ዶ/ር ቶም ፓልመር ከኢንተርፕርነር ጆን ማኬ ጋር ያደረገው ቃለምልልስ (ክፍል 1)

Imageይህ ቃለ ምልልስ ኢንተርፕርነር ፣የሆል ፉድስ(Whole Foods) መስራች እና ስራ አስፈፃሚ የሆነው ጆን ማኬ ንቃተ ካፒታሊዝም በማለት የሰየመውን ፍልስፍናውን በማብራራት ስለሰዎች ተፈጥሮና መነቃቃት እንዲሁም ስለ ቢዝነስ ባህርይ የነፃ ገበያ ካፒታሊዝም ከ ክሮኒ ካፒታሊዝም(Crony Capitalism) ጋር ስላለው ልዩነት ሃሳቦቹን ያጋራናል፡፡

ጆን ማኬ ከሌሎች አጋሮቹ ጋር በመሆን የሆል ፉድስ(Whole Foods) ገበያን በ1980 ዓ/ም(እኤአ) በመመስረት ስለጤናማ የአመጋገብ ስርዓት ስነምግባርን ስለተከተለ የእንስሳት አያያዝና በማህበረሰብ እድገት ላይ ቢዝነስ ስላለው አዎንታዊ ተሳትፎ በማስተማር እና በተግባር በማሳየት ላይ ይገኛል፡፡

ፓልመር፡ ማኬ አንተ በቢዝነስ ዓለም ብርቅየ ሰው ነህ፡፡ስለካፒታሊዝም ሞራላዊነት በኩራት የምትሟገት ኢንተርፕርነር ነህ፡፡ ግለ-ፍላጎት ብቻውን ለካፒታሊዝም በቂ አይደለም በማለትም ትታወቃለህ፡፡ ይህን ስትል ምን ማለትህ ነው? 

ማኬ፡ እያንዳንዱን ነገር ከግለ ፍላጎት ጋር ማቆራኘት፣ እጅጉን ባልተሟላ ንድፈ ሃሳብ ላይ በመመስረት የሰውን ተፈጥሮ መግለጽ ማለት ነው፡፡ ይህ የሚያስታውሰኝ ምክንያታዊ ሆነህ የምትሰራው እያንዳንዱ ነገር ከግለ-ፍላጎት የመነጨ ነው፤ አለዚያ ግን አትሰራውም በማለት ሃሳባቸውን አሳማኝ ለማድረግ ይጥሩ የነበሩ የኮሎጅ ተከራካሪዎችን ነው፡፡ ይህ አይነቱ አቋም እጅጉን እርባና ቢስ ነው፡፡ ትክክለኛ አለመሆኑንም ለማሳረዳት ያዳግታል፡፡ ምክንያቱም ከግለ ፍላጎትህም ውጭ ያለውን ነገር ብትሰራ እነዚያ ሰዎች ይህንንም ከግለ ፍላጎት የመጣ ነው የሚሉት ባይሆንም አትሰራውም ነው ምክንያታቸው፡፡እናም ይህ አይነቱ የማሳመኛ አካሄድ ቀለበታዊ(እሽክርክሮሻዊ) ድምዳሜ ላይ ያደርሳል፡፡

ፓልመር፡ ከግለ-ፍላጎት ባሻገር ሌሎች መነቃቃቶች ለካፒታሊዝም አስፈላጊነታቸው በምን መልክ ነው?

ማኬ፡ በእውነቱ ይህን ጥያቄ አልወደውም፡፡ ምክንያቱም ግለ-ፍላጎትን በተመለከተ ሰዎች የየራሳቸው ብያኔወች አላቸው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ከሰዎች ጋር ስትነጋገር ብዙዉን ጊዜ በሃሳብ ትተላለፋለህ፡፡ አትግባባም፡፡ ለዚህም ነው እያንዳንዱን ነገር ከግለ ፍላጎት ጋር የሚያቆራኙትን የኮሌጅ ዓይነቱን ውይይት የጠቀስኩት፡፡የሰው ልጆች ውስብስቦች ናቸው ያልኩት ብዙ ማነቃቂያዎች እንዳላቸው ለመግለጽና ከነዚህም ውስጥ ግለ ፍላጎት አንዱ እንደሆነ ነገር ግን ብቸኛው እንዳልሆነ ለመናገር ነው፡፡ እኛ በምናተኩርባቸው በርካታ ነገሮች እንነቃቃለን፡፡ ይህ ግለ-ፍላጎታችንንም ይጨምራል፡፡ የግል-ፍላጎታችን ላይ ብቻ የተገደብን አይደለንም ለማለት ነው፡፡ ግለ-ፍላጎት በአንድ ጎኑ የሊበርታሪያን ንቅናቄን ይመስላል፡፡ከአየን ራንድ እና ከበርካታ ኢኮኖሚስቶች ተጽዕኖ ጭምር የመጣ፡፡ለቢዝነስ ወይም ለካፒታሊዝም ወይም ለሰው ተፈጥሮ ፍትህን የማያመጣ፤ የሞተ ያበቃለት ርዕዮተ ዓለም ዓይነት ነው፡፡

