ዶ/ር ቶም ፓልመር ከኢንተርፕርነር ጆን ማኬ ጋር ያደረገው ቃለምልልስ (ክፍል 2)

Image

ፓልመር፡ ግለ-ፍላጎትን ከማሳደድ ወይም ትርፍ ከማግኘት በተለየ ቢዝነስ ምን ተጨማሪ ነገር ያስገኛል?

ማኬ፡ በአጠቃላይ አገላለጽ ስኬታማ ቢዝነስ እሴትን ይፈጥራል፡፡ የካፒታሊዝም ድንቅና ዕጹብ ነገር ሙሉ በሙሉ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የጋራ ጥቅም ማስገኛ የልውውጥ ሥርዓት መሆኑ ነው፡፡ የሆል ፉድስ (Whole Foods) ገበያን ቢዝነስ እንደምሳሌ እንውሰድ፡፡ ሸቀጦችን በማቅረብና አገልግሎቶችን በመስጠት ለደንበኞቻችን እሴት ፈጥረናል፡፡ ደንበኞቻችን ከእኛ ጋር መነገድ አያስፈልጋቸውም፡፡ያላስፈለጋቸው ፍላጎታቸው ስለሆነ ነው፡፡ ፍላጎቶቻቸውን በማሟላታችን እሴት ፈጥረንላቸዋል፡፡ ለሰራተኞቻችን እና ለቡድን አባላቶቻችንም እሴት ፈጥረንላቸዋል፡፡ አንዳቸውም የእኛ ባሪያ አይደሉም፡፡ ሥራውን ስለሚፈልጉትና ስለሚወዱት በፈቃደኝነት ይሰራሉ፡፡ የሚያገኙት ክፍያም አመርቂ ነው፡፡  ሆል ፉድስ (Whole Foods) ውስጥ በመስራታቸው በርካታ ጥቅሞችን ያገኛሉ፡፡የገንዘብ እና የስነ ልቦናን ጨምሮ፡፡ እናም እሴት እየፈጠርንላቸው ነው፡፡ ለባለሃብቶችም እሴት እየፈጠርንላቸው ነው፡፡ ምክንያቱም ገበያችን ከአስር ቢሊዮን ዶላር(10.00000000000) በላይ  ደርሷል፡፡ ከባዶ ተነስተን ነው እዚህ የደረስነው፡፡ እናም ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ውስጥ ለኢንቨስተሮቻችን ከከአስር ቢሊዮን ዶላር(10.00000000000) በላይ  እሴት ፈጥረንላቸዋል፡፡ ባለ አክሲዮኖቻችንም አንዳቸውም ሳይገደዱ ነው የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት የሆኑት፡፡ ሁሉም ባላአክሲዮን የሆኑት እሴት ልንፈጥርላቸው እንደምንችል በእኛ ላ እምነት ስለነበራቸው ነው፡፡ ከቢዝነሳችን ጋር የንግድ ግንኙነት ላላቸው አቅራቢዎቻችንም እሴት እየፈጠርንላቸው ነው፡፡ ለዓመታት ስመለከታቸው ቢዝነሳቸው እያደገና እነርሱም እየበለጸጉ ሲሄዱ እንዲሁም ሥራውም በአጠቃላይ በፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ ወደፊት መገስገሱን ነው ያየሁት፡፡እነርሱም  ሆል ፉድስ (Whole Foods) ኩባንያ እንዲያድግ ረድተውናል፡፡ እኛም እነርሱ እንዲያድጉ አስችለናቸዋል፡፡  

ፓልመር፡ የፍልስፍናህ ስያሜ ‘ንቃተ ካፒታሊዝም’( conscious capitalism) የሚል ነው፡፡ንቃተ ካፒታሊዝም ስትል ምን ማለትህ ነው?

ማኬ፡ ይህን ስያሜ የመረጥኩት ብዙ ውዥንብር ከሚፈጥ ሌሎች የቃላት ጋጋታ ለምሳሌ ኮርፖሬት ካለው ማህበራዊ ሃላፊነት (corporate social responsibility) ወይም ቢል ጌትስ ፈጠራዊ ካፒታሊዝም(creative capitalism) በማለት ከሚጠራው ወይም ዘለቂያዊ ካፒታሊዝም(sustainable capitalism) ተብሎ ከሚጠራው ሁሉ ለመለየት ነው፡፡አራት መርሆዎችን መሰረት በማድረግ ‘ንቃተ ካፒታሊዝም’( conscious capitalism) ምን ማለት እንደሆነ በጣም ግልጽ በሆነ መንገድ ማሳረዳት ይቻላል፡፡

