የፓልመር ኢንተርቪው ከኢንተርፕርነሩ ማኬ ጋር

Dr.Tom Palmer

Dr.Tom Palmer

John Mackey

John Mackey

ኬ ፡ ሁለተኛው የንቃተ ካፒታሊዝም መርህ የባለድርሻዎች መርህ ነው፡፡ ቀደም ብዬ በተዘዋዋሪ ተናግሬያለሁ፡፡ እሱም ቢዝነሱ ለተለያዩ ባለድርሻዎች የሚፈጥረውን እሴትና ቢዝነሱ ላይ ጫና ማሳደር ስለሚችሉት ጉዳዬ ባዮች ሁሉ ማሰብ ነው፡፡ ለእነዚህ እርስ በርስ በጥቅም ለተሳሰሩት ባለድርሻዎች ፣ ለደንበኞች ፣ ለሠራተኞች ፣ ለአቅራቢዎች ፣ ለኢንቨስተሮችና ለማህበረሰቡ እሴት ለመፍጠር ስለሚተጋው ቢዝነስ ውስብስብነት ማሰብ ነው፡፡
ሦስተኛው መርህ – ቢዝነስ እጅግ በሥነ-ምግባር የታነፁና ለዓላማ ቅድሚያ የሚሰጡ የሥራ መሪዎችን ይፈልጋል፡፡ የሥራ መሪዎቹ የባለድርሻ አካላትን መርህ በመከተል ለቢዝነሱ ዓላማ የሚያገለግሉና የሚጥሩ ይሆናሉ፡፡ ስለሆነም እርምጃቸው ሁሉ ስለቢዝነሱ ጉዳይ (ወሬ) ይሆናል ማለት ነው፡፡
አራተኛው የንቃተ – ካፒታሊዝም መርህ – አላማ ፣ የባለድርሻ አካላትና የሥራ አመራር ተጣጥመውና ተቀናጅተው አብረው መጓዝ እንዲችሉ የሚያግዝ ባህል መፍጠር ነው፡፡
ፓልመር ፡ እነዚህ የጠቀስካቸው መርሆዎች አንተ ጠዋት ከመኝታህ ስትነሳ በግል ደረጃ አንተን የሚያነቃቁህ ናቸውን? “ተጨማሪ ዶላር ለማግኘት እሔዳለሁ” ነው የምትለው ወይስ “ለዐቢይ መርሆዎቼ ታማኝ እሆናለሁ” ነው?
ማኬ ፡ ይህን በተመለከተ እኔ ትንሽ ለየት ያልኩ ነኝ ብዬ አስባለሁ፡፡ ምክንያቱም ላለፉት አምስት ዓመታት ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል ከጠቅላላ ምግቦች ምንም ደመወዝ አልወሰድኩም፡፡ ጉርሻም (Bonuses) እንደዚያው፡፡ ይህ ይገኝ የነበረው ገንዘብ በዓለም ዙሪያ ላሉ ድሃ ሰዎች ለጥቃቅንና አነስተኛ ስራ የብድር አገልግሎት እንዲውል ለጠቅላላ ምግቦች ዓለምዓለ ማዕከል (The Whole Planet Foundation) ተሰጥቷል፡፡ ይህን የፈቀድኩት ከድርጅቱ ምንም ዓይነት ከፍተኛ የገንዘብ ማካካሻ አገኛለሁ ብዬ አስቤ ሳይሆን የከፍተኛ ምግቦች ዓላማ በከፍተኛ ሁኔታ ውስጤ በመስረፁ ተነሳስቼ ነው፡፡ በዓል ደረጃም ከኩባንያው ባለኝ የአክስዮን ድርሻ የማገኘው ሐሰት ከበቂዬ በላይ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

TEAM
ፓልመር ፡ እስቲ እንደገና አንድ ዓላማ የሚለውን እንዴት ታብራራዋለህ?
ማኬ ፡ የጠቅላላ ምግቦችን ከፍተኛ ዓላማዎች በቂ ጊዜ በምናገኝበት ሰዓት ይበልጥ ልገልፅልህ እችላለሁ፡፡ አሁን በደቂቃ ውስጥ መናገር የምችለው ኩባንያችን ሰባት ዐቢይ እሴቶችን መሰረት ባደረጉ ዓላማዎች ላይ የተዋቀረ መሆኑን ነው፡፡ የመጀመሪያው ዐብይ እሴታችን ደንበኞቻችንን ማርካትና ማስደሰት ነው፡፡ ሁለተኛው ዐብይ እሴታችን የሥራ ቡድኖቻችንን ደስታና ክብር ማሳደግ ነው፡፡ ሦስተኛው ዐብይ እሴታችን ኩባንያችንን አሳድገን ትርፋማ በመሆን ሐብት መፍጠር ነው፡፡ አራተኛው ዐብይ እሴት በማህበረሰባችን ውስጥ መልካም ዜጋ በመሆን የቢዝነስ ስራችንን ማከናወን ነው፡፡ አምስተኛው ዐብይ እሴት ቢዝነሳችንን ከተፈጥሮቸ አካባቢያችን ጋር የተቀናጀና የተወዳጀ ማድረግ ነው፡፡ ስድስተኛው ዐብይ እሴት አቅራቢዎቻችንን እንደ ባለድርሻ አካል በመውሰድ ከእነርሱ ጋር አብሮ የማደግ (የማሸነፍ) ግንኙነት ማዳበር ነው፡፡ ሰባተኛው ደግሞ ለቢዝነሳችን የድርሻ አካላት (Partners) በሙሉ ስለጤናማ የአመጋገብ ስርዓትና ጤናማ የአኗኗር ዘዬን ማስተማር ነው፡፡ ስለሆነም ከፍተኛ ዓላማዎችን በእነዚህ ዐብይ እሴቶቻችን ላይ በቀጥታ የተዋቀሩ ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል ለመጥቀስ ያህል አንዱ የአሜሪካን ሕዝብ ጤና መታደግ ነው፡፡
ሕዝባችን ወፍራምና ሕመምተኛ ነው፡፡ ጤናን የሚያናጉ ምግቦችን እየተመገብን በልብ ሕመም ፣ በካንሰርና በስኳር በሽታ እንሞታለን፡፡ እነዚህ ከአኗኗር ዘዬ ጉድለት የሚከሰቱ በሽታዎች ናቸው፡፡ በሽታዎቹን በአብዛኛው ልንከላከላቸው ወይም ልንቀለብሳቸው እንችላለን፡፡ ሌላው ከፍተኛ ዓላማ የግብርና ስርዓታችንን የተመለከተ ነው፡፡ የግብርናው ስርዓታችን ይበልጥ ዘላቂ እንዲሆንና የምርታማነት አቅማችን መጎልበት እንዲችል መጣር ነው፡፡
ሦስተኛው ከፍተኛ ዓለማችን ከመላው ዓለም ማዕከል (The kghole plane foundation) ጋር የተያያዘ ሲሆን ከግራሚን ትረስት (Grameen Trust) እና ሌሎች የጥቃቅንና አነስተኛ ሥራ የብድር ተቋማት ጋር በመሆን ከዓለም ላይ ድህንት እንዲጠፋ ዕገዛ ማድረግ ነው፡፡ (ግራሚን ባንክና ግራሚን ትረስት በድሃ አገሮች ውስጥ እየተንቀሳቀሰ የማይክሮፋይናንስ ድጋፍ በመስጠት በተለይም ለሴቶች እገዛ በማድረግ ወደ ልማት እንዲገቡ በመስራት ላይ ያለ ድርጅት ነው፡፡) በአሁኑ ጊዜ በ34 አገራት ውስጥ እየተንቀሳቀሰ እንገኛለን፡፡ በዚህ አካሔድ በመቶ ሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እያመጣን እንገኛለን፡፡ አራተኛው ከፍተኛ ዓላማዎች ንቃተ – ካፒታሊዝምን ማስፋፋት (ማሰራጨት) ነው፡፡
ፓልመር ፡ ስለቢዝነስ ዓላማዎች ተናግረሃል፡፡ ከዓለማዎቹ አንፃር ስናስብ ትርፋማ መሆን ለምን አስፈለገ? ቢዝነስ የትርፍን ከፍተኛነት እያሳደገ የሚሔድ ድርጅት አይደለም ወይ? ለትርፋማነት ሳትሔዱ እነዚህን ዓላማዎች ማሳካት አይቻላችሁም ወይ? ወጪያችሁ ብቻ መሸፈን የሚያስችል ገንዘብ ማመንጨት አይቻልም ወይ?
