የአስተማማኝ ሕዝባዊ ፖሊሲ 7 መርሆዎች በላውረንስ ሪድ

የአስተማማኝ ሕዝባዊ ፖሊሲ ሰባት መርሆዎች የነጻ ኢኮኖሚ ምሰሶዎች ናቸው፡፡ እንደደኔ እምነት፣የየሃገሩ እና የየፌደራል ተቋማት ዋነኛ ማዕዘናት ሁሉ በእነዚህ መርሆዎች ተውበው ቢሆን፣በተለይ ደግሞ እያንዳንዱ ህግ አርቃቂ አካል ቢረዳውና ለመርሆዎቹ መተግበር በታማኝነት ቢጥር ኖሮ እጅግ ጠንካራ፣ነጻ፣የበለጸገና የላቀ መልካ አስተዳደር ያለው ህዝብ መፍጠር ይቻል ነበር፡፡

መርህ 1- ነጻ ሰዎች እኩል አይደሉም፤እኩል ሰዎች ነጻ አይደሉም፡፡

በቅድሚያ በመርሆ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ዓ/ነገር የትኛውን የ ‘እኩልነት’ አይነት እንደሚመለከት ግልጽ ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡አንድን ወንጀል መፈጸምህን አለመፈጸምህን መሰረት በማድረግ ወንጀለኛ ወይም ነጻ ስለመሆንህ በምትዳኝበት ጊዜ በሕግ ፊት እኩል የመሆንን መብት የሚመለከተውን አይደለም፡፡ ከጾታ፣ከዘር፣ከሐብት፣ከአምልኮ ወይም ከሥርዓተ ጾታ ጋር የተገናኘውንም አይደለም፡፡
እኔ እያወራሁ ያለሁት በልውውጥ፣በገበያ፣በሥራና በየንግድ ሥራ ሊኖር ስለሚችል ገቢንና ቁሳዊ ሐብትን ስለሚመለከት ‘እኩልነት’ ነው፡፡ስለኢኮኖሚያዊ እኩልነት ነው እየተናገርኩ ያለሁት፡፡እስቲ ይህን የመጀመሪያ መርህ ሁለት ቦታ ከፍለን ቀዳሚውን ግማሽ እንመልከት፡፡

ነጻ ሰዎች እኩል አይደሉም፡፡የራሳቸውንም ሆነ የቤተሰቦቻቸውን ደህንነት እንዲያሻሽሉ፣በዕጣ-ፈንታዎቻቸው ላይ እንዲወስኑና ራሳቸውን መሆን እንዲችሉ ሰዎች ነጻነት አግኝተው ገበያ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ ወይም የንግድ ሥራ ሲያከናውኑ የሚያገኙት ውጤት የሐብት እኩልነትን የሚፈጥር አይደለም፡፡ሰዎች የሚያገኙት የገቢ መጠን በሰፊው ይለያያል፤የሚያካብቱት የሐብት መጠን እጅጉን ይለያያል፡፡ለአንዳንዶች ይህ ዕውነታ ስለማይዋጥላቸው ‘በሐብታሞች እና በድሆች መካከል ያለ ክፍተት’ ነው በማለት ችግር ያወራሉ፡፡ይልቅ እኔን እንደሚገባኝ በነጻ ማሕበረሰብ ውስጥ ያሉ ሰዎች በራሳቸው የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ እያንዳንዳችን ከሌላው በሕይዎት ካለውም ከሌለውም የምንለያይበት የትየለሌ የሆኑ ልዩ ነገሮች አሉን፡፡ታዲያ በዓለም ላይ ይን ዕውነታ እያየን፣ገበያ ውስጥ የምናደርጋቸው መስተጋብሮች ተመሳሳይ ውጤቶችን እንዲያፈሩልን ለምንድነው ተስፋ የምናደርው?

በተፈጥሮ ተሰጥኦዎቻችን እና ችሎታዎቻችን የተለያየን ነን፡፡ አንዳንዶች ከሌሎች የላቀ ተሰጥኦ አላቸው ወይም የአንዳንዶች ተሰጥኦ ብልጫ ያለው እሴት የሚፈጥር ነው፡፡አንዳንዶች ያላቸውን እጅግ የላቀ ተሰጥኦ ሳያውቁት ዕድሜያቸው ይሄዳል፡፡ከነጭራሹ ተሰጥኦዎቻቸውን ሳያውቁ የሚያልፉም ሞልተዋል፡፡ ማይክ ጆንሰን ተሰጥኦ ያለው የቅርጫት ኳስ ተጨዋች ነው፡፡እኔ ከማፈራውገንዘብ ጋር ሲነጻጸር እሱ እጅግና እጅግ ብዙ የበለጠ ገንዘብ በቅርጫት ኳስ ጨዋታ ቢያፈራ፣ይህ ሌሎችን ሊያስገርም ይገባልን?