የመጀመሪያው መርህ-ቢዝነስ ገንዘብን ማፍራት የሚያስችል ሆኖ ገንዘብ ማፍራቱ ላይ ብቻ ሳይወሰን ከፍተኛ ዓላማን መፍጠር የሚያስችል አቅም ያለው ነው፡፡ እያንዳንዱ ቢዝነስ ለከፍተኛ ዓላማ የሚያበቃ ሃይል አለው፡፡ ይህን አስመልክተን ስናስብ ማህበረሰባችን ውስጥ ያሉት ሌሎች የሙያ ዓይነቶች ሁሉ በዓላማ የተነቃቁ ናቸው-ዓላማ የሚለውን ትርፍ ማሳደግ ነው የሚል ጠባብ ትርጓሜ ከመስጠት ተቆጥበን፡፡ ሐኪሞች በማህበረሰባችን ውስጥ ከፍተኛ ክፍያ ከሚያገኙት መካከል ናቸው፡፡ እናም ሐኪሞች ዓላማ አላቸው፡፡ እሱም በህክምና ት/ቤት የተማሩትን የሙያ ስነ ምግባር በመከተል ሰዎችን ከጤና ችግሮቻችው መፈወስ ነው፡፡ የህን ስንል ታዲያ ሥነ-ምግባር የሚጎድላቸው ስግብግብ ሐኪሞች አይኖሩም ማለታችን አይደለም፡፡ ነገር ግን ቢያንስ የማውቃቸው አብዛኞቹ  ሐኪሞች ለሕመምተኞቻቸው  ጨዋነትን በተላበሰ ሁኔታ እንክብካቤ በማድረግ ከህመሞቻቸው ለመፈወስ ይሞክራሉ፡፡ መምህራን ሰዎችን ለማስተማር ይተጋሉ፡፡አርክቴክቶች ሕንጻዎችን ዲዛይን ያደርጋሉ፡፡ የሕግ ሙያተኞች(ስለ ሕግ ሙያተኞች የሚወሩትን ቀልዶች ጥያቄ ውስጥ ሳናስገባ) የማህበረሰቡ ፍትህ እንዲረጋገጥና የሕግ ውሳኔዎች ፍትሃዊነት እንዲጠበቅ ለማረጋገጥና ለማስተማር ይሠራሉ፡፡ እያንዳንዱ የሙያ መስክ ትርፍን ከማሳደግ ያለፈ ዓላማ አለው፡፡ ቢዝነስም እንዲሁ ነው፡፡ ሆል ፉድስ (Whole Foods) የግሮሰሪ ገበያ በመሆኑ ሰዎች ጤናማ ሕይዎት እንዲኖራቸው እና ረዥም እድሜ እንዲኖሩ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ተፈጥሮኣዊና ከተፈጥሮኣዊ ግብዓቶች የተመረቱ ምግቦችን ለሽያጭ ያቀርብላቸዋል፡፡

 ፓልመር፡ ሁለተኛውስ መርሕ?

ማኬ፡ ሁለተኛው የንቃተ ካፒታሊዝም መርህ የባለድርሻዎች መርህ ነው፡፡ቀደም ብየ በተዘዋዋሪ ተናግሬአለሁ፡፡ እሱም ቢዝነሱ ለተለያዩ ባለድርሻዎች የሚፈጥረውን እሴትና ቢዝነሱ ላይ ጫና ማሳደር ስለሚችሉት ጉዳዬ ባዮች ሁሉ ማሰብ ነው፡፡ ለእነዚህ እርስበርስ በጥቅም ለተሳሰሩት ባለድርሻዎች-ለደንበኞች፣ለሠራተኞች፣ለአቅራቢዎች፣ለኢንቨስተሮችና ለማህበረሰቡ ዝሴት ለመፍጠር ስለሚተጋው ቢዝነስ ውስብስብነት ማሰብ ነው፡፡

ሶስተኛው መርሕ-ቢዝነስ እጅግ በሥነ-ምግባር የታነጹና ለዓላማ ቅድሚያ የሚሰጡ የስራ መሪዎችን ይፈልጋል፡፡ የሥራ መሪዎቹ የባለድርሻ አካላትን መርሕ በመከተል ለቢዝነሱ ዓላማ የሚያገለግሉና የሚጥሩ ይሆናሉ፡፡ስለሆነም እርምጃቸው ሁሉ ስለ ቢዝነስ ጉዳይ ይሆናል ማለት ነው፡፡

አራተኛው የንቃተ ካፒታሊዝም መርህ ዓላማ የባለድርሻ አካላትና የሥራ አመራር ተጣጥመውና ተቀዳጅተው አብረው መጓዝ እንዲችሉ የሚያግዝ ባህል መፍጠር ነው፡፡

ይቀጥላል…

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.