የሞራላዊነት አያዎ(በማኦ ዩሺ)

???????????????????????????????በዚህች መጣጥፍ ኢኮኖሚስቱ ፣ ምሁሩና ማህበራዊ ኢንተርፕሬነሩ ቻይናዊዉ ማኦ ዩሺ ገበያ የኅብረት ሥራንና ሠላምን በመፍጠሩ ረገድ የሚጫወተውን ሚና ያብራራልናል፡፡ ግለ-ፍላጎታዊ ባሕርያትንና የካፒታሊስት አቃቂረኞች የሚያቀርቡትን የቅዠት ሐሳቦች በማነፃፀር በገበያ ውስጥ ያሉ ሰዎች ትረፍንና ዝቅተኛ የሸቀጦች ዋጋን ከመፈለግ አንፃር የሚያገኙትን ጥቅሞች ይገልፅልናል፡፡ ምሣሌዎቹን የሚያቀርብልን የቻይናን ሥነ-ጹሑፋዊ ቅርስና የራሱን ተሞክሮዎች (እንዲሁም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቻይናውያንና ተሞክሮዎች) በማጣመር ቻይና ካፒታሊዝምን ለማስወገድ ያደረገችውን አሰቃቂ የሙከራ ጉዞ መሠረት በማድረግ ነው፡፡ማኦ ዩሺ መሠረቱ ቤይጂንግ ፣ ቻይና የሆነው የዩኒሩል ኢንስቲትዩት መሥራችና ሊቀመንበር ነው፡፡ የበርካታ መጽሐፍትና የብዙ ትምህርታዊና ሕዝባዊ መጣጥፎችን ደራሲ ነው፡፡ በተለያዩ ዩኑቨርስቲዎች ኢኮኖሚክስን አስተምሯል፡፡ በጣም ቀዳሚ የሚባሉትን መንግስታዊ ያልሆኑ የበጎ አድራጎ ድርጅቶችንና ከጥገኝነት ነፃ የሚያደርጉ ራስን የመቻል ድርጅቶችን በቻይና አቋቁሟል፡፡ የነፃነት ብርቱ ሻምፒዮን መሆኑ በሚገባ ይታወቃል፡፡ በ1950ዎቹ ውስጥ “የአሳማ ሥጋ ለመግዛት የምንሔድበት ካጣን ፣ የአሳማ ሥጋ ዋጋ መጨመር አለበት” እንዲሁም “ሊቀመንበር ማኦ አንድን ሳይንቲስት መገናኘት ቢፈልጉ ፣ ማን ነው ወደ ማን የሚሐየድ?” በማለቱ የጉልበት ሥራ ፣ የስደት ፣ የ”ዳግም ትምህርት” ና የረሃብ ቅጣቶችን ለመቀበል ተገድዷል፡፡ ይህ መጽሐፍ ወደ ሕትመት ከመሔዱ ጥቂት ጊዜ ቀደም ብሎ በ2011 በ82 ዓመት ዕድሜው “ማኦ ጊዶንግን ወደ ሰው ልጅ ቅርፅ መመለስ” በሚል ርዕስ ሕዝባዊ መጣጥፍ ደርሶ ለሕትመት በማብቃት በኢንተርኔት በኬይሽን ኦን ላይን ተለቅቃለች፡፡ ይህች መጣጥፍ በርካታ የግድያ ሙከራዎችን ያስከተለችበት ሲሆን በዚያው ልክ የእውነትና የፍትሕ ድምፅ በመሆን እጅግ ከፍተኛ ክብርን አስገኝታለታለች፡፡ ማኦ ዩሺ በዚህች ዓለም ከሚገኙ የዘመናችን ታላላቅ የሊበርታሪያን ቁንጮ ሰዎች መካከል አንዱ ሲሆን የሊበርታሪያንን ሐሳቦችና የነፃነት ተሞክሮን ወደ ቻይና ሕዝብና ወደ ሰፊው ዓለም ለማድረስ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይል ሠርቷል፡፡

