ክፍል 5- ሁሉን የሚያውቅ አእምሮ የለም (እኔ እርሳስ-በሊኦናርድ ሪድ)

Image(በቲ ንቅናቄ) አሁንም ይበልጥ አስደናቂ እውነታ አለ – እኔን ወደ ህልውና ለማምጣት እነዚህን ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሥራዎች መምራት ወይም ተቆጣጥሮ ማስፈጸም የሚችል ሁሉን-አወቅ አእምሮ ያለው አንድም ሰው አይገኝም፡፡የዚህ አይነት ሰው ይኖራል ብላችሁ ብትኳትኑ ጨርሶ አታገኙም፡፡ይልቅ የማይታየው ስውር እጅ (Invisible hand) ሥራን ያከናውናል፡፡ ቀደም ብየ እንቆቅልሽ እሆናለሁ በማለት ያመላከትኩት ይህንን ነው፡፡

ዛፍን የሚፈጥር እግዚአብሄር ብቻ ነው ይባላል፡፡ ለምንድን ነው በዚህ ሀሳብ የምንስማማው? እኛ ራሳችን አንዲት ዛፍ መፍጠር እንደማንችል ስለምንገነዘብ አይደለምን? ሌላው ቀርቶ ዛፍን በአግባቡ መግለጽ እንችላለን? ላይ ላዩን ካልሆነ በቀር ጨርሶ አንችልም፡፡ለምሳሌ የሆኑ ሞልክዩላዊ ቅንብሮሾች በመጥቀስ የዛፍ መገለጫ ይህ ነው ልንል እንችላለን፡፡ እስቲ በትንሹ የትኛው የሰው አእምሮ ነው በአንድ ዛፍ የህይወት ዘመን ውስጥ የሚካሄደውን እያንዳንዱን ሞልክዩላዊ ለውጥ መዘገብ የሚችለው? ሊታሰብ እና ፈጽሞ ሊሆን የማይችል ነገር ነው፡፡

‘እኔ  እርሳስ’  የውስብስብ ተአምራቶች ቅንብሮሽ ነኝ፡፡   የዛፍ፤የዚንክ፤የመዳብ፤የግራፋይት እና የሌሎችም፡፡ ከነዚህ በተፈጥሮ ከሚገኝ ተአምራቶች በተጨማሪ የሚታከል እጅግ ልዩ ተአምር አለ – ይሄውም የሰው ልጅ መስተሃይላዊ የፈጠራ ብቃት (creative human energies) ነው፡፡ ይህ የሰው ልጅ አይምሮኣዊ ብቃት በተፈጥሮኣዊ እና በራስ አካሄድ በሚሊዮን ከሚቆጠሩ የማይተዋወቁ፣ የተራራቁ ብሎም በጠላትነት የሚፈላለጉ አገራት ሳይቀሩ ለሰው ልጅ መሠረታዊ ነገሮች እና ፍላጎቶች ምላሽ ለመስጠት በያሉበት ‘እኔን እርሳስን’ ለመፍጠር ያላቸውን ጥቃቅን ነገር ያበረክታሉ፡፡ ለሰው ልጅ ዛፍን የሚፈጥረው እግዚአብሄር ብቻ በመሆኑ እኔንም የሚፈጥረኝ እግዚአብሄር ብቻ እንደሆነ አጥብቄ እናገራለሁ፡፡ ሰው ሞለክዩሎችን አቀናብሮ ዛፍ መፍጠር እንደማይችለው እኔንም እንዲሁ እነዚህን በሚሊዮን የሚቆጠሩ እውቀቶችን በማቀናጀት ወደ ህላዌነት ሊያመጣኝ አይችልም፡፡ እላይ በጽሁፌ ‹‹እኔ በተአምራዊነቴ የምወክለውን ተምሳሌት መገንዘብ ከቻላችሁ የሰው ልጅ በመከፋት እያጣ ያለውን ነጻነቱን እንዲታደግ ልትረዱት ትችላላቸሁ›› በማለት የገለጽኩት ይህንኑ ነው፡፡ ሰው እነዚህን ጥቃቅን እውቀቶች በተፈጥሮአዊ አካሄድ መጓዝ እንዳለባቸው ከተገነዘበ ጥቃቅኖቹ እውቀቶች አውቶማቲክ በሆነ አኳኀን ራሳቸውን ወደ ፈጠራዊ እና ምርታማዊ መልክ በመቀነባበር ለሰው ልጅ መሰረታዊ ነገሮችና ፍላጎቶች ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ይህ የሚሆነው ከመንግስትም ሆነ ከሁሉን-አውቃለሁ ባይ ምንም አይነት ጫና ያልተደረገበት እንደሆነ ነዉ፡፡ ያኔ እያንዳንዱ ሰው ለነጻነቱ ፍጹም መሰረታዊ የሆነ ቅመም ያገኛል-በነጻ ማህበረሰብ አስፈላጊነት እምነት ይኖረዋል፡፡ ነጻነት ያለዚህ እምነት ፈጽሞ የማይቻል ነዉ፡፡