ማኬ ፡ አንደኛው መልስ – ውጤታማ መሆን አትችልም ነው ምክንያቱም ወጪህን መሸፈን የሚያስችል ገንዘብ ለማመንጨት ብቻ የምትሔድ ከሆነ መፍጠር የምትችለው ተፅዕኖ በጣም የመነመነ ነው የሚሆን፡፡ ጠቅላላ ምግቦች ዛሬ እየፈጠረ ያለው ተፅዕኖ ከሰላሳ ወይም ከሃያ ወይም ከአስራ አምስት ወይም አስር ዓመታት በፊት ከነበረው እጅግ የላቀ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ምክንያቱም እጅግ ትርፋማ ሆነን ማደግ በመቻላችን ነው፡፡ ዓላማዎቻችንን ይበልጥና ይበልጥ ዕውን ለማድረግ ከጥቂት ሺዎች ይልቅ ሚሊዮን ሕዝቦች ጋር ማድረስና መርዳት ችለናል፡፡ ስለሆነም ዓላማህን በተሻለ ደረጃ ማሳካት ከፈለግክ ትርፋማ መሆን እጅግ አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡ ሌላው የትርፋማነት ጥቅም ዓለማችን ለምትፈልገው ክልሰፋና የዕድገት እርምጃ የሚያስፈልገውን ካፒታል መፍጠር ያስችላል፡፡ ትርፉ ከሌለ ዕድገት የለም፡፡ ሁለቱ እርስ በርሳቸው ሙሉ በሙሉ የተቆራኙ ናቸው፡፡
ፓልመር ፡ የቢዝነስ ትርፎቻችሁ ወደ የባለ አክስዮኖቹ ኪስ ቢገባ ፣ ተልዕኮአችሁን በተፈለገው ደረጃ ማሳካት ይቻላችኃልን?
ማኬ ፡ በርግጥ ቢዝነሱ የሚያፈራው አብዛኛው ትርፍ ወደ ባለአክስዮኖች ኪስ የሚገባ አይደለም፡፡ በአንፃራዊነት ስናይ በጣም ትንሽ እነጅ (ፐርሰንት) ብቻ ነው ከትርፉ ድርሻ (dividends) ለባለ አክስዮኖቹ የሚከፋፈል ካተረፍነው ገንዘብ ከዘጠና ፐርሰንት በላይ የሚሆነው ለቢዝነሱ ማስፋፊያ ዳግም እዚያው ኢንቨስት ይደረጋል፡፡ አበክሬ የምናገረው ትርፋችንን መቶ ፐርሰንት ለባለ አክስዮኖቹ እንደ ትርፉ ድርሻ አከፋፍለን ቢሆን ኖሮ ፣ በርግጥ ያ መሆን ይችል ነበር፡ ግና ይህን የሚያደርግ አንድም የቢዝነስ ድርጅት አላውቅም ከሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ትረስት (Real Esate Investment Trust, REIT) በስተቀር የትም ስፍራ ቢሆን ማንኛውም የቢዝነስ ድርጅት በሚያገኘው ትርፍ ቢዝነሱን ያስፋፋል፡፡ ከዚህም በላይ ባለአክስዮኖቹ ትርፋማ በመሆናቸው ራሱ ለቢዝነሱ አንቨስት እንዲያደርጉ ይገፋፋቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ከፍተኛ ዓላማዎችህን ከግብ የምታደርስበት ካፒታል ሊኖርህ አይችልም፡፡ የአንድን ተቋም የካፒታል እሴት መጨመር መቻል ማለት እሴት መጨመር መቻል ማለት ነው፡፡ ለዚህ ጥሩ መለኪየው ደግሞ ምን ያህል አክስዮን ገዝተሃል የሚለው ይሆናል፡፡ ይህ ነው ባለፉት ሰላሳ ዘለል ዓመታት ውስጥ ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው እሴት መፍጠር ችለናል በማለት ቀደም ብዬ የተናገርኩት፡፡
ፓልመር ፡ አንዳንዴ ሰዎች ነፀ ገበያ መበላለጥን ወይም ልዩነትን (inequality) ይፈጥራል ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ይህን ጉዳይ አንተ እንዴት ትመለከተዋለህ?