የፍላጎት ግጭት – በጨዋዎቹ ምድርበ18ኛውና በ19ኛው ክፍለዘመናት መካከል ቻይናዊው ደራሲ ሊ ሩዜን “የመስታወት ውስጥ አበቦች” በሚል ስያሜ ልብ ወለድ ፃፈ፡፡ መጽሐፉ አግኝቶ ሰላጣና የእንጀራ ወንድሙን ተከትሎ በባሕር ላይ ስለተሰደደ ታንግ ኦ የተባለ ሰው የሚገልፅ ነው፡፡ ይህ ሰው በጉዞው ወቅት ፣ ለማመን የሚያዳግት እንግዳ የሆነ የማየት ችሎታና የተለየ ድምፅ ያላቸው ሕዝቦች የሚኖሩበትን አገራት ይጎበኛል፡፡ ከጎበኛቸው አገራት መካከል የመጀመሪያው “የጨዋዎቹ ምድር” ነው፡፡
የጨዋዎቹ ምድር ነዋሪዎች በሙሉ የሌሎችን ሰዎች ጥቅም ለመጠበቅ ሲሉ የራሳቸውን ጥቅም በማሳለፉ ሆን ብለው የችግር ኑሮ የሚገፉ ናቸው፡፡ የመጽሐፉ አስራ አንደኛ ምዕራፍ አንድ የሕግ ኦፊሰር (ፀሐፊው ሊ ሩዜን በጥንታዊቷ ቻይና የሕግ ኦፊሰሮች ልዩ የጥቅም መብቶች እንደነበራቸውና የተራ ሰዎችን ንብረት በጉልበት ይነጥቁ እንደነበር ስለሚታወቅ ፣ የሕግ ኦፊሰሩን ሆን ብሎ እንደ አንድ ገፀ ባሕርይ ተጠቅሟል) ሸቀጦችን ሲገዛ የገጠመውን ሁኔታ እንደሚከተለው ይገልፃል፡፡
በርካታ ሸቀጦችን በሚገባ ፈትሾ ካየ በኃላ የሕግ ኦፊሰሩ ሻጩን “ጓደኛዬ ፣ ዕቃዎህ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ናቸው ፤ የዕቃዎቹ ዋጋ ግን ዝቅተኛ ነው፡፡ የአንተን ጥቅም በዝቅተኛ ዋጋ ስወስድብህ እንዴት ጥሩ ስሜት ሊኖረኝ ይችላል? ዋጋ ካልጨመርክ ፣ ቀጥለን እንዳንገበያይ ትገታናለህ፡፡” ይለዋል፡፡
ሻጩም “ወደኔ መደብር መምጣትህ ለኔ ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡ አንድ አባባል አለ፡፡ ሻጭ ሰማይ የሚነካ ዋጋ ሲጠይቅ ገዥው ወደ ምድር ውረድ ብሎ መለሰለት ይባላል፡፡ የዕቃዎቼ ዋጋ ሰማይ ድረስ ሆኖ ሳለ አንተ ግን አሁንም እንድጨምር ትፈልጋለህ፡፡ በሐሳብህ ለመስማማት ይከብደኛል፡፡ ዋጋ ስለማልጨምር የምትፈልጋቸውን ዕቃዎች ሌላ መደብር ሔደህ ብትገዛ ይሻልሃል” ብሎ መለሰላት፡፡
የሕግ ኦፊሰሩ የሻጩን መልስ ካዳመጠ በኃላ የሚከተለውን ተናገረ፡፡ “ለእነዚህ ከፍተኛ ጥራት ላላቸው ዕቃዎች የሰጠኃቸው ዋጋ ዝቅተኛ ነው፡፡ ይህ ለአንተ ክስረት አይደለምን? ያለመወሻሸት በተረጋጋ አእምሮ መነጋገር ይገባናል፡፡ ሁላችንም ውስጥ የሠረፀና እንደ ጋሪ ፈረስ በአንድ አቅጣጫ የሚያስኬደን አንዳች ነገር ይኖል አያስብልምን?” ለተወሰነ ጊዜ ቢጨቃጨቁም ሻጩ ዋጋ አልጨምርም በሚለው አቋሙ ፀና፡፡ የሕግ ኦፊሰሩ እየተናደደ ለመግዛት አቅዶ ከነበረው ግማሹን ያህለ ዕቃ ብቻ ገዛ፡፡ ገዢው ልክ ከመደብሩ ሊወጣ ሲል ሻጩ መደብሩ ገቡ፡፡ ሽማግሌዎቹ የገዢውንና የሻጩን አታካራ ግራና ቀኝ ካዳመጡ በኃላ የነበረውን የግብዓት ሁኔታ በማረገጋት የሕግ ኦፊሰሩ የዕቃዎቹን 80 በመቶ እንዲወስድ በማዘዛቸው የተባለውን መጠን ወስዶ ወጣ፡፡