በትጋት የማምረት ደረጃ ወይም ለሥራ ባለን ፈቃደኝነት ሁላችንም የተለያየን ነን፡፡አንዳንዶች ይበልጥ ጠንክረው ይሰራሉ፡፡ሌሎች ደግሞ ረጅም ሰዓታትን በሥራ ያሳልፋሉ፡፡በአሰራር ጥበብ የሚልቁም አሉ፡፡ይህ ዕውነት ሥራችንን የሚመዝኑበትን መስፈርትና ለሠራነው ሥራ የሚከፍሉንን የገንዘብ መጠን በሰፊው እንዲለያይ ያደርጋል፡፡
በመቆጠብም አቅምም እንዲሁ እንለያያለን፡፡ እንበልና የሃገሪቱ መሪ በዛሬዋ ምሽት አንዳች እርምጃ በመውሰድን በሃብት እና በገቢ ሁላችንንም እኩል ቢያደርጉን፣ነገ በተመሳሳይ ሰዓት ሊኖረን የሚችለው የሐብት መጠን የተለያየ ይሆናል፡፡ምክንያቱም አንዳንዶቻችን ስንቆጥብ ሌሎቻችን እናባክናለንና ነው፡፡እስቲ እናንተም ነጻ ሰዎች በኢኮኖሚ እኩል ሊሆኖ የማይችሉባቸውን ሌሎች ምክንያቶች አስቡ፡፡
እኩል ሰዎች ነጻ አይደሉም፡፡ይህ የመጀመሪያው መርህ ሁለተኛ ግማሽ ሃተታ ነው፡፡ በዓለም ላይ በየትኛውም ስፍራ ይሁን በኢኮኖሚ እኩል የሆኑ ሰዎችን ልታሳዩኝ ከቻላችሁ፣እኔ ደግሞ እነዚህ ሰዎች እጅጉን ነጻ አለመሆናቸውን አሳያችኋለሁ፡፡

ማህበረሰብን በገቢና በሐብት እኩል ማድረግ የሚያስችልህ የመጨረሻውና ብቸኛው አማራጭ በእያንዳንዱ ሰው ግንባር ላይ ጠመንጃ መደቀን ነው፡፡በሌላ አነጋገር ሰዎችን እኩል ማድረግ የምትችለው አስገዳጅ ኃይል በመጠቀም ነው፡፡አንገት መቅሊያ ሰይፍ፣ሰው መስቀያ ሸምቀቆ ገመድ፣ጥይት ወይም የኤሌክትሪክ ገመድ ታዘጋጅና ትዕዛዝ ታስተላልፋለህ፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ሰውን በሥራህ ላይ አትጠበብ፤አጠገብህ ካለው ሰው ይበልጥ ጠንክረህ ወይም ሥራህን አሳምረህ አትሥራ፤ከሌሎች የበለጠ ብልህ ሆነህ አትቆጥብ፤አዲስ ምርት ለማቅረብ ቀዳሚ አትሁን፤ተፎካካሪህ እያቀረበ ካለው ሰዎች ይበልጥ የሚፈልጉትን ምርቶች አታቅርብ ወይም አገልግሎቶች አትስጥ ማለት ነው፡፡

እርግጠኛ ነኝ ማናችሁም ብትሆኑ በእነዚህ ትዕዛዞች የሚመራ ማህበረሰብ እንዲኖር አትፈልጉም፡፡እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ መገባደጃ ላይ ኬሜር ሩዥ ካምቦዲያ እዚህ ደረጃ ላይ ለመድረስ ተቃርባ ነበር፡፡ የዚህ ውጤት ከ8ሚሊዮን ሕዝቦቿ መካከል ከ2ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን 4 ዓመታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሞት አበቃቸው፡፡ ሥላጣንን ተቆናጠው በበላይነት መዋቅር ላይ ከነበሩት በቀር በዚያን ወቅት በሕይዎት መቆየት የቻሉት የዚያች አሳዛኝ ምድር ሕዝቦች ያሳለፉት የመከራ ኑሮ በድንጋይ ዘመን ከነበረው እጅጉን የማይተናነስ ነበር፡፡

የዚህ የመጀመሪያ መርህ መልዕክት ምንድነው? በገቢ መለያየቱ የሚመጣው ከራሱ ከሕዝብ ከሆነ፣ይህን አታጥፋው ነው፡፡ አርቲፊሻል ከሆነ ፖለቲካ ወለድ እንቅፋቶች የሚመጣ ከሆነ ደግሞ አስወግደው ነው፡፡ግና እኩል ያልሆኑ ሰዎችን ወስደህ በመጫን እኩል (ወጥ) ለማድረግ አትሞክር፡፡ ለምሳሌ በ Confiscatory Tax Rates ሰዎች እኩል ማድረግ አይቻልም፡፡ ይልቁንም ይህ ኢንተርፕርነሮችና ታታሪ አምራቾች ወደ ሌሎች ሥፍራዎች እንዲሰደዱ ወይም ሥራቸውን እንዲቀይሩ የሚያደር ሲሆን ከእነዚህ ሃብት አስፋዎች ተጠቃሚ የሆነውን ብዙሃን ደግሞ የድህነት አረንቋ ውስጥ የሚከትት ነው፡፡ አብርሃም ሊንከን “ሌላውን ሰው ወደታች በመግፋትህ አንድን ሰው ከጉድጓድ ልታወጣው አትችልም::” የምተለዋ ክብር ያስገኘችለት ይህች አባባሉ ለዚህ ጥሩ ምሣሌ የምትሆን ነው፡፡

የተቀሩት 6 ተከታይ መርሆዎች በተከታታይ ይቀርባሉ፡፡

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.