ማኬ ፡ ይህ እውነት አይመስለኝም፡፡ በአጠቃላይ የሰው ልጅ ታሪክ እንዳየነወ ስር በሰደደ ድህነት ውስጥ መኖ ለአብዛኞቹ ሕዝቦች የተለመደ የሰው ልጅ ክስተት ሆኗል፡፡ ሁሉም የሰው ልጆች እኩል ድሆች ነበሩ ፤ ይኖሩ የነበረው የዕድሜ ጣራው በጥቅሉ ሲታይ አጭር ነበር፡፡ ከዛሬ ሁለት መቶ ዓመታት በፊት በዚህች ምድር ላይ በሕይወት ይኖሩ ከነበሩት ሰዎች 85 በመቶ (ፐርሰንት) ያህሉ በዛሬው ዶላር ተመን ለዕለት ኑሮአቸው ከአንድ ዶላር ባነሰ ገቢ ይተዳደሩ ነበር፡፡ አስቡ 85 በመቶ ሕዝብ ይህ አኃዝ ዛሬ ወደ 20 በመቶ ወርዷል፡፡ በዚህ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ዜሮ መድረስ ይኖርበታል ነው፡፡ ስለሆነም ይህ የሚያመለክተወ እየተጨመረ የሚሔድን ዕድገት ነው፡፡ ዓለም ሐብታም እየሆነች ነው ፤ ሕዝብ ከድህነት እየተላቀቀ ነው ፤ ሰብአዊነትም በትክክል እያደገ ነው ፤ ባህላችንም እየዳበረ ነው ፤ ዕውቀታችን እየሰፋ ነው፡፡ አካሔዳችን ቁልቁል ሳይሆን ወደ ላይ ነው፡፡ እራሳችንን ከጥፋት (ውድቀት) መቆጣጠር ከተሳነን ግን ያ አደጋ ያስከትላል፡፡ ምክንየቱም አንዳንዴ ሰዎች ጦርነት ናፋቂ ይሆናሉ፡፡ በነገራችን ላይ ቢዝነስ ፣ የቢዝነስ ተቋማት እንዲሁም ፈጠራ ሐብት እንዲስፋፋ የምንተጋው አንዱ ምክንያታችንም ሰዎች ኃይላቸውን (ውስጣዊ አቅማቸውን) ለጦርነት ፣ ለፖለቲካዊ ግጭትና ለሐብት ውድመት ሳይሆን ለጤናማ ሥራ (አገልግሎት) እንዲውሉ ለማድረግ ነው፡፡ ይህ ራሱን የቻለ ትልቅ ርዕሰ ጉዳይ ነው፡፡
እናስ ይኼ መበላለጥን (ልዩነትን) ይጨምራል? ካፒታሊዝም ያን ያህል መበላለጥን ይፈጥራል ብዬ አላስብም፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ይበልጥ እንዲበለፅጉ ያደርጋልና፡፡ ይህ ማለት ግን እያንዳንዱ ሰው በእኩል ደረጃና ፍጥነት ያድጋል ማለት አይደለም፡፡ ሁሉም ሰው በጊዜ ሂደት ውስጥ ወደ ዕድገት ይመጣል፡፡ ይህ እየሆነ ያለ መሆኑን ተመልክተናል፡፡ በተለይም በላፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በቻይናና በሕንድ ከድህነት ሲላቀቁ አይተናል፡፡ ይህ የሆነው ካፒታሊዝምን ይበልጥ በመቀበላቸው ነው፡፡ በገሀድ እንደምናየው አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች ቀድመውና ፈጥነው በመበልፀግ ድህነትን በቀላሉ ያመልጣሉ፡፡ ይህ ታዲያ ድህነትን መከሰት አይደልም ድህነት እንዲያከትም ማድረግ እንጂ ብዙ ሰዎች እንደሚያስቡት ነፃ ገበያ መበላለጥን (ልዩነትን) አይከሰትም፡፡ ታሪክ እንደሚመሰክረው በየትኛውም የማህበረሰብ አደረጃጀት ውስጥ ሁሌም መበላለጥ (ልዩነት) ይኖራል፡፡ ሌላው ቀርቶ የማህበረሰቡን አባላት እኩል የሐብት ባለቤት ያደርጋል ተብሎ የተሰበከለት የኮምዩኒዝም ስርዓት ሳይቀር የሐብት ባለቤቶችን በደረጃዎች ያዋቀረች ምሁራንን የልዩ ጥቅም ባለመብት የሚያደርግ ነው፡፡ ስለሆነም መበላጥን የካፒታሊዝም ችግር አድርጎ ማየት ተገቢ አይመስለኝም፡፡ ካፒታሊዝም ሰዎችን ከድህነት የሚያወጣ ፣ ይበልጥ እንዲበለፅጉ የሚያደርግና ሐብት እንዲያፈሩ የሚያስችል ነው፡፡ ይህ በጣም ጥሩ ነገር ነው፡፡ ልናተኩርበት የሚገባውም ይኸው መሆን አለበት፡፡
በዓለም ላይ የሚታየው ትልቁ ክፍተት የነፃ – ገበያ ካፒታሊዝምን በመቀበላቸው ሀብታም በሆኑና ባለመቀበላቸው ድህነት ውስጥ በቀሩት መካከል ያለው ነው፡፡ ችግሩ አንዳንዳችን ሐብታም ሆኑ ሌሎች ደህይተው ቀሩ አይደለም፡፡ መሆንም ያለበት ይህ አይደለም፡፡
ፓልመር ፡ የነፃ ገበያ ካፒታሊዝም ሰዎች ትርፋማና የቢዝነስ ባለቤቶች መሆን ከቻሉበት ሌሎ ስርዓቶች በተለይም ከክሮኒ ካፒታሊዝም የተለየ መሆኑን ተናግረሃል፡፡ ይህን አስመልክቶ በአንተ የሞራል ዕይታና በብዙ የዓለም አገራት ባለው ተጨባጭ ዕውነታ መካከል ልዩነት ምንድነው?
