የአስተማማኝ ሕዝባዊ ፖሊሲ መርሕ- “የራስህ ከሆነ ትንከባከበዋለህ፤ባለቤት ከሌለው ለውድመት የተጋለጠ ነው፡፡” በላውረንስ ሪድ

FEE President and Author of Seven Principles of Sound Public Policy-Lawrence W. Reed

FEE President/Lawrence W. Reed

የአስተማማኝ ሕዝባዊ ፖሊሲ መርሕ- “የራስህ ከሆነ ትንከባከበዋለህ፤ባለቤት ከሌለው ለውድመት የተጋለጠ ነው፡፡”

በላውረንስ ሪድ የፋውንዴሽን ፎር ኢኮኖሚክ ኢዱኬሽን-ፕሬዚዳንት

መርሕ 2:-ይህ መርሕ የግል ንብረትን አስፈላጊነት ምትሃት ፍንትው አድር ያሳያል፡፡ በዓለም ላይ ተከስቶ የነበረውን የሶሻሊስታዊ (የጋራ) ኢኮኖሚ ውድቀትን ያብራራል፡፡ በቀድሞዋ የሶቬት ግዛት መንግስት ንብረቶችን በባለቤትነት መያዝንና በማዕከላዊ እዝ በበላይነት መምራት የሚያስችል አዋጅ አውጆ ነበር፡፡ ዋናው ዓላማ ንብረት በግል እንዳይያዝ ለማድረግ ወይም በግለሰብ ደረጃ የሚያዙ ንብረቶች እጅጉን አናሳ እንዲሆኑ ነበር፡፡ የዚህ ምክንያት ደግሞ ንብረቶችን በግል ባለቤትነት መያዝን የስግብግብነትና የፀረ-አምራችነት ተግባር እንደሆነ ማሰባቸው ነበር፡፡

በወቅቱ የነበረው መንግስት ሃብቶች ለእያንዳንዱ ሰው ጠቀሜታ ግልጋሎት ላይ እንዲውል አዋጅ አጸደቀ፡፡ ይህ በመሆኑም ቀደም ብሎ የገበሬ ቀለብ የነበረው በአንዴ ‘የሕዝብ ቀለብ’ ሆነና ሕዝብ ርሃብ ላይ ወደቀ፡፡ የኢንተርፕርነር ፋብሪካ የነበረው በአንዴ ወደ ‘ሕዝብ ፋብሪካ’ ተቀየረና ሕዝቡ ጥራት የሌላቸው ሸቀጦችን ማምረት በመጀመሩ ገበያው/ሽያጩ/ ድንበር መሻገር ተሳነው፡፡ የቀድሞዋ ሶቬት ግዛት ከጊዜ ወደጊዜ መፍጠር የቻለችው አንድ የኢኮኖሚ ጎተራንና አንድ የሕይዎታዊ መስተጋብር ቅዠት የነበረ መሆኑን ዛሬ ላይ ቆም ብለን የምናስታሰው ነው፡፡ ይሕ ከእያንዳንዱ የሶሻሊዝም ተሞክሮ የተገኘ ትምሕርት ነው፡፡ ዕውነታው ይህ ሆኖ ሳለ የሶሻሊዝም አራማጆች ግን ኦምሌት ለማዘጋጀት የተወሰኑ እንቁላሎችን መሰባበር ያስፈልጋል የሚለውን በማብራራት ፍቅር ተነድፈው ነበር፡፡ ግና እንቁላሎችን ከመሰባበር በስተቀር አንዲትም ኦምሌት ጨርሶ ማዘጋጀት አልተቻላቸውም፡፡

ንብረት መንከባከብ ላይ ጎበዝ ነኝ ብለህ የምታስብ ከሆነ፤እስቲ ለአንድ ወር ያህል ኑሮህን በሌላ ሰው ቤት ውስጥ አድርግ ወይም የዚያን ሰው መኪና ንዳ፡፡ከተወሰነ በኋላ ቤቱም ሆነ መኪናው የአንተ ቢሆን ኑሮ ሊገኝ ከሚችልበት ይዞታ (ሁኔታ) ጋር ተመሳሳይ እንደማይሆን ላረጋግጥልህ እችላለሁ፡፡ የማበረሰቡ ውስን(አላቂ) ሐብቶች እንዲባክኑ(እንዲበተኑ) ከፈለግክ፣ማድረግ ያለብህ ሐብቶቹን ከፈጠሩ ወይም ካካበቱ ሰዎች እየነጠክ፣ማዕከላዊው መንግስት እንዲያስተዳድረው አሳልፈህ መስጠት ነው፡፡ይህን ካደረግክ ሐብቱ በሞላ በአንዴ ድራሹ ይጠፋል፡፡

የተቀሩት 5 ተከታይ መርሆዎች በተከታታይ ይቀርባሉ፡፡

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.