት በእነዚህ ወንበዴዎች አማካኝነት ለሴተኛ አዳሪነት ይሸጣሉ፡፡

ከመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ካላቸው ቤተሰቦች ኒውጀርሲ ውስጥ ተወልዶ ያደገው ጃሬድ ግሪንበርግ የኮሌጅ ትምህርቱን የተከታተለው በኤር ፎርስ አካዳሚ ነው፡፡ከምረቃ በኋላም በዚህ ኮሌጅ ተቀጥሮ ለአስራ ሦስት ወራት ያህል በአየር ኃይል መኮንንት አገልግሏል፡፡በሃያ ሁለት ዓመቱ የኮሌጅ ትምህርቱን እንደጨረሰ በዚያው በተማረበት ኮሌጅ ተቀጥሮ በአየር ኃይል መኮንንት ያገለገለው ጃሬድ ከአስራ ሦስት ወራት በኋላ ሥራውን ለቆ በአንድ አማካሪ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሯል፡፡

በየጊዜው እያሻቀበ የመጣውን ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የሚሰራና ሰለባዎችን የሚረዳ ድርጅት ለማቋቋም ምክንያት የሆነው ግን በአጋጣሚ የተመለከተው በወሲብ ባርነት ላይ የሚያጠነጥን ዘጋቢ ፊልም እና በእጁ የገባው በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የተጠናቀረ አስደንጋጭ ሪፖርት ነበር፡፡

እንዲያውም ፊልሙን ከተመለከተ በኋላ ለሁለት ዓመታት ያህል በሥራ ቦታ ላይ እና በማህበራዌ ሕይዎቱ ለሚያውቃቸው ሁሉ ስለጉዳዩ አስከፊነት  ሲያስረዳ ቆይቷል፡፡በተጠራበት የኮክቴል ግብዣ ላይ ሳይቀር ለጓደኞቹ ለምንድነው በዚህ ጉዳይ ላይ አንዳች የሚያደርግ የጠፋው ፖለቲከኞቻችን ለምን ችላ አሉት ባለጸጋዎቻችንስ እንዚህን ተጎጅዎች መርዳት አይፈልጉ ይሆን እያለ ሲናገርና እራሱን ሲጠይቅ የቆየው ጃሬድ ’አንድ ዕለት ከእንቅልፌ ስነቃ ግን ሌሎች ዛሬ እንዲያደርጉት የምፈልገውን ነገር ለምንድነው እኔ እራሴ ለማድረግ የማልሞክረው ብየ በድጋሚ እራሴን ጠየኩት፡፡’ ይላል፡፡

ይህንኑ ሃሳብ በተመለከተ ከጓደኛው ጋር ለመመካከር ወደ ኒክ ዘንድ ያመራው ጃሬድ አልቀናውም፡፡ጃሬድ ግን ለኒክ ቅሬታውን ነገረው፡፡አክሎም እኔ የወሲብ ባርነትን ለመዋጋት በያዝነው ዓመት ብዙ ሚሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ እፈልጋለሁ፡፡

ጃሬድ የእርዳታ ገንዘብ ማሰባሰብ የሚያስችል በቂ ችሎታ ያልነበረው ሲሆን ከሃብታሞችና ከለጋሾች  ጋርም ምንም ዓይነት ትውውቅ አልነበረውም፡፡በዚህ ምክንያት ጃሬድ ብዙም ሳይቆይ ነበር ሃሳቡ ዕውን ሊሆን እንደማይችል የተረዳው፡፡ያም ሆኖ ግን ጉዳዩን ወደፊት ለመግፋት ጥረት ሳያደርግ የቀረበት ሁኔታ የለም፡፡በሌላ ጊዜ ከኒክ ጋር የተገናኘው ጃሬድ ለነዚህ ሙሉ ነጻነታቸውን በወንጀለኞች ላጡ ዓለም ለዘነጋቻቸው ወጣት ሴቶችና ህጻናት በጋር መስራት እንደሚችሉ ሲገልጽለት የተሰማው ደስታው ወደር አልነበረውም፡፡