ማኬ ፡ የሕግ የበላይነት ሊኖህ ይገባል፡፡ ሰዎች እያንዳንዳቸው ላይ በእኩል ደረጃ ተፈፃሚ የሚሆኑ መመሪያዎች ሊኖቸው ይገባል፡፡ መመሪያዎቹ ተፈፃሚ መሆን አለባቸው፡፡ በሁሉም ሰው ላይ በእኩል ደረጃ መተግበርን ዋነኛ ግቡ ያደረገ ሕገ ያስፈልገናል፡፡ አንዳንዳችን ልዩ መብት አጎናፅፎ ሌሎችን የሚናፍግ መሆን የለበትም፡፡ በብዙ ማህበረሰቦች እየተካሔደ ያለና በአሜሪካ ደግሞ ይበልጥ እየተካሔደ ያለው ምን መሰለህ – ከፖለቲካዊ ጋር ትስስር ያላቸው ሰዎች የተለየ ጥቅም እንዲየገኙ ይደረጋል፡፡ ይህ ስህተት ብቻም ሳይሆን መጥፎም ነው፡፡ አንድ ማህበረሰብ የክሮኒ ካፒታሊዝም ወይም በጓደኞቼ ማይክል ስትሮንግ አጠራር የ”ካፒታሊዝም” ሰለባ በሆነበት ደረጃ ልክ ከነፃ ገበያው ማህበረሰብ ውጭ ስለሚሆን ፣ በሙሉ አቅሙ ሰርቶ ከፍተኛ ብልፅግና ላይ እንዳይደርስ ያደርገዋል፡፡ ይህ አግባብነት የጎደለው ተግባር ለብዙና ብዙ ሰዎች እንቅፋት በመሆን በሕግ የበላይነት በታገዘ እውነተኛ የነፃ ገበያ ስርዓት የሚመሩ ሰዎች ሰርተው ከሚበለፅጉት በታች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡
ፓልመር ፡ አሁን እየኖርክባት ወዳለኸው አገር እንመለስ – ወደ አሜሪካ፡፡ በአሜሪካ ውስጥ ክሮኒዝም አለብህ ታሰባለህ?
ማኬ ፡ ወቅታዊ የሆኑ ሁለት ምርጥ ምሳሌዎቼን ልስጥህ፡፡ የእርዳታ መመሪያዎችንና ደንቦችን በተመለከተ ያቀረቡት ሰነድ በ Obama care ስር አልፎ (ታይቶ) በኦባማ አስተዳደር ተቀባይነትን እንዲያገኝ ያደረጉ በቁጥር ከሺህ በላይ የሚሆኑ የዕርዳታን መኖ ጠያቂዎች አሉ፡፡ ይህ አንዱ የክሮኒዝም ዓይነት ነው፡፡ መመሪያዎቹ በእያንዳንዱ ሰው ላይ በእኩል ተፈፃሚ የሚሆኑ አይደሉም፡፡ ለአንዱ የዕርዳታ መኖር ጠያቂ (waiver) ስልጣን መስጠት ማለት ሌላውን ደግሞ ስልጣን መንፈግ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ስትጓዝ ስልጣን ላይ ላለው የፖለቲካ ፓርቲ የገንዘብ ድጋፍ ያላደረጉትን ወይም በማንኛውም ምክንያት ያልወደድካቸውን መብት መንፈግ ትችላለህ፡፡ እያለህ አንዳንዶች ላይ የምትተገብር ሌሎ ላይ የማትተገብር እንደፍላጎትህ የምትጠቀምበት (arbitrary law) ሕግ ይኖረሃል፡፡
ሁለተኛ ምሳሌ – ክሮኒ ካፒታሊዝምን በአሁኑ ወቅት ለግሪን ቴክኖሊጂ (Green Technology) እየተደረገ ባለው ያ ሁሉ ድጎማ እያየሁኝ ነው ያለሁት፡፡ መንግስት በራሱ ገንዘብ ስለሌለው ፤ ከግብር ከፋዮች ገንዘብ እየሰበሰበ አንዳንድ ቢዝነሶችን ይደጉማል ፤ ፖለቲካዉ ለወደዳቸው ሰዎችም ያከፋፍላል፡፡ የጀነራል ኤሌክትሪክን (General Electric) የታክስ አከፋፈለ በተመለከተ በልዩ ሁኔታ ከታክስ ነፃ የተደረገበትን ጨምሮ የተደረጉለትን የታክስ ቅነሳዎች ከተፃፈው የታክስ ሕግ ውስጥ እስከማካተት ድረስ እየተደረገ ያለው ነገር ሁሉ እያየሁኝ ነው፡፡ እነዚህ (እነርሱ) ወደ አማራጭ የኃይል ቴክኖሎጂ (alternatice energy techonology) በመግባታቸው ወይም ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቻቸው ከሚያገኙት አብዛኛው ገቢ ላይ ታክስ እማይቆረጥበት ደረጃ ላይ እየደረሱ ነው ምክንያቱም ዳግም ከፖለቲካው ጋር ትስስር ስላላቸው ነው፡፡ እናም ይህ ያበሳጨኛል፡፡ በጣም መጥፎ ነገር ሆኖ ይታየኛል፡፡
ፓልመር ፡ ሞራል የለሽ (ሞራል አልባ) ልትለው ትችላለህ?
ማኬ ፡ አዎ ፣ በሚገባ ሞራል የለሽ … ነው፡፡ ሞራል የለሽ ብዬ እጠራዋለሁ፡፡ ምን ማለት እንደሆነ ማስረዳት ያስፈልጋል ግን ይህ የኔን ስነ-ምግባርና ስሜቴ ሰናይና ዕኩይ ብሎ የሚለይልኝን የሚጥስብኝ ነው በእውነቱ የሌሎችን ሰዎች ሰነ-ምግባር ይጣስ አይጣስ መናገር ያዳግታል፡፡ እኔ በእውነቱ አልወድደውም ፤ እቃወማለሁ፡፡ ማህበረሰብ እንዴት መተዳደር እንዳለበት እኔ ከማስበው ጋር ጨርሶ አይጣጣምም፡፡ ጠንካራ የሕግ የበላይነት ባለው ማህበረሰብ ውስጥ እንደዚህ ዓይነቱ ነገር መፈጠር የለበትም፡፡
ፓልመር ፡ የነፃ ገበያ ካፒታሊዝም ተጠቃሚዎች እነማን ናቸው ትላለህ?
ማኬ ፡ ሁሉም፡፡ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ሰው ተጠቃሚ ነው፡፡ የነፃ ገበያ ካፒታሊዝም ሰዎችን ከድህነት ውስጥ በማውጣት ሰብአዊነትን እጅግ ከፍ ያደረገ ነው፡፡ ይህችን አገር ሐብታም ያደረጋት እሱ ነው፡፡ መናጢ ድሆች ነበርን፡፡ ግና ያኔም አሜሪካ የዕድል በር ከፋች ምድር ነበረች፡፡ አሜሪካ ምንም እንኳ ፍፁም ባትሆንም በዓለም ላይ ለጥቂት መቶ ዓመታት ከዓለም ገበያዎች እጅጉን ነፃ ሊባል የሚችለውን ማጣጣም የቻለች አገር ናት፡፡ በዚህም ምክንያት ነው ከከፋ የድህነት ኑሮ በመላቀቅ መበልፀግና በአስደናቂ ፍጥነት ሐብታም መሆን የቻልነው፡፡
ፓልመር ፡ ዴይርድሬ ማክ-ክሎስኪ “የቡርዥዋ ክብር” በተባለው መጽሐፍዋ ውስጥ ሰዎች ስለ ቢዝነስና ስለ ኢንተርፕሬነራዊ ፍልሰፋ የነበራቸው የአስተሳሰብ ለውጥ ነበር ሰዎችን ወደ ብልፅግና ማምጣት ያልቻለው የሚል አቋም አላት፡፡ እና ሐብትን ለሚፈጥሩ ቢዝነሶች ደግሞ ክብር ሊኖረን ይቻላል ብለህ ታስባለህ?
