ኢንተርፕርነር ዳን ጌለር-የGeller/Goldfine Productions & Storyline Productions ፕሬዚዳንት

Image

ወደፊት የምትሰማራበትን የስራ መስክ ከልጅነትህ ምኞትና ካሣለፍከው ሕይዎት ጋር እንደሚያያዝ የተለያዩ የሥራ ዓይነቶችን የሚያጠኑ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ሶስት የኤሚ/Emmy ሽልማቶችን ጨምሮ ከሃያ በላይ የሚሆኑ ለፊልም ስራዎች የሚሰጡ ሽልማቶችን ለማግኘት የታደለው ዳንም እንደባለሙያዎቹ አስተያየት የሱም የጀርባ ታሪክ አሁን ላገኘው ስኬት ቁልፍ ሚና ተጫውቷል፡፡ዳን የተወለደው ዮንከርስ/ኒውዮርክ ውስጥ በአሜሪካ ሃገር ነው፡፡

በልጅነቱ ለህጻናት ልደት ይሆን ዘንድ አጫጭር  ፊልሞችን አስማተኛ በመምሰል ይሰራ የነበረው ዳን አስተማሪ የነበሩት አባቱ በሚያስተምሩበት አንድ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ሆኖ በመግባቱ ፊልም ለመስራት የነበረውን አምሮት ሊቆርጥ ችሏል፡፡

ዳን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ኮርኔል ዩኒቨርስቲ ገብቷል፡፡ዳን በኮርኔል ዩኒቨርሲቲ ስር ተማሪዎች የሚያንቀሳቅሱት ሬዲዮ ጣቢያ ውስጥ ጋዜጠኛ ኋላ ላይም የጣቢያው አስተዳዳሪ ሆኖ ሠርቷል፡፡ ዳን እንደሚለው “በዚህ ወቅት በ1979ዓ/ም ማለቴ ነው ወደ አምስት መቶ ሺሕ ዶላር በጀት ከአንድ መቶ በላይ ጊዜያዊና ጥቂት ቋሚ ሰራተኞች ጋር አስተዳድር ነበር፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ የአመራር ቦታ ይዤ መቆየት እንዳልነበረብኝ ተረዳሁ፡፡” ይላል፡፡

ከመመረቁ በፊት የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቱን ለመቀጠል ይረዱኛል ያላቸውን መረጃዎች ከተለያዩ የቢዝነስ ት/ቤቶች የሰበሰበው ዳን በ1982 ሲመረቅ ሰብስቦት የነበረውን መረጃ ሁሉ ጥሎ አቅጣጫውን በመቀየር የሁለተኛ ዲግሪውን በዶክመንታሪ ፊልም አሰራር ጥበብ ከስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ለማግኘት ችሏል፡፡ ዳን እንደተመረቀ ማስታወቂያ የሚሠራና አጫጭር ስልጠና የሚሰጥ የቪዲዮ ኩባንያ ሲልኮን ቫሊ ካሊፎርኒያ ውስጥ ከፈተ፡፡

ዳን በአፍላ እድሜው ቤተሰቡ እራት ሲመገብ ያደርግ ከነበረው ምክክር የቀሰመው ትምሕርት አሁን ሥራ ላይ ለሚገጥመው መሰናክል አይበገሬ እንዳደረገው ይናገራል፡፡

“እኔ ብዙ ነገሮችን ነው ከቤተሰቤ የተማርኩት፡፡በተለይ ሥራ በምትጀምርበት ወቅት የሚገጥምህን ተስፋ አስቆራጭ የሚባሉ እንቅፋቶችና እዚህ ግባ የማይባል ገቢ ምን ያህል የብዙዎችን ቅስም እንደሚሰብር ያኔ ነው የተረዳሁት-ከቤተሰቤ የራት ላይ ማዕድ ወግ፡፡ስለዚህ ህልሜን እውን ለማድረግ በእንዲህ ያለ ምክንያት ከመሰናከል ይልቅ ወደ ፊት መግፋት እንዳለብኝ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ጥሩ ሆኖ መገኘትም ለተሻለ ስኬት እንደሚያበቃ የተማርኩት ትምህርት ቤት ውስጥ አይደለም፡፡”

“በተፈጥሮዬ አንድን ነገር ለተወሰነ ጊዜ በጥሩ ጎኑ የመመልከት ባህሪ አለብኝ፡፡በዚህ የራሴ ሕገመንግሥት እድለኛ ነኝ ነው የምለው፡፡ምክንያቱም ብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በአስቸጋሪነታቸው ውስጥ ለማለፍ አስችሎኛል፡፡ ምክንያቱም ከዚያ ተቃርኖ ባህሪየ ስመለስ ስጋቴን ሁሉ ለቤተሰቤና ለጓደኞቼ በማማከር ችግር መፍቻ ዘዴና ብልሃት ስለማገኝ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለማለፍ ችግርን መጋፈጥ እንዳልፈራ ሆኜ ስለታነጽኩ ነው፡፡”

