ሕክምናን ለትርፍና ውስጣዊ ፍላጎት በዶ/ር ቶም ጂ ፓልመር

Imageበዚህ መጣጥፍ ዶ/ር ቶም ጂ ፓልመር ከነበረበት የሕመም ስቃይ ለመገላገል ሕክምና ባደረገበት ወቅት ያገኘውን ተሞክሮ መሠረት በማድረግ ግላዊ ተመስጦውን ያጫውተናል፡፡ ይህ ፅሑፍ እንደ አጠቃላይ አስተምህሮ የቀረበ ወይም እንደ አንድ የማህበራዊ ሳይንስ ለሕትመት የተበረከተ አይደለም፡፡ ይልቁንም በቢዝነስ ድርጅትና በተቆርቋሪነት ስሜት መካከል ያለውን ቁርኝት ለማብራራት የተሠነዘረ ሙከራ ነው፡፡

                  ***

ትርፋማነትን ዓላማ ያደረገ የሕክምና ሥራ አሰቃቂና ሞራል የለሽ ተግባር ተደርጎ ይታያል፡፡ ይህን መሰል ትችትም ዘወትር እሰማለሁ፡፡ በእርግጥ እኔም ይህን እየፃፍኩ ባለሁበት ጊዜ ፣ በግል ሆስፒታሎች ላይ በካናዳ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እየተሰነዘረ ያለውን የመረረ ወቀሳም እየሰማሁኝ ነው፡፡ በርካታ ሰዎችም ሐኪሞች ፣ ነርሶችና የሆስፒታል አስተዳደር ሠራተኞች ስለገቢያቸው ብቻ የሚጨነቁ ከሆነ ፣ ተቆርቋሪነት (ውስጣዊ ርህራሄ) በጭካኔና በራስ ወዳድነት ይተካል ይላሉ፡፡

ከደረሰብኝ ከፍተኛ የሕመም ሥቃይና የአካል ጉዳት ለመገላገል ስል ሁለት ሆስፒታሎችን – አንዱ ለትርፋማነት የሚሰራ ፣ ሌላው ለትርፋማነት ሳይሆን የበጎ አድራጎት ስራ ላይ የተመሰረተ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጥ ሆስፒታል የመጎብነት አጋጣሚ በማግኘቴ ጉዳዩን በተመለከተ አዲስ ሐሳብ አግኝቼያለሁ፡፡

ቅርብ ጊዜ የጀርባ አጥንቴ ዲስክ በመሰበሩ ፣ ጨርሶ ለመግለፅ የሚያዳግት ከፍተኛ የሕመም ስቃይ ውስጥ ነበርኩ፡፡ በአካባቢዬ የሚገኝ ለትርፍ የሚሰራ አንድ ሆስፒታል ሔጄ ከአንድ ልዩ (ስፔሻሊስት) ሐኪም ጋር ተገናኘሁ፡፡ ልዩ ሐኪሙ እዚያ በሚገኝ ለትርፍ የሚሰራ አንድ የጨረር (ራዲዮሎጂ) ክሊኒክ ሔጄ ኤም አር አይ (Magnetic Resonance Imaging, MRI) ስካን እንዳሰራ በአንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ አመቻቸልኝ፡፡ ከዚያም ለሕመም ሥቃዬ ምክንያት የሆነውን እና የሰረሰር አምድ (Spinal Column) ነርቮችን ብግነት መቀነስ የሚያስችል በሰርሰር ሽፋን በኩል በመረፌ የሚሰጥ መድኃኒት እንዳገኝ አመቻቸልኝ፡፡ በእንደዚያ አሰቃቂ የሕመም ስቃይ ሥር ስለነበርኩ ፣ ጨርሶ መንቀሳቀስ እንኳ ተስኞኝ ነበር፡፡ ለትርፍ በሚሰራው ሆስፒታል ስር የሚገኘው ለትርፍ የሚሠራ የሕመም ክሊኒክ ሐኪሞችና ነርሶች በቃላት መግለፅ ከምችለው በላይ እጅግ ርህራሄ በተሞላበት ሁኔታ በጨዋነት የሕክምና እንክብካቤ አድርገውልኛል፡፡ የሕክምናውን ቅደም ተከተልና ሁሉንም መመሪያዎች ነርስዋ ነግራኝ በትክክል መረዳቴን ካረጋገጠች በኃላ ፣ መርፌ የወጋችኝ ሐኪም በቅድሚያ ራስዋን አስተዋወቀችኝ ፣ ከዚያም እያንዳንዱን የሕክምና ቅደም ተከተል ነገረችኝ ፤ ቀጥሎም ሁለቱንም ነገሮች ማለትም ሙያዋ የሚጠይቃትንና ሰብአዊ ርህራሄን አንድነት በማጣመር በሚታይና አስደሳች በሆነ መልክ የሕክምና አገልግሎት ሰጠችኝ፡፡

