ጂም ኢሊስ: በደቡባዊ ካፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የማርሻል ት/ቤት ዲን ኢንተርፕርነር እና የዩኒቨርስቲ መምህር

የባንክ ባለሙያ የነበረው አባቱ “ስኬታማ መሆን ከፈለክ በማንኛውም ዓይነት የሥራ ዘርፍ ውስጥ ብትገባ እንኳ ቁጥሮችን በደንብ መረዳት አለብህ!” ይለው እንደነበር ያስታውሳል፡፡ በተጨማሪም “አባቴ ሁልጊዜ ጧት ወደ ሥራ ስትገባ የመጀመሪያው ሰው ሁን ማንም እንዳይቀድምህ፤ስትወጣ ግን የመጀመሪያ መሆን የለብህም፡፡እንዲያውም የጀመርከው ሥራ ካላለቀ በቀር እንዳትወጣ! ይለኝ ነበር፡፡” ብሏል፡፡ ለአባቱ ጆሮ ሳይነፍግ ምክሩን በጥሞና ያደመጠው ጂም በኒው ሜክሲኮ እና በደቡብ ማእከላዊ ሎስአንጀለስ የSears & Roebuck ኩባንያ የብድር ክፍል ሰራተኛ ሆኖ ተቀጥሮ አካውንቲንግና ፋይናንስን በጥልቀት መረዳት ቻለ፡፡ ከዚያም ወደ ማሳቹሴት በማምራት ሁለተኛ ዲግሪውን በቢዝነስ አስተዳደር ትምህርት ከሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ አግኝቷል፡፡በ1970ዓ/ም፡፡

ለጂም ኢንተርፕርነር ማለት ለሥራው ለራሱ እና ለሌሎች ክብር ያለው ሰው ነው፡፡  “እነዚህ ሰዎች ጠንክረው የሚሰሩ፣የሞሉት የቀጠሮ ሰዓት ጧት ሲያንቃጭል ከአልጋቸው ዘለው በመውረድ የራሳቸውን ቀን የሚመሩ እንጂ ሰዓቱ ሲጮህ ኤጭ ነጋ ደሞ፡፡ቆይ ትንሽ ልተኛና እነሳለሁ የሚሉት አይደሉም፡፡” የሚለው ጂም በቢሮ ተቀምጦ በሚያሳልፍባቸው በርካታ ሰዓታት ውስጥ ከትላልቅ የኩባንያ ባለቤቶች ጋር ለመነጋገር የሚያገኘውን አጋጣሚ እና ከጓደኞቹ ጋር የሚይዘውን የእራት ግብዣ ፕሮግራም ሳይቀር ህልሙን ዕውን ለማድረግ ስለቀየሰው መንገድ እንዲሁም መንገዱ ላይ ሊገጥሙኝ ይችላሉ ያላቸውን መሰናክሎች በመግለጽ መፍትሄ ከብዙ አቅጣጫ ከመፈለግ አይሰንፍም ነበር፡፡    

በዚህ ምክንያም የሃርቫርድ ትምህርቱን እንደጨረሰ በተቀጠረበት ‘Broadway Department Stores’ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሥራ እድገት በማግኘት የድርጅቱ ሊቀመንበር እስከመሆን የደረሰ ታታሪ ሰው ነው፡፡

ጂም ኢሊስ የተወለደው በዋሽንግተን ግዛት አሜሪካ ውስጥ ሲሆን፤ በደቡባዊ ካፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የማርሻል ት/ቤት ዲን ሆኖ ከ2007 ዓ/ም ጀምሮ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ ጂም ኢንትራፕርነር(ተቀጣሪ)፣የተሳካለት ኢንተርፕርነር እና የዩኒቨርስቲ መምህር ነው፡፡

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.