መንግስት የፈጠራ ስራዎችን በምኖፖል በያዘበት ሁኔታዎች ውስጥ ለምሳሌ ፖስታ ማደልን(ማድረስን)፣ነጻ ሰዎች የፖስታ ማደልን ስራ እነዲያከናውኑ ቢደረግ አብዛኛኞቹ ሰዎች ፖስታዉን በብቃት ማደል አይችሉም የሚል እምነት ያድርባቸዋል፡፡

ምክንያቱ ደግሞ እያንዳንዱ ሰው ራሱ ከፖስታ ማደል ጋር የተያያዙት ስራዎች እንዴት መስራት እንደሚችል አለማወቁን በጸጋ ስለሚቀበል ነው፡፡ይህንን ስራ ሌላ ማንም ሰው ሊሰራው እንደማይችልም ይገነዘባል፡፡ እነዚህ ይሆናሉ ብየ ያስቀመጥኳቸው ሃሳቦች (assumptions) በትክክል የሚሰሩ ናቸው፡፡አንድም ሰው እርሳስን መፍጠር የሚያስችል በቂ እዉቀት የለውም፡፡እንዲሁ ሁሉ አንድም ሰው የአንድ አገር ፖስታ የማደል ስራ ማከናዎን የሚያስችል በቂ እውቀት ሊኖረው አይችልም፡፡ በነጻ ማህበረሰብ የማመን እምነት ባልኖርበት እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጥቃቅን እዉቀቶች በተፈጥሮኣዊና በተአምራዊ አኳኋን በመቀናጀት ለመሰረታዊ ፍላጎቶች ምላሽ መስጠት መቻላቸዉ ግንዛቤ በሌለበት ሁኔታ ግለሰብ ለነጻነት እገዛ ማድረጉ ቀርቶ ፖስታ ማድረስ የሚችለው ‹‹ሁሉን-አዋቂ›› የሆነው መንግስት ብቻ ነዉ የሚል የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ ይደርሳል፡፡

ይህን ጽሁፍ በቀጥታ እንዲደርስዎት ከፈለጉ የፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ከዚያ በተጨማሪ ለሚያውቁት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪ እንዲሁ እንዲደርጉ ይንገሩልን፡፡ የኛ ፕሮጀክት ባብዛኛው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ማዕከል ያደረገ ሲሆን ተማሪዎችን ያሰለጥናል፣ የተለያዩ ሽልማት የሚያስገኙ ውድድሮችን ያካሂዳል፡፡ ውድድሩ በብሎጋችን እና በፌስ ቡክ ገጻችን ከሚወጡ ጽሁፎችን በመንተራስ የሚካሄድ ሲሆን ፤ የቲ ንቅናቄን ዓላማ ከግብ ለማድረስ በማሰብ የተዘጋጀ ነው፡፡ ውድድሩ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ይካሄዳል፡፡

የፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ፡ www.facebook.com/teamuvement

ስለትብብርዎ እናመሰግናለን፡፡

TEA Movement is proud producing and translating articles that promotes the foundations of a free society, economics of liberty, and entrepreneurship. You can get them on our blogs on our face www.tmuv.wordpress.com , by liking our face book page፡ www.facebook.com/teamuvement , and by following us on twitter:  www.twitter.com/TeaMovement1

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.