በህይወት ዘመናችን ስለዚህ ጉዳይ ስናስብ ግለ-ፍላጎታችን ላይ እጅግ የተመሰጥንበት ግዜ ቢኖር በወጣትነት እድሜያችንና በስሜት ባላበሰልንበት ግዜ ይሆናል፡፡ ሕፃናትና በጉርምስና እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ አብዛኞቹ ሰዎች እጅጉን በራሳቸው ላይ ያተኮሩ ናቸው ወይም ቅት ባለፈ የራስ ፍቅር እና አድናቆት ውስጥ የወደቁ ናቸው፡፡ድርጊቶቻቸው ሁሉ ከግለ ፍላጎት በሚመነጭ ስሜቶቻቸው የሚታዘዝ ነው፡፡ እያደግንና እየበሰልን ስንሄድ ሌሎችን የመረዳት አቅማችን እየሰፋ ይሄዳል፡፡ የሰው ልጆችን ስሜቶቻቸውን በሰፊው መጋራት እንጀምራለን፡፡ ሰዎች ነገሮችን የሚያከናውኑት በበርካታ ምክንያቶች ነው፡፡ ግለ-ፍላጎት ወይም ራስ ወዳድነት አንዱ ተጠቃሽ ነው፡፡ሌላው ደግሞ ከራስ ፍላጎት ተላቆ ለሌሎች ማሰብ ነው፡፡ይህ የማይነጣጠሉ ነገሮች መነጣጠል(false dichotomy) ነው፡፡ እንደኔ አስተሳሰብ ሁለቱም በውስጣጭን አለ፡፡ የግል ፍላጎት አለን፡፡ ግን ስለሌሎችም እናስባለን፡፡ ብዙውን ጊዜ ስለ ቤተሰቦቻችን እናስባለን፡፡ስለ እንስሳቶች ደህንነት እና ስለምንኖርበት ተፈጥሮኣዊ አካባቢም የምናስብ ነን፡፡ ምድራችን የተሻለች እና ለሰው ልጆች ምቹ እንድትሆን የሚያነቃቃን ሃሳብ ይኖረናል፡፡ እንደ ወግ አጥባቂዎች አመለካከት ከሆነ ይህ ግለ ፍላጎትን የሚቃረን ይመስላል፡፡ አለዚያም የምትሰሩት ሁሉም ነገር ከግለ ፍላጎት የመነጨ ነው ወደሚለው ገደምዳሜያዊ ድምዳሜ ላይ ያደርሳችኋል፡፡

ስለሆነም ግለ ፍላጎት በራሱ በቂ እንዳልሆነ ይሰማኛል፡፡እያንዳንዱ ግለ-ፍላጎታ ድርጊት የሰውን ልጅ ተፈጥሮ የሚገልጽ ጥሩ ንድፈ-ሃሳብ አድርጎ መጥቀሱ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ይልቁንም ካፒታሊዝም እና ቢዝነስ የሰውን ተፈጥሮኣዊ ውስብስብነት በተሟላ መልኩ የሚያንጸባርቁ ይመስለኛል፡፡ ሁለኩን ነገር ከግለ ፍላጎት ጋር ማቆራኘት  የካፒታሊዝም እና የቢዝነስን መልካም ገጽታዎች እጅጉን የሚያደበዝዝ ይመስለኛል፡፡ምክንያቱም የካፒታሊዝምና የቢዝነስ ጠላቶች ካፒታሊዝምን እና ቢዝነስን የራስ ወዳድነት፣የስግብግብነት፣ እና የበዝባዥነት ተምሳሌት አድርገው እንዲስሉ በር ይከፍትላቸዋል፡፡ዕናም ይህ በእውነቱ ያሳስበኛል ፓልመር፡፡ ምክንያቱም ካፒታሊዝም እና ቢዝነስ ለዓለም መልካም ነገሮችን መስራት የሚችል እጅግ ትልቅ ሃይል ነው፡፡ ሰዎች ላለፉት ሶስት መቶ አመታት ካፒታሊዝምን እና ቢዝነስን በተሳሳተ መልኩ ነበር ሲመለከቱት የነበር፡፡ካፒታሊዝም እና ቢዝነስ ላገኘው ድንቅ እሴት ተገቢው ዋጋ አልተሰጠም፡፡

ይቀጥላል…

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.