ዳን የፈጠራ ችሎታውን ይበልጥ ያሳየው ‘ከነፍስ/ከልብ መንቀሳቀስ’ በተባለው የመጀመሪያ ፊልሙ ሲሆን በ1989ዓ/ም ላይ ቀርቦ ቀዳሚ የሆነው በዚያው ዓመት ከሳንፍራንሲስኮ ዓለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫል ላይ በመቅረብም የ golden gate award ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ዳን “ኢንተርፕርነር ማለት ተስፋ የሚያደርግ ሰው ነው ይላል፡፡ያ ተስፋ ደግሞ በውስጡ ካለው ፍላጎት የሚመነጭ ነው፡፡  ይሄ ምንጭ እየጎለበተ ሲሄድ ተነሳሽነትን በልቡ ያሰርጽና ዕውን ማድረግ ወደሚፈልገው ነገር ይገፋፋዋል፡፡ይህ ብቻውን ለስኬት ቁልፍ ነገር ነው እያልኩ አይደለም፡፡ ሆኖም  ህልሙ እንዲያብብ ግን ወደዚያ መጠጋት ስላለበት ነው መጀመሪያ፤ከዚያ ጥሩ ውጤት እየጠበቅህ ሥራህን ጀምር፡፡አየህ ስትጀምር ያሰብከው ነገር ውስጥህ የኖረ ስለሆነ ታውቀዋለህ፡፡ሆኖም ስለምታውቀው የምትጠብቀው ጥሩ ውጤት ይመጣል ማለት አይደለም፡፡እንዲያም ከሆነ ግን ተቀበለው፡፡” የሚለው ዳን እራሱ ባለ ተስፋ ነው፡፡

“ከተስፋ ጋር ለስራው የሚገባውን ያህል ላብ ማፍሰስ እንዳለብኝ ግን አልዘነጋም፡፡ያ ይመስለኛል እኔና ፊልሞቼን ተመራጭና ተሸላሚ ያደረገን፡፡”

ከባለቤቱ፣ከቢዝነስ አጋሩና ከፈጠራ ተጓዳኙ ዳይና ጎልድፋይን ጋር የሚሰሯቸው ፊልሞች ውስጥ የሚካተቱት ሰዎች “ሥራቸውን  ከልብ የሚወዱና ስለዚያም የሚኖሩ” ይላቸዋል-ዳን፡፡

“ጀማሪ የዩኒቨርስቲ ተማሪም ሆነ አዲስ (ስራ ጀማሪ) ኢንተርፕርነር ሁለቱም ባለተስፋና ስለሚያደርጉት ነገር ውስጣዊ ፍላጎት ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡ለዚያ ነው የምንሰራቸው ፊልሞች ሁሉ በተወሰነ መልኩ እውነተኛ ታሪክ እና የሁነቱን ትክክለኛ ወቅት የምንጠቅሰው፡፡ አየህ ይህ ነው የሌሎች ሰዎችን ትኩረት እንዲያገኝ ያደረገው፡፡” ዳን ይቀጥልና “የኛ ፊልሞች እየጠነከሩ የሚሄዱ ዓይነት ናቸው፡፡እኔ ስለሰዎች ታሪክ በተለይም በስራቸው ከገጠማቸው ችግር  ጋር ተናንቀው የሚገኙ ወይም በራሳቸው ስህተት ቢዝነሳቸው አደጋ ላይ የወደቀ  ኢንተርፕርነሮችን ፈልጌ እጽፋቼዋለሁ፡፡እነሱ ለማለፍ ያደረጉትንና እያደረጉት ያለውን ጥረት ስመለከት ተስፋ ዋነኛው ድል ማድረጊያቼው እንደሆነ ነው የተገነዘብኩት፡፡ እነዚህ ሰዎች ከማንም ምንም የገንዘብ ድጋፍ ሳናገኝና ዓመታትን ወስደው ለሚያልቁት ፊልሞቻችን ዕውን መሆን እኛንም የተስፋ ስንቅ አሳዝለው ያነቃቁናል፡፡”ይላል ዳን፡፡

ዳን ስለስራው እና በስራው በርካት ሽልማትን የተቀበለ ሲሆን ከነዚህ መሃል ጎልደን ጌት አዋርድ/Golden Gate Award ለ ISODORA በ1994ዓ/ም Outstanding Directorial Achievement ከ Academy of Motion Picture Arts & Science ለ FROSH እንዲሁም በ 1999 ዓ/ም በርካታ የEmmy ሽልማትን BALLETS RUSSES ለተሰኘው ፊልሙ ተቀብሏል፡፡ ታይም መጽሄት/Time Magazine the Los Angeles Times,The Hollywood Reporter,The Sanfrancisco Croncle & State የተባሉት የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት በ2005 ዓ/ም በምድረ አሜሪካ ከሚገኙ ምርጥ አስር ፊልሞች መሃል አንዱ አድርገውት ነበር፡፡

ዳን ጊለር ሲበዛ ተስፈኛ ነው፡፡የማስተርስ ዲግሪውን በቢዝነስ የትምህርት መስክ ለመማር በማሰብ የሰበሰባቸውን መረጃዎች ሁሉ ላሰበው አላማ ሳይጠቀምባቸው የበታተናቸው ህልሙን ዕውን ለማድረግ በሰነቀው ተስፋ እንጅ ገንዘብ አግኝቶ አልነበረም፡፡ዳን እራሱ ከካሜራው ጀርባ ስላለው ስኬታማ ሥራው የሚከተለውን ለሁላችንም ይነግረናል፡፡ ከእኔ ጋር በዚያው ተለያየን፡፡

“ይህ የምሠራው ሥራ ተነሳሽነትን የሚያጭረው ፊልሙን ሠርተን ታሪኩን የምንነግረውን ተመልካች ብቻ አይደለም፡፡ይህ ሙሉ ለሙሉ ያልተጠበቀ ክስተትና አንተም ሊገጥምህ የሚችል እውነት ነው፡፡ እኔን ከፍም ዝቅም እያደረገ በጎ አሳቢ እና አዎ..አዎ..አዎ! ባይ ቅን ሰው ያደረገኝ፡፡”

 

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.