መጽሐፉ በመቀጠል ገዥ የዕቃዎቹ ጥረት ከፍተኛ ሆኖ ሳለ የሚጠየቀው ዋጋ እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ስለማሰቡና ሻጭ ደግሞ ዕቃዎቹ አዲስ አለመሆናቸውን (አሮጌ መሆናቸውን)ና እንደ ተራ ዕቃ መታየት እንዳለባቸው የሚገፋፉበትን ሌላ ግብዓት ይገልጻል፡፡ በመጨረሻም ገዥው ከሻጩ ዕቃች መካከል እጅግ መጥፎዎቹን ይመርጣል፡፡ በስፍራው ያሉ ሰዎች ሻጭ አግባብነት የጎደለው ሥራ እየሠራ መሆኑን እንዲመለከቱ ካደረገ በኃላ ጥፋተኛ ያስብለውና ገዥው ግማሹን ከፍተኛ ጥራት ካላቸው ቀሪውን ግማሽ ዝቅተኛ ጥራት ካላቸው የዕቃ ድርድሮች ይወስዳል፡፡ በሦስተኛው ግብይት ሁለቱም ወገኖች ለግብይት የቀረበ የብር (Silver) ክብደትና ጥራት በመፈተሸ ላይ ሳሉ ይጣላሉ፡፡ ብሩን በመግዛት ላይ ያለው ሰው ቁጣ በተቀላቀለበት ስሜት የብሩ ጥራት ዝቅተኛ መሆኑንና ክብደቱም በቂ አለመሆኑን ሲናገር በመሸጥ ላይ ያለው ወገን ደግሞ የብሩ ጥራትም ሆነ ክብደት የላቀ መሆኑን ይናገራል፡፡ ከፋዩ (ገዥው) ልክ መደብሩን ለቅቆ እንደወጣ ፣ ተከፋዩ (ሻጩ) ትርፍ ናቸው ብሎ የሚያስባቸውን ብሮች (Silverሰ) ከውጭ ሀገር ለመጡ የኔ ቢጤዎች (ድሆች) መስጠት እንዳለበት ይወስናል፡፡

በልብ ወለዱ ውስጥ ፋይዳ አለሽነታቸው ይበልጥ የሚጠቀስ ሁለት ነጥቦች ተነስተዋል፡፡ የመጀመሪያው ሁለቱም ወገኖች ለየራሳቸው ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅም መተው በሚወስኑበት ጊዜ ወይም ሁለቱም ሊያገኙ የሚችሉት ጥቅም በጣም ከፍተኛ የሆነ መሆኑን አቋም በሚይዙበት ጊዜ ያለውን መተማመን ያሳያል፡፡ በገሀዱ ሕይወት የሚያጋጥሙን (የምናደርጋቸው) ምክንያታዊ ውሳኔዎ አብዛኞቹ የየራሳችንን ፍላጎቶች ከማሳደድ የሚመነጩ ናቸው፡፡ ስለሆነም ለሌላው ወገን ሁሌም የምንወግን ከሆነ የዚህ ዓይነቱ ውዝግብ ይቀራል ብለን ከማሰብ የተነሳ የዘወትር ስህተት ውስጥ እንወድቃለን፡፡ ነገር ግን በጨዋዎቹ የተነሳ የዘወትር ስህተት ውስጥ እንወድቃለን፡፡ ነገር ግን በጨዋዎቹ ምድር ያለውን ተሞክሮ በማየት የሌሎችን ፍላጎቶች ለውሳኔዎችን መሰረት አድርገን መውሰዳችን ወደ ጭቅጭቅ የሚከትተን መሆኑን እንመለከታለን፡፡እናም አሁንም የተጣጣመና የተቀናጀ ማህበረሰብ መፍጠር የሚያስችል ምክንያታዊ መሰረቶችን ፍለጋ እንቀጥላለን፡፡
በምርምራችን አንድ እርምጃ ወደፊት ስንጓዝ ደግሞ በገሃዱ ዓለም ያለውን የቢዝነስ ጉዳይ ዕውነታዎች ስንመለከት በግብይት ውስጥ ያሉ ሁለት ወገኖች የየራሳቸውን ጥቅም ለማስከበት ባላቸው ፍላጎት በመግባቢያ ነጥቦች /ምሳሌ ዋጋና ጥራት/ ላይ በሚደራደሩበት ጊዜ ሁለቱም ወገኖች መተማመን /መስማማት/ ላይ መድረስ የሚችሉበትን ሁኔታ እንገነዘባለን፡፡ በንፅፅር ስናይ በጨዋዎቹ ምድር የዚህ ዓይነቱ ስምምነት የማይቻል ነው፡፡ በልቡ ወለዱ ውስጥ ግጭትን ለመፍታት ፀሀፊው ሽለግሌውንና የኔ ቢጤውን ማስገባቱን ከዚያም አልፎ የኃይል ግፊት መጠቀም ግድ ይለዋል፡፡ እዚህ ጋ ወሳኝና ጉልህ ዕውነታን እሃገኛለን፡፡ ይኸውም ሁለቱም ወገኖች የየራሳቸውን ጥቅም በመሻት የሚያደርጓቸው ድርድሮች ሚዛናዊነትን ማስፈን ማብቻሉ ሲሆን በአንፃሩ ግን ሁለቱም ወገኖች አንዱ የሌላውን ፍላጎቶች የሚመለከቱ ከሆነ ደግሞ ፈፅሞ ስምምነት ላይ መድረስ የማይችሉ መሆኑን ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ይህ ዘወትር ከራሱ ጋር የሚጣረስን ማህበረሰብ ይፈጥራል፡፡ ይህ ሀቅ ከአብዛኞች ሰዎች ተስፋዎች /ግምቶች/ በተቃራኒ የሚሄድ ነው፡፡ ምክንያቱም የጨዋዎቹ ምድር የነዋሪቿ የግንኙነት ሚዛን ምን መሆን እንዳለበት መገንዘብ ባለመቻሉ ምድሪቱ የከንቱዎችና የውርጋጦች ምድር ትሆናለች፡፡ ምክንያቱም በጨዋዎቹ ምድር ሰዎች የሌሎችን ሰዎች ፍላጎቶች ስለሚያሳድሩ ፣ ምድሪቱ የዕኩዮች (የመጥፎዎች) መፈልፈያ ትሆናለች፡፡ ጨዋዎቹ ልውውጥ መቋጨት በሚያዳግታቸው ጊዜ ፣ ጨዋዎቹ ጥቅም ማግኘትን የሚሹት የራሳቸውን ፍላጎቶች በመፃረር ነው የሚለውን ሐቅ በመጠቀም ከንቱዎችና ውርጋጦች ጥቅም ማግኘት የሚችሉበት ዕድል ይፈጠራል፡፡ ነገሮች በዚህ ሁኔታ ከቀጠሉ ፣ ጨዋዎቹ ይሞቱና ከንቱዎችና ውርጋጦች ይተካሉ፡፡

ከላይ ከተቀመጠው ነጥብ ማየት የምንችለው የሰው ልጆች የየራሳቸውን ፍላጎቶች በሚሹበት ጊዜ ብቻ ነው ተባብረው መስራት የሚችሉት፡፡ ይህ ነው ለሰብአዊነት ፅኑ መሠረት በመሆን ሠናይ ዓለምን መገንባት የሚያስችል የሰው ልጅ የራሱን ጥቅም ሙሉ በሙሉ በመተው በቀጥታ የሌሎችን ጥቅም ማግኘት የሚሻ ከሆነ ፣ ሠናይነት ሊታሰብ አይችልም፡፡
በእርግጥ ግጭትን ለመቀነስ ከነባራዊ ሁኔታ በመነሣት ሁላችንም ለሌላው ትኩረት መስጠትና የራስ ወዳድነት ፍላጎታችንን መቆጣጠር የሚያስችሉንን መንገዶች ማግነት ይገባናል፡፡ ነገር ግን የሁሉም ሰዎች ግብ ለሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች አትኩሮት መስጠት የሚሆን ከሆነ በጨዋዎቹ ምድር ሊ ሩዜን የገለፀው ዓይነት ግጭት ይፈጥራል፡፡ ምናልባት በጨዋዎቹ ምድር ላይ የሚታየው ዓይነት ይበልጥ አስቂኝ የሆኑ የሕይወት ገጽታዎች በገሀዱ ዓለም አይከሰትም የሚሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ግና መጽሐፉ ቀስ በቀስ የሚያቀርበው ማስረጃ በገሀዱ ዓለምና በጨዋዎቹ ምድር የሚታዩት ክስተቶች ተመሳሳይ መንስኤዎች ያላቸው መሆኑን ነው፡፡ በሌላ ዓይነት አገላለፅ ግለ-ፍላጎትን የማሳደግ መርህን በተመለከተ በሁለቱም በገሀዱ ዓለምና በጨዋዎቹ ምድር ግልፅነት ይጎድላል፡፡