ጥቂት ሳምንታት አለፉ፡፡ የነበርኩበት የሕመም ስቃይና አቅም ማጣቱ እንደቀጠለ ቢሆንም ያገኘሁት የጤና መሻሻል የሚናቅ አልነበረም፡፡ ጤናዬ ይበልጥ እንዲሻሻልና ወደ ነበርኩበት የጤናማነት ሁኔታ መመለስ እችል ዘንድ ሐኪሜ ቀደም ብዬ በመርፌ የወሰድኩትን መድኃኒት ተጨማሪ እንድወስድ አዘዘልኝ፡፡ አለመታደል ሆነና ቀደም ብዬ መርፌ የተወጋሁበት ለትርፍ የሚሰራው የሕመም ክሊኒክ ለድፍን ሶስት ሳምንታት ያህል በሌሎች ሕሙማን ወረዳ ተያዘ፡፡ ለሶስት ሳምንታት ያህል መጠበቅ ስላልፈለግኩ በአቅራቢያዬ ለሚገኙ ሌሎች ሆስፒታሎች ስልክ ደዋወልኩ፡፡ ባደረግኩት የስልክ ጥሪ በሁለት ቀናት ውስጥ ሊያስተናግደኝ የሚችል በጣሙን የታወቀ በዋነኝነት ለትርፍ የማይሰራ (non-profit) ሆስፒታል አገኘሁ፡፡ ደስ ብሎኝ ቀጠሮ ያዝኩ፡፡                                                                                                                                                                          

ለትርፋማነት ወደ ማይሰራው ሆስፒታል እንደሔድኩ ፣ መጀመሪያ የተነጋገርኩት የበጎ አድራጎት ሠራተኞች መሆናቸውን የሚያመለክት የፀዳ ዩኒፎርም ከለበሱና ለሕሙማን ድጋፍ የሚያደርጉ ጡረተኛ ሴቶችና ወንዶች ጋር ነበር፡፡ ለትርፍ የማይሠራ ሆስፒታል ውስጥ ያሉትን ማንም ሰው መገመት እንደሚችለው ሰዎቹ የበጎ አድራጎት ሠራተኞች መሆናቸው ግልፅ ነው፡፡ ከዚያም በከዘራዬ (መመርኮዣዬ) እየታገዝኩ ወደ ሕመም ክሊኒኩ እየተጎተትኩ በማረፊያ ዴስኩ ተቀመጥኩ፡፡ አንዲት ነርስ ከውስጥ ወጣችና ስሜን ጠራች፡፡ እኔ መሆኔን አሳወቅኩ፡፡ እዚያው ማረፊያ ቦታ መጥታ አጠገቤ ተቀመጠች፡፡ በእንግዶች ተከብቤ ባለሁበት እዚያው ቦታ ቃለ መጠይቅ አደረገችልኝ፡፡ ደግነቱ በሰዎች ፊት ለመመለስ የሚያሳፍር ጥያቄዎችን አልጠየቀችኝም፡፡ ሌሎ ነርሶች ሕሙማንን ትዕዛዛዊ በሆነ ድምፀት ሲያዝዙ አየኋቸው፡፡ አንድዋ ነርስ አንድዋን ሴት ሕመምተኛ (ሴትዮዋ በሕመም ሥቃይ ውስጥ ያለች መሆኑ በግልፅ ይታያል) ከነበረችበት ተነስታ ሌላ ወንበር ላይ እንድትቀመጥ አዘዘቻት፡፡ ሕመምተኛዋም የነበረችበት ቦታ ይበልጥ እንደተመቻት ስትገልጽላት ወደ ሌላ ወንበር ላይ ወንበር እያመለከተቻት “አይቻልም ፣ ከዚያ ጋ ተቀመጭ” አለቻች፡፡ ይህችው ነርስ ወደኔ ስትዞር (ስትቃረብ) ፣ ታዛዥ የት/ቤት ተመዝጋቢ ላይ እንደሚፈፀመው በዚያ መልኩ መስተናገድ እንደማልፈቅድ ገፅታዬ ነገራት፡፡ አንዲት ቃል ሳትተነፍስ በምልክት የምርመራ ክፍሉን አመለከተችኝ፡፡ ገባሁ፡፡