‘በእርግጥ ይህን አስቸጋሪ ነገር ለመሥራት ቃል ስንገባ ከፊታችን ምን እንደሚጠብቀን እና ወደፊት ምን ማድረግ እንደሚገባን እንኳ የምናውቀው ብዙ አልነበረም፡፡ብቻ የሕገወጥ ሰዎች ዝውውርን የሚመለከት መረጃ ለማሰስ ቀንና ማታ እንዲሁም ብዙ የእረፍት ቀኖቻችንን ተጠቅመናል::’

በመቀጠልም የሁለት ሳምንት እረፍት ወሰዱና ጉዞ ሆነ-ወደ ካምቦዲያ፡፡በእርግጥ ቤተሰቦቻቸውም ሆኑ አለቆቻቸው ጉዟቸውን ለማደናቀፍ ፈልገው ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ሁለቱ ጓደኛሞች ጉዳዩ አሳስቧቸው ገቡበት እንጅ ድርጅቱ ተቋቋሞ ሥራውን እንዴት እንደሚሰራ በሃሳብ ደረጃ እንኳ ምንም አልነበረም፡፡ሴቶችን ከሽርሙጥና ቤት ለማስወጣት ጥረት የምታደርግ እና ምቹ ሁኔታን ልትፈጥርላቸው የምትዳክር አንዲት ሴት ወይዘሮ አገኙ፡፡

ብቻ ለእነሱ ዋናው ነገር ገንዘቡን መሰብሰብና ለቃላቸው ታማኝ ሆነው መገኘታቸውን ማረጋገጡ ላይ ነው፡፡ይህንንም ለማሟላት ወደካምቦዲያ በማቅናት በሪፖርት ላይና በፊልም የዩትን የማይታመን የሕገወጥ ሰዎች ዝውውር ሰለባዎችን እዚህ በዓይናቸው ማየት ችለዋል፡፡

ያች ሴት ወይዘሮ ከወሲብ ባርነት ያላቀቀቻቸውን ሴት ልጆች በሰራችላቸው መጠለያ ውስጥ እያስጎበኘቻቸው ነበር፡፡ ‘እስኪ አስበው ዶክመንታሪ ፊልም እኮ አንድ ነገር ነው፡፡እዚህ ግን ከወሲብ ባርነት የወጣች እና ሰቆቃ የተፈጸመባት የ6 ዓመት ልጅ ታያለህ፡፡ይህ እኮ በአይምሮህም ሆነ በምናብህ ለማሰብ የሚከብድ ሰቅጣጭ ነገር ነው፡፡በወቅቱ ወይዘሮዋን ለመርዳት ቃል ብንገባላትም ከፊታችን የሚጠብቀን ግን አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡እንዴት መርዳት እንዳለብን መንገዱም እውቀቱም አልነበረን፡፡ምናልባት ይሄ አለማወቃችን ነበር ዋነኛ ችግራችን፡፡ምንም ባናውቅም ቅሉ በየመጽሃፉ ላይ የሰፈሩትን ህጎችና አሰራሮች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ልንጥሳቸው እንደምንችል ከኒክ ጋር ተስማማን፡፡’ ይላል-ጃሬድ ግሪንበርግ፡፡

ወደፊት ሊወስዳቸው የሚችለውን ማንኛውንም አስፈላጊ ነገር ሁሉ ለማድረግ በድጋሚ ቃል የገቡት እነ ጃሬድ ኢንተርፕርነር ማለት ይላሉ ‘ኢንተርፕርነር ማለት ያሰበውን እና መሆን የሚመኘውን ለሰዎች ለመግለጽ ውስጣዊ ፍላጎት ያለው በአስቸጋሪ ሰዓት እንኳ ይህን ምኞቱን ዕውን ለማድረግ ወደፊት አቋሙን የማያዛንፍ እና ህልሙን ለመፈጸም ተነሳሽነቱ ያለው ሰው ነው፡፡ይህን ደግሞ እያንዳንዱ ግለሰብ ሊያደርገው ይችላል:: ምንም ዓይነት የተለየ ትምህርትና ብቃት አይጠይቅም፡፡የሚፈለግብህ ነገር ቢኖር ሊገጥምህ በሚችሉ አስቸጋሪ ነገሮች አለመማረር መቻል ነው፡፡እንዲያውም ከውስጥህ ተነሳሽነቱ ካለህ እንዲህ ያሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ለህልምህ መሳካት መሸጋገሪያ ድልድይ ሊሆኑህ ይችላሉ፡፡ልክ እንደ እኛ፡፡’

ይቀጥላል……..

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.