የጨዋዎቹ ምድር ነዋሪዎች ፍላጎት ምንድን ነው? በቅድሚያ “ሰዎች ለምንድን ነው ልውውጥ የሚያካሄዱት?” ብለን መጠየቅ ይገባናል፡፡ በጥንት ዘመን የነበረው ዕቃን በእቃ መለዋወጥም ሆነ በዘመናዊው ዓለም ያለው ዕቃዎችን በገንዘብ መለዋወጥ ስንመለከት ከልውውጡ ጀርባ ያለው ፍላጎት የሰውን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ነው ፤ አኗኗሩ ይበልጥ ምቹና የተቃና እንዲሆን ለማድረግ ነው፡፡ የሰዎች ፍላጎት ይህ ካልሆነ ፣ ለምንስ ነው ግለሰቦ ራሳቸው ጥረው ግረው ከማግኘት ይልቅ ልውውጥን የሚመርጡት? ከመርፌና ከክር አንስተን እስከ ማቀዝቀዣና ባለቀለም ቴሌቪዥን ያሉትን ቁሳቁሳዊ መደሰቻዎቻችንን ሁሉ የምናገኘው በልውውጥ አማካይነት ነው፡፡ ሰዎች ባይለዋወጡ ኖሮ እያንዳንዱ ሰው ማድረግ ይችል የነበረው ወደ ገጠር ወጥቶ ለቀለቡ እህልና ለልብሱ ጥጥ ማምረት ፣ ቤቱንም ለመገንባት የአፈር ሸክላዎችን መጠቀምና ለህልውናው አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ሁሉ ከመሬት ውስጥ ለማውጣት መታገል ብቻ ነበር፡፡ በዚህ አካሔድ ጥንት አባቶቻችን ለአስር ሺዎች ዓመታት ሲያደርጉ እንደነበረው እያንዳንዱ ብዙ ለፍቶ የሚያገኘውን ትንሽ ውጤት በመቆጠብ ኑሮውን መግፋት ግድ ይለው ነበር፡፡ እናም የዛሬው ዘመናዊ ስልጣኔ ያስገኛቸውን ፍሬዎች (ጥቅሞች) ማጣም ባልቻልን ነበር፡፡
የጨዋዎቹ ምድር ሕዝብ መላ ያልተፈየደለትና ራስን የሚያስችል ኢኮኖሚ ያለውና ቁሳዊ ፍላጎቱንም ለማሳደግ (ለማሻሻል) ይልቁን የልውውጥን መንገድ መከተል የመረጠ መንግስትና ገበያ ያለው ነው፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ የጨዋዎቹ ምድር ነዋሪዎች ኢኮኖሚያዊ ልውውጦችን ሲያከናውኑ ስለራሳቸው ፍላጎቶች ማሰብን የማይቀበሉት ለምን ይሆን? በእርግጥ ከመነሻው ሲታሰብ የመለዋወጡ ዓላማ የራስን ጥቅም ለማሳነስና ለሌሎች ጥቅም ለመቆም ከሆነ ምናልባት ይህ የ”ጨዋነት” ባሕርይ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ በልውውጥ ውስጥ የሚሳተፉ ሰው ወይም የልውውጥ ተሞክሮ ያለው ማንም ሰው እንደሚያውቀው በልውውጥ ውስጥ ያሉ ሁለቱም ወገኖች ለየራሳቸው ጥቅም ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ግና በልውውጥ ሒደት ወቅት ከግለ-ፍላጎቶቻቸው በተፃራሪ የሚንቀሳቀሱት ፣ የቅንጅት የለሽ ፍላጎቶች ክስተት ሰለባ ይሆናሉ፡፡

ሥራ ክፍያ ድርድሮች ሳይኖር ማህበረሰብን በመረዳዳት ጠቀሜታ ላይ ማዋቀሩ አዋጭ ነው?

