ሉላዊነት ባህል እና ስልጣኔ (ኖቤል ሎሬት ማሪዮ ዮሳ)

Image

ሉላዊነትን በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎች በአብዛኛው ኢኮኖሚያዊ ከሆኑ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ አይደለም፡፡ይልቁንም የማህበረሰብ ደንቦችና ባህል ነክ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች በተደረጉ ውይይቶች ጎልተው ከወጡት መከራከሪያዎች ውስጥ እንዲህ የሚል ይገኝበታል፡፡

“የብሄራዊ ድንበሮች መጥፋትና ዓለም በአንድ የገበያ ትስስር በተያዘች ቁጥር  የነዚህ ሀገሮች መለያ የሆኑ ባህሎች ቅርሶች ልማድ እና ወጎች ለጥፋት የተጋለጡ ይሆናሉ፡፡በአብዛኛው ያደጉ አገራት ውስጥ የአሜሪካን ባህል እንደ ዋና መመዘኛና መለኪያ በመወሰዱ የራሳቸውን ነባር ባህል ለማጣት ተገደዋል፡፡በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢምፔሪያሊዝም ይህን የህዝቦች ማንነት እና መንፈሳዊ ወኔ ከማሳጣት ባሻገር ዓለምን በካፒታል በወታደራዊ ሃያልነትና በሳንሳዊ እውቀት በመምራት ቋንቋውን እና እምነቱን በመጫን ላይ ነው፡፡”

ለሉላዊነት ምስጋና ይግባውና እንዲህ አይነቱ  መከራከሪያ የነ ማርክስ ማኦ ወይም ቼጉቬራ ዓይነት የግራ ዘመም ፖለቲካን የሚያቀነቅኑ ቡድኖች ቅዠት ሆኖ ቀርቷል፡፡ እንዲህ ያለው የጥላቻ ዘመቻ በሰሜን አሜሪካዋ ታላቅ ሃገር ላይ ብቻ ያነጣጠረ  ሳይሆን በስልጣኔ ስነ ቋንቋ እና የባህል ብዝሃነት ላይ የሚቃጣ ድርጊት ነው፡፡

እነ ሞንቴኝ ዲካርቴን ራሴንና በዴለርን ያፈራ ምድር ብቻ ሳይሆን ለረዥም ዘመናት የዓለም የፋሽን አልባሳት እና የአዳዲስ እሳቤ የጥበብ ምንጭ ሆና የዘለቀችው ፈረንሳይ በማክዶናልድ፣፣ ፒዛ ሀት ፣ በኬንቲክ ቺክን ፣ በሮክ፣ እና በራፕ የሆሊውድ ፊልሞች በሰማያዊ ጅንስ ስኒከሮች እና ቲሸርቶች እንዳትጥለቀለቅ እንዲሁም የፈረንሳይን ባህል ከሉላዊነት ተጽዕኖ ለመታደግ በሚል አስገራሚና ሰፋ ያለ እንቅስቃሴ ያደረገው የፈረንሳይ መንግስት ዘመቻ የፈረንሳይ ብሄራዊ የፊልም ኢንዱስትሪን ከመደጎም ቲያትር ቤቶችም ከአሜሪካ የሚያስገቧቸውን ፊልሞች ቁጥር እንዲቀንሱ ወይም ኮታ እንዲጠቀሙ ከማድረግ አልፎ ምሁራንና ፖለቲከኞች ለህዝቡ በሚያደርጉት ንግግር ውስጥ እንግሊዝኛ ቋንቋን እንዳይቀላቅሉ ትዕዛዝ እስከማስተላለፍ ደርሷል፡፡ ለነገሩ ትእዛዝም ባይኖር ቋንቋን ለሚበርዙ ሰዎች ፈረንሳዊን ክብር በመንፈግ ይታወቃሉ፡፡

ከሉላዊነት በተቃራኒ የሚደረግ ባህል ነክ ሙግት ተቀባይነት እንደማይኖረው ባምንም ጠለቅ ብለን መመልከት ብንችል በውስጡ የማያወላዳ እውነት ሊኖር እንደሚችልመበንዘብ እንችላለን፡፡የምንኖርበት ዓለም በተለይ ይህ ምዕተ ዓመት ካለፉት ጊዜያት ጋር ሲነጻጸር  አካባቢያዊ በሆኑ ባህላዊ ቀለሞች የማሸብረቁ ነገር እየቀነሰ መጥቷል፡፡ከዚህ ቀደም የነበሩ ፌስቲቫሎች አልባሳትና ልማዶች ክብረ በዓላት ባህልና ዕምነቶች የሰው ልጅን ማንነትና መለያውን በግልጽ ያስቀመጡ የነበሩ ቢሆንም አሁን አሁን አብዛኛው የዓለም ክፍል እየተዋቸውና ከዘመኑ ጋር በሚሄድ ሌላ ባህል እየተካቸው ይገኛል፡፡ ምናልባት ጊዜው ሊረዝም ይችል ይሆናል እንጅ ይህ ሁኔታ የማያጋጥመው የዓለማችን ክፍል አይኖርም፡፡ ይሁንና ይህ የሚሆነው ሉላዊነት ከዘመናዊነት ጋር ሲሄድ ብቻ ነው፡፡በርግጥ አሁን ባለንበት ምቹ ሁኔታ ላይ ቆመን ያለፈውን ደስታ የተሞላበት እና በቀለማት ያሸበረቀ ወቅት ወደኋላ ዞር ብለን ብንመለከት የሃዘን ስሜት ሊሰማን ይችላል፡፡ሆኖም ግን ይህን የማይቀር የለውጥ ሂደት ማንም ሊያስቀር አይቻለውም፡፡

እንደ ኩባ እና ሰሜን ኮሪያ ያሉ አፋኝ መንግስታት ማንኛውም የሚፈጥሩት ክፍተት ሊያጠፋቸው እንደሚችል በመስጋት በሮቻቸውን ዘግተው ከዘመናዊነት ራሳቸውን አግልለው ቢቆዩም ቀስ እያለ ሰርጎ የገባውን የሉላዊነት ተጽዕኖ ግን መቋቋም ተስኗቸዋል፡፡

እንዲህ ከተጽዕኖ ውጭ ባህላዊ ማንነት ሳይነካ ለመቆየት አፍሪካና አማዞን የተሻሉ አካባቢዎች ቢሆኑም ሙሉ ለሙሉ ስኬታማ የሚሆነው ግን ከሌሎች ጋር ያለውን ማናቸውንም ልውውጦች በማቋረጥ ራሳቸውን ችለው ሲገኙ ብቻ ይሆናል፡፡ በዚህ ረገድ ስኬታማ ቢሆኑም ማህበረሰቡንና አካባቢውን ‘ማንነቴ’ ከሚሉት ባህላቸው ጋር ቁልቁል ይወርዳሉ የአኗኗር ዘይቤያቸው እንደምኞታቸው ፈጽሞ ሊሆን አይችልም፡፡

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.