ሉላዊነት ባህል እና ስልጣኔ (ኖቤል ሎሬት ማሪዮ ዮሳ) -2

Image

The Culture of Liberty 2-by Mario Vargas Llosa(Nobel Laureate)

ዘመናዊነት በርካታ መልክ ያላቸውን ዘልማዳዊ የአኗኗር ዘይቤዎች ለጥፋት ሊዳርግ እንደሚችል እሙን ነው፡፡ ይሁን እንጅ ለአጠቃላዩ ማሕበረሰብ ወደፊት መራመድ መልካም አጋጣሚዎችንም ይፈጥራል፡፡ ለዚህም ነው ሰዎች የመምረጥ ነጻነት ሲሰጣቸው ያለምንም ማቅማማት መሪዎቻቸው ወይም ምሁራኖቻቸው የሚያዘወትሯቸውን ለመከተልና ለመምረጥ የሚሞክሩት፡፡

ሉላዊነትን ነቅፎ መለያ ባህልን ለመጠበቅ የሚደረግ ዕሰጥ-አገባ እዚህ ግባ የሚባል መሰረት የለውም፡፡ የትኞቹ ባህሎች ናቸው በጊዜ ሂደት ሳይለወጡ ቋሚ ሆነው የቆዩት? እንዲህ ያሉትን ለማግኘት በዋሻ ውስጥ የሚኖሩ ጥንታዊ የጥንቆላ እምነቶችን ተከታይ የሆኑ ኋላቀር ማህበረሰቦችን ወይም መብረቅንና አራዊትን የሚያመልኩ ሰዎችን ማግኘትና ማጥናት ይኖርብናል፡፡ ኋላቀር ከመሆናቸው የተነሳ ያለማቋረጥ ለብዝብዛ ከመዳረጋቸውም በላይ እየከሰሙ መጥተዋል፡፡

አያሌ ዓመታት አልፈው ዘመናዊነትን ለመቀዳጀት የበቁት ሌሎች ባህሎች ሁሉ ከሁለት ወይም ሶስት ትውልዶች በፊት የነበረውን ሁኔታ ያንጸባርቁ እንጅ ይብዛም ይነስ በአንዳች የለውጥ ሂደት ውስጥ ማለፋቸው አይቀርም፡፡ ይህ የለውጥ ሂደት በፈረንሳይ በእስፓኝ እና እንግልጣር(እንግሊዝ) ያለፈበት መንገድ ፈጣን ግልጽና እጅግ ታላቅ በመሆኑ እነ ማሪል ፕሮስት እና ፍሬደሪክ ግራሽያ ሎሪ እና ቨርጂኒያ ዎፍ የተወለዱበትን ዘመን እና ማሕበረሰብ ምን መልክ እንደነበራቸው ዛሬ ላይ ሆኖ ለመረዳት አዳጋች ነው፡፡ ሆኖም እነዚህ የተጠቀሱ ሰዎች ማሕበረሰቡ እንዲታደስ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረጋቸው አይካድም፡፡

ባሕላዊ ማንነት የሚለው ሃሳብ ችግር ፈጣሪ ሃሳብ ነው፡፡ ከማህበራዊ ዕይታ አኳያ እንዲሁ አጠራጣሪና ተፈጥሯዊ ያልሆነ ሃሳብን ይወክላል እንጅ ፖለቲካዊ ገጽታው የሰው ልጅን ውድ የስኬት ደረጃ የሆነውን ነጻነትን የሚወክል ነው፡፡ ተመሳሳይ ቋንቋ የሚናገሩ በተመሳሳይ ሁኔታ የተወለዱና የሚኖሩ ተመሳሳይ ችግሮችን የተጋፈጡ ወይም አንድ ኃይማኖትና ባሕል ያላቸው ሕዝቦች የጋራ ባህሪያት እንደሚኖሯቸው አልክድም፡፡ ይሁንና የጋራ ማንነታቸው ሙሉ በሙሉ እያንዳንዳቸውን ሊገልጽ አይችልም፡፡ይልቁንም አንደኛው የቡድኑ አባል የሌላኛው አንዳንድ ባህሪያት ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዝቅ ያደርጋቸዋል ወይም ከናካቴው ሊያጠፋቸው ይችላል፡፡ የማንነት ጽንሰ ሃሳብ በግለሰብ ደረጃ ካልሆነ በቀር የማህበረሰቡን አባላት ወደ አንድ አነስተኛ ደረጃ የሚያወርድ ሰብዓዊነትን የሚጋፋ የጋርዮሽ ርዕዮተ ዓለማዊ አስተሳሰብ ሲሆን ማናኛውም የሰው ልጅ በግል የሚያደርጋቸው ወጥ ፈጠራዎች ተለይተው እንዳይዎጡ የሚያደርግ የኋላቀሮች ሃሳብ ነው፡፡ ይህ የግለሰብ ነጻነት በዘር ውርስ፣ በመልከዓ ምድራዊ አቀማመጥና በማህበራዊ ጫና የሚመጣ ባለመሆኑ ምክንያት ይህን ነጻነት መለየት በማይቻልበት ደረጃ በአንድ የጋርዮሽ ርዕዮተ-ዓለም ከረጢት ውስጥ ማስቀመጥ የተሻለ ውጤት ማግኘት ትርፉ ድካም ነው፡፡

የጋራ ማንነት ርዕዮተ-ዓለማዊ ልቦለድ ሲሆን የብሄርተኞች መሰረትም ነው፡፡ በርካታ የሰው ዘር አመጣጥና ባህል አጥኝዎች የጋራ ማንነት የጥንታዊውን የጋርዮሽ ማህበረሰብ እንኳ አይወክልም ይላሉ፡፡ የጋራ ባህሎችና ልማዶች በቡድን ወሳን የመከራከሪያ ነጥቦች ቢሆኑም በቡድኑ አባላት መካከል ያለውን ነጻ ለመውጣት የሚደረግ ሂደት ልዩነትን የሚወስኑ የግል ፈጠራና ተነሳሽነት ከፍተኛ ሆኖ ነው የሚታየው፡፡ ግለሰባዊ መለያዎቹ ከጋራ መለያ ይልቅ ጎልተው የሚወጡት እያንዳንዱ ግለሰብ ከጋርዮሽ ማንነቱ ተነጥሎ መታየት ሲችል ነው፡፡ሉላዊነት በዚህ ምድር ላይ ላሉ ህዝቦች ሁሉ ያገራቸውን ባህላዊ ማንነት በግለሰብ ደረጃ በፍቃደኝነትና ፍላጎትን መሰረት ባደረገ መልኩ መመስረት እንዲችሉ ዕድሉን ሰጥቷል፡፡ አሁን አሁን ዜጎች እንደበፊቱ አይነት አስገዳጅ ሁኔታ አፋኝ የሆነ ማንነትን እንዲያከብሩ የሚገደዱበት በቋንቋም በእምነት ተቋሞችና በተወለዱበት አካባቢ ላይ የተመረኮዘ ጫና የለባቸውም፡፡ ከዚህ አኳያ ሉላዊነት የግለሰባዊ ነጻነትን አድማስ የሚያሰፋ በመሆኑ እውቅና ልንሰጠውና ልንቀበለው ግድ የሚለን ጉዳይ ነው፡፡……

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.