በሀገረ ቻይና የሌይ ፌንግ የሕይወት ታሪክና ሥራዎቹ በሰፊው በናኘበት (በተነገረበት) ዘመን ፣ እያንዳንዱ ሰው ፋታ የለሽ ከሆኑት የሌይ ፌንግ የመጠገኛ መሳሪያዎች መካከል አንደኛው የተሰበሰቡ ሰዎችን ማንቆሪቆሪያዎችና ድስቶች (የማብሰያ ቁሳቁሶች) ሲጠግን ምስሉን በቴሌቪዥን አዘውትሮ ይመለከት ነበር፡፡ እያንዳንዱ ሰው እንዲጠገንለት የሚፈልገውን የተበሳሱና የተሸነቋቆሩ የማብሰያ ዕቃዎቹን ይዞ ከፊት ለፊቱ ረጅም ሰልፍ በመስራት ሲጠባበቅ ይስተዋላል፡፡ በእነዚህ ምሥሎች አማካይነት ለማስተላለፍ የተፈለገው መልዕክት ሕብረተሰቡ የሌይ ሬንግን አርአያነት እንዲመለከትና ቀናነት የተሞላበት የሥራ ጥረቱንም በማየት ሌሎች እንዲከተሉትና ተመሳሳይ ሥራ እንዲሰሩ ለማበረታታት ነበር፡፡ በምስሉ የሚታየው የሰዎች ሠልፉ ረጅም ባይሆን ኖሮ ፕሮፖጋንዳው የማሳመን ኃይል ሊኖረው እንደማይችል ልብ ማለት ያሻል፡፡ ማንቆርቆሪያዎቻቸውንና ድስቶቻቸውን ለማስጠገን እዚያ ተኮልኩለው የነበሩ ሰዎችም ከሌይ ፌንግ ለመማር እዚያ ስፍራ ባልተገኙ እንደነበር ልናጤን ይገባል፡፡ ግና በተፃራሪው ደግሞ ሰዎች በሌሎች ሰዎች ልፋት የራሳቸውን ጥቅም ማግኘት በመሻታቸው እዚየሠ ተገኝተዋል፡፡ የዚህ ዓይነቱ ፕሮፖጋንዳ አንዳንዶች መልካም ስራዎችነ ለሌሎች እንዲሠሩ ማስተማር የሚችል ሲሆን በዚያውም ጎን ለጎን በግል ደረጃ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች ሥራዎች እንዴት ይበልጥ መጠቀም እንደሚችሉ የሚያስተምር ነው፡፡ ባለፉት ዘመናት ይህን መሰሉ ፕሮፓጋንዳ ያለምንም የሥራ ክፍያ ሰዎች ሌሎችን እንዲያገለግሉ በማነሳሳት ማህበረሰባዊ ሞራሎችን ይገነባል ተብሎ ይታሰብ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ይህ አንዳች ዓይነት ግለሰባዊ ጥቅም እንዴት መሻት እንዳለባቸው የሚማሩ ሰዎች ሌሎችን ለማገልገል እንዴት መሥራት እንዳለባቸው ከሚማሩት በቁጥር እጅጉን ለሚበልጡት አብዛኞች በትክክል ትልቅ የአረዳድ ስህተት የሚፈጥርባቸው ነው፡፡
ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ከማግኘት አንፃር ስንመለከት ፣ ሌሎችን ለማገልገል የምንገባው ሁለንተናዊ ግዴታ እርባና የለሽ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ነፃ የጥገና አገልግሎቶችን የማግኘት ሱስ ያደረባቸው ሰዎች ጥቅም የለሽ የተበላሹ ዕቃዎችን ምናልባትም ውዳቂ (የተጣሉ) ዕቃዎችን ሳይቀር ይዘው ይቀርባሉ፡፡ ግና እነዚህን ዕቃዎች ለማስጠገን የሚፈለግባቸው ክፍያ ዜሮ በመሆኑ ምክንያት ዕቃዎች የመጠገኑ ጫና በሌሎች ትከሻ ላይ ስለሚወድቅ ፣ ነፃ ጥገና የሚፈልገው የእያንዳንዱ ሰው አማካይ ወጪ በሰልፉ ጊዜ የሚያባክነው ጊዜ ብቻ ይሆናል፡፡ በጥቅሉ ከማህበረሰባዊ ጠቀሜታ አንፃር ስንመለከት እነዚያን የተበላሹ ዕቃዎች ለመጠገን መስዋዕት የሆነው ጊዜ ፣ ጥረትና ቁሳቁስ ሁሉ የማገልገል ጠቀሜታቸው ከቁብ የማይገባ ማንቆርቆሪያዎችንና የማብሰያ ዕቃዎችን ያስገኘ ነው፡፡ ይልቁንም የባከነው ጊዜና ቁሳቁስ ይበልጥ ምርታማ ለሆኑ ተግባራት ውሎ ቢሆን ኖሮ በእርግጠኝነት ለማህበረሰቡ የላቀ እሴት ይፈጥር ነበር፡፡ ከኢኮኖሚያዊ ብቃትና አጠቃላይ ደህንነት አኳያ ይህ ክፍያ የለሽ ግዴታዊ የጥገና ሥራ ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ይበልጣል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የቀናነት ባሕርይ ያለው የሌይ ፌንግ ተከታይ ደግሞ ነፃ የጥገና አገልግሎት ለማግኘት ማንቆርቆሪያዎቻቸውን ይዘው ከተሰለፉት ሰዎች መካከል ለአንዱ ሰው ወረፋ (ሰልፉ) በመያዝ ያን ድሃ ከአድካሚው ሰልፍ ነፃ ማድረግ ቢችል ደግሞ ዕቃዎቹ እንዲጠገንለት ሰልፉ ይዞ ለሚጠባበቀው ሰው ሰልፉ ይበልጥ ይረዝም ነበር፡፡ በእርግጥ ይህ አንዱ ቡድን ሲሰለፉ ሌላው ከመሰለፉ የሚተርፍበት ቂልነት የሚያሳይ ምልከታ ነው፡፡ የዚህ ዓይነቱ ግዴታዊ ሥርዓት የሚገለገለውን ቡድን ፍቃድ በቅድመ ሁኔታነት ታሳቢ የሚያደርግ ነው፡፡ ምንም ዓይነት የሥራ ክፍያ በማይጠየቅበት በዚህ ዓይነቱ የመረዳዳት አገልግሎት ያለው ሥርዓት የበላይን የሚኮፈሱ ሰዎች ስርዓቱ የሚያስከትለውን ችግር ሙሉ ለሙሉ ማየት የማይችሉ መሆናቸው በግለፅ የሚታወቅ ነው፡፡
የሌሎችን ቁሳቁሶች የመጠገኑ ግዴታ ያልታሰበ ተጨማሪ ክፍያ ይኖረዋል፡፡ ይህም እንደዚህ ዓይነቱ ሥራ በሌይ ፌንግ ተከታዮች መስፋፋት ሲጀምር ከዚያ ቀደም ክፍያ ባለው የቁሳቁስ ጥገና ንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሰዎች ሥራ እየተጣበበ ይሔድና ሰዎቹም ሥራቸውን ያጣሉ ፣ ለችግር ኑሮም ይጋለጣሉ፡፡
ችግረኞችን በመርዳቱ ፣ ለማህበረሰቡ አዎንታዊ ከመሆንዎ አልፎ አስፈላጊ ተግባር በመሆኑ በምንም መንገድ የሌይ ፌንግን ትምህርት አልቃወምም፡፡ ነገር ግን ሌሎችን የማገልገሉ ሥራ ግዴታ የመሆኑ ጥያቄ ትርምስንና ቀውስን ይፈጥራል፡፡ የሌይ ፌንግንም የፈቃደኝነት መንፈስ ያጎድፋል፡፡

በማህበረሰባችን ውስጥ ቀናነት የጎደላቸውና ማህበረሰብን የሚጠሉ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በእነርሱ ግምት ማህበረሰቡ ከምንም በላይ ገንዘብን የሚያስበልጥ ነው፡፡ እንደነርሱ አስተሳሰብ ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ችግር የሚባል ነገር የማይደርስባቸውና