ማኬ ፡ አዎ ፣ የምንችል ይመስለኛል፡፡ ምክንየቱም ሮናልድ ሬጋን በተመረጠበት ጊዜ ምን እንደተከሰተ አይቻለሁ፡፡ በ1970ዎቹ አሜሪካ ቁልቁል እየሔደች ነበር፡፡ ይህ ምንም የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ ግሽበትና የወለድ ምጣኔው የት ደርሶ እንደነበር ፣ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) ወዴት እያመራ እንደነበርና ገበያ የተዳከመበትን ፍጥነት መመልከት ይቻላል፡፡ የነበርንበት የስታግፍሌሽን (Stagflation) ሰለባ ፣ ወደ ኬይኔሽያን ፍልስፍና (Keynesian Philosophy) ጥልቅ ሽንቁሮች ማምራታችንን ነበር የሚገልጸው ከዚያም አዲስ መሪ መጣ ታክሶችን የቆረጠና ከአንዳንድ ደንቦችን በርካታ ኢንዱስትሪዎችን ነፃ ያወጣ መሪ አሜሪካን ወደ ህዳሴ ፣ ዳግም ውልደት ቀየራት፡፡ ይህ ድንቅ ስራ ላለፉት 25 ወይም ከዚያ በላይ ዓመታት ይዞን መጣ፡፡ በመሰረቱ ወደ ላይ አቅጣጫ የሚያመራ ዕድገትና ግስጋሴ ነበረን አለመታደል ሆኖ አሁን ደግሞ ዳግም ይበልጥ ወደ ኃላ ተመለስን ቢያንስ በተወሰኑ እርምጃዎች ወደ ታች ተንሸራተትን፡፡ በመጀመሪያ በ ……. እነዚህን ፕሬዚዳንቶችና ፖለቲከኞች እያንዳንዳቸውን ነው የምወቅሰው፡፡ ሬጋንም በምንም መንገድ ፍፁም አልነበረም፡፡ ነገር ግን የቅርቡ ቡሽ ያንን ውድቀት አፋጠነው፡፡ አሁን ደግሞ ቀደም ያሉት ፕሬዚዳንቶች ወደ ኃላ ከመለስን በላይ እጅጉን በተለየ ደረጃ አርቆ ወደ ኃላ መለሰን፡፡
ግና ታውቃለህ ፤ እኔ ኢንተርፕሬነር ነኝ ፤ እናም አመለካከቴ ቀና ነው፡፡ ይህን ሒደት መቀልበስ ይቻላል ብዬ አስባለሁ፡፡ ውድቀታችን የማይቀለበስ ደረጃ ላይ የደረሰ አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን አግባብነት ያላቸውን ወሳኝ ለውጦች በፍጥነት ማካሔድ ይገባናል ብዬ አስባለሁ፡፡ በአንድ ምክንያት ክስረት ውስጥ እየገባን ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የታክስን መጠን ሳንጨምና የአሜሪካን ተቋማት ሥራ ሳናስቆም ፈቃደኛ ሆነን በአፅንኦት ልንነጋገርበት ካልቻልን ፣ ቁልቁል የመሄዳችን ጉዳይ አይቀሬ ሆኖ ይታየኛል፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ድረስ ነገሮችን ማስተካከል ይቻላል የሚል ተስፋ አለኝ፡፡
ፓልመር ፡ ካፒታሊዝም መስማማትን (Conformity) ይፈጥራል ብለህ ታስባለህ ወይስ ለብዝሃነት (diversity) ቦታ ይሰጣል ትላለህ? የአይሁድ ሕግ የሚጠይቀውን መስፈርት የሚያሟላ ምግብ (Kosher food) ወይም በሙስሊም ሕግ የተዘጋጀ (Halal food) ምግብ ስለሚወድዱ ሰዎች ፣ ወይም በሃይማኖት ወይም በባህል ወይም በፆታ …… አናሳ ስለሆኑት ሰዎች እያሰብኩ ነው፡፡
ማኬ ፡ እነዚህን ነገሮች መዘርዘር በመቻልህ አንተ ራስህ ለጥያቄዎቹ ምላሽ አግኝተሃል ማለት እችላለሁ፡፡ ካፒታሊዝም በዋነኝነት ለሌሎም ለራስም እሴት ለመፍጠር ሰዎችን በአንድነት ያስተባብራል፡፡ ካፒታሊዝም ማለት ያ ነው፡፡ በእርግጥ ግለ – ፍላጎትም በዚህ ውስጥ ይኖራል፡፡ ቁልፍ ነገር ተባብሮ በመስራት ለራስም ሆነ ለሌሎች እሴት መፍጠር መቻል ነው፡፡ እናም ለምርታማነት የሚደረገው ጥረት ብዝሃነትን ይፈጥራል – ምክንያቱም የሰው ልጆች በጣም ብዝሃናት ያለው ፍላጎቶች አላቸውና፡፡ ካፒታሊዝም ገበያውን በማስተባበር እነዚህን ፍላጎቶች ለሟሟላት ይሠራል፡፡ ይህ ደግሞ ለግለኝነት ሰፊ ምህዳር ይሰጣል፡፡ በጌታና ሎሌ (በአዛዥና ታዛዥ) ዓይነት ሥርዓት ሰዎች በልዩ የጥቅም መብት በተደራጁበት ወይም በሐይማኖት የእልቅና መሰላል በተዋቀሩበት ወይም የዩኒቨርስቲ ምሁራንም ሆኑ ሌሎች ፍፁም የሚበጅህን የማውቅልህ እኔ ብቻ ነኝ የሚሉ ቡድኖች ባሉበት ማህበረሰብ ውስጥ የምትኖር ከሆነ ፣ እነዚህ ሰዎች ወይም ቡድኖች ሐሳቦቻቸውን በእያንዳንዱ ሰው ላይ በኃይል ይጭናሉ ፤ ሰዎችን በማስገደድ ያዝዛል፡፡ በካፒታሊዝም ማህበረሰብ ውስጥ ለግለኝነት በጣሙን የላቀ ነፃነት ይሠጣል፡፡ የካፒታሊስቱ ማህበረሰብ ቢሊዮኖች አበቦች እንዲያድጉና እንዲያብቡ ዕድል ይሠጣል፡፡ ምክንያቱም የካፒታሊዝም ዋነኛ ግቡ ወይም መዳረሻው ወይም የተፈጠረበት ዓላው ለሰው ልጅ ዕድገት ነውና!