መርፌ የሚወጋኝም ሐኪም ገባ፡፡ ራሱን አላስተዋወቀኝም፡፡ ስሙን አልነገረኝም፡፡ አልጨበጠኝም፡፡ የኔን ፋይል (መዝገብ) አነሳና ከራሱ ጋር ተነጋገረ፡፡ አልጋው ላይ እንድቀመጥ ነገረኝ፡፡ ሙታንታዬን ጎትቶ አወለቀው፡፡ ሸሚዜን ወደ ላይ ሰበሰበው፡፡ ለትርፋማነት በሚሰራው የሕመም ክሊኒክ ሕክምና ሲደረግልኝ በጎኔ ተጋድሜ እንደነበርና አሁንም በጎን መጋደሙ የተሻለ እንደሚመቸኝ ነገር ግን መቀመጡ የህመም ሥቃዬን እንደሚያባብሰው ነገርኩት፡፡ እሱ ደግሞ የኔን መቀመጥ እንደሚመርጥ ነገረኝ፡፡ በጎን መጋደም እንደሚሻለኝ ምላሽ ሰጠሁት፡፡ መቀመጡ ለሕክምናው ሥራ ይበልጥ እንደሚመች መለሰልኝ፡፡ ቢያንስ ይህን ምክንያት መስጠቱ ሁለታችንንም ያስማማናልና ትዕዛዙን በዝምታ ተቀበልኩ፡፡ ከዚያም ለትርፍ ከሚሰራው ሆስፒታል ውስጥ ካከመኝ ሐኪም በታቃራኒ በሚገርምና ከፍተኛ የሕመም ስቃይ በሚፈጥር ሁኔታ መርፌውን በኃይል ሰግስጎብኝ መድኃኒቱን ሰውነቴ ውስጥ ሲጨምረው ሕመሙ አስጮኸኝ፡፡ ቀደም ብዬ በታከምኩበት ሆስፒታል እንደዚያ ያለ ጩኸት አልተከሰተብኝም፡፡ ከዚያም መርፌውን ከላዬ ላይ ነቀለ ፤ ፋይሉ ላይ ማስታወሻ ከፃፈ በኃላ ወጥቶ ሔደ፡፡ ነርሷ ወረቀት ሰጠችኝና ለቅቄ እንድወጣ አመላከተችኝ፡፡ ክፍያ ፈፅሜ ሔድኩ፡፡

Advertisement

One thought on “ሕክምናን ለትርፍና ውስጣዊ ፍላጎት በዶ/ር ቶም ጂ ፓልመር

  1. For-profit Medicine and Compassion Motive has been written by Dr Tom G.Palmer and excerpted from the Morality of Capitalism that has been edited by himself. It is now translated into Amharic language.

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.