ሐብታሞች ራሳቸውን ከቀሪው ማህበረሰብ በላይ እንደሆኑ አድርገው የሚያስቡ ፣ ድሆች ግን ለሰብአዊነት ሥራ ሲሉ የችግር ኑሮ የሚገፉ ናቸው፡፡ ገንዘብ በሰው ልጆች መካከል ለሚኖረው ግንኙነት ከተለመደው ውጭ የተሻለ ነገር አይፈጥርም የሚል እምነት አላቸው፡፡ በዚህም የተነሳ ስለገንዘብና ስለክፍየዎች (money and prices) ከመነጋገር የፀዳና መረዳዳትን መሠረት ያደረገ ማህበረሰብን መፍጠር ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ገበሬዎች ያላንዳች ክፍያ የምግብ ሰብል የሚያመርቱበት ፣ ሠራተኞች ያለምንም ክፍያ ለሁሉም ዜጋ አልባሳት የሚሸምኑበት ፣ ፀጉር አስተካካዮች የሰዎችን ፀጉር በነፃ የሚቆርጡበት ወዘተ ያቀፈ ማህበረሰብ ማለት ነው፡፡ ታዲያ ይህን መሰል ማህበረሰብ በተግባር ዕውን ማድረግ ይቻላልን?
ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ከርዕሰ ጉዳያችን ትንሽ ወጣ በማለት የሐብትን አመዳደብ ኢኮኖሚያዊ ንድፈ ሐሳብን (economic theory of resource allocation) ልንመለከት ይገባል፡፡ ቀለል አድርገን ለማየት ብንሞክር ፣ ሐሳባዊ ከሆነ ሙከራ ልንነሳ እንችላለን፡፡ አንድን ፀጉር አስተካካይ እንውሰድ፡፡ አሁን ባለንበት ወቅት ወንዶች ከሦስት እስከ አራት ሳምንታት ባለው ጊዜ ውስጥ ፀጉራችን አንዴ ይቆረጣሉ፡፡ ይሁንና ፀጉራቸውን የሚቆረጡት ያለክፍየ (በነፃ) ቢሆን ኖሮ ፣ ፀጉራቸውን ለመስተካከል ወደ ፀጉር ቤት የሚሔዱበት በየሳምንቱ ይሆን ነበር፡፡ ለፀጉር ማስተካከል ስራ ገንዘብ ማስከፈሉ ፣ ፀጉር በመቁረጥ ላይ የሚሰማራውን የሰው ኃይል በተሸለ መንገድ መጠቀም ያስችላል፡፡ በገበያ ውስጥ ለፀጉር ማስተካከል አገልግሎቶች የሚፈከፈለው ዋጋ (price) ፣ በሙያ መልኩ ሊሰማራ የሚችለውን በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን የሠራተኞጭ ተሳትፎ (ቁጥር) ይወስናል፡፡ ለፀጉር መቆረጫ የሚከፈለውን የዋጋ መጠን መንግስት ዝቅ እንዲል የሚያደርግ ከሆነ ፣ ፀጉር መቆረጥ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር ይጨምራልና የፀጉር ቆራጮችም ቁጥር መጨመር ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም ያለውን አጠቃላይ የሰው ኃይል የሆነ ቁጥር ላይ ወስነን የተመለከትን ከሆነ ሌሎች ስራዎች ላይ የሚሰማራው የሠራተኛ ቁጥር መቀነሱ ግድ ይላል፡፡ ይህ ፀጉር አስተካካዮችን የተመለከተ እውነታ ፣ በሌሎችም የሥራ መስኮች ላይ የሚሠራ እውነታ ነው፡፡

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.