ፓልመር ፡ ካፒታሊዝምን አስመልክቶ መጪው ጊዜ የሰነየ ፣ የደረጃና ብልፅግናን የሚያስገኝ እንዲሆን ምንድነው ርዕይህ?

ማኬ ፡ እንደኔ ፍላጎት ቀዳሚ መሆን ያለበት – የካፒታሊዝም ተሟጋቾች (ጠባቂዎች) እየተጠቀሙ ያለው ስትራቴጂ በካፒታሊዝም ጠላቶች እጅ እየወደቀ መሆኑን ሊረዱ ይገባል፡፡ እነዚህ ሰዎች በከፍተኛ የሞራል መሰረት ላይ የተገነባው ካፒታሊዝም – መበላለጥ የሚያመጣ ፣ ሠራተኞችን የሚበዘብዝ ፣ ሸማቶችን የሚያታልል ፣ ተፈጥሮአዊ አካባቢን የሚያወድምና ማህበረሰብን የሚሸረሽር የብዝበዛ ፣ የስግብግብነትና የራስ ወዳድነት ስርዓ ተደርጎ እንዲሳል ለካፒታሊዝም ጠላቶች በር ከፍተዋል፡፡ የካፒታሊዝም ተሟጋቾች ለጠላቶቻቸው እንዴት አፀፋ መስጠት እንዳለባቸው አያውቁም፡፡ ምክንያቱም ካፒታሊዝም እንዲተች (እንዲብጠለጠል) ራሳቸው ትልቅ ክፍተት ካፒታሊዝም እየፈጠረ ያለውን እሴት ማየት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይኸውም ለኢንቨስተሮች ብቻ ሳይሆን (ለኢንቨስተሮችም እሴት መፍጠሩ እንዳለ ሆኖ) በቢዝነስ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ላለው አጠቃላይ ሕዝብ ፣ ለደንበኞች ፣ ለሰራተኞ ፣ ለአቅራቢዎና በአጠቃላይ ለማህበረሰቡ ሁሉ እሴቶችን ይፈጥራል፡፡ በመንግስትም እሴትን ይፈጥር – ማለት የፈለኩት የሥራ እድሎችን በመክፈት ፣ ገቢንና ሐብትን በመፍጠር ታክሶችን መሰብሰብ ከሚያስችለው ካለ ጠንካራ የቢዝነስ ሴክተር በመፍጠር መንግስታችን ምን ይዉጠው ነበር? ይህ አይደለም እኔን ዘወትር ደስ የሚያሰኘኝ፡፡ ልብ በል፡፡

ካፒታሊዝም የእሴት ምንጭ ነው፡፡ ማህበራዊ ትብብርን (የህብረት ስራን) በመፍጠር ረገድ እስከ ዛሬ ከነበሩት ሁሉ እጅጉን የላቀ ድንቅ መሳሪያ ነው፡፡ ይህን ታሪክ ነው መንገር ያለብን፡፡ የአነጋገር ስልታችንን መቀየር ይኖርብናል፡፡ ከሥነ-ምግባራዊነቱ አንፃር ለጥቂቶች ብቻ ሳይሆ ለእያንዳንዱና ሁሉም ሊጋራው የመችል እሴት እየፈጠረ መሆኑን ለማሳየት ስለ ካፒታሊዝም የምንመሰክርበት የአነጋገር ሥልታችንንን መለወጥ ያስፈልገናል፡፡ እኔ በማየው መንገድ ሌሎም ሰዎች ማየት ከቻሉ ፣ እኔ ካፒታሊዝምን እንደወደድኩት እነርሱም ሊወድዱት ይችላሉ፡፡
ፓልመር ፡ ጊዜ ሰጥተህ ቃለ – ምልልስ ማድረግ በመቻላችን አመሰግንሃለሁ!
ማኬ ፡ እኔም ደስ ብሎኛል!

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.