(በቲ ንቅናቄ) ቀደም ብየ እኔ እንዴት እንደተሰራሁ ሊያውቅ የሚችል ሰዉ በዚህ ምድር ላይ ቢፈልግ አንድም ሊገኝ አይችልም በማለት ያስቀመጥኩትን ሀሳቤን በመቃዎም ሊሞግተኝ የሚችል ማን አለ?
እርግጥ ነዉ በእኔ አፈጣጠር ዉስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠር የሰዉ ልጅ እጆች አለ፡፡ከእነዚህም ሰዎች መካከል ከጥቂት በስተቀር አንዱ ሌሎችን አያውቅም፡፡ይበልጥ መግለጽ ካስፈለገኝ ደግሞ የብራዚል ቡና ለቃሚዎች ድረስ በመራቅና በተለያዩ ስፍራዎች የምግብ ሰብል አምራቾችን ከፍጥረቴ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው መናገር እችላለሁ፡፡ በዚህ አቋሜ የጸናሁ ነኝ፡፡ ከእነዚህ ሚሊዮኖች መካከል የእርሳስ ካምፓኒውን ፕሬዝዳንት ጨምሮ አንድም ግለሰብ ስለ እኔ አሰራር ከቅንጣት ያለፈ እዉቀት ያለውና ከዚህ እዉቀቱ የዘለለ አስተዋጽኦ ያበረከተ አይገኝም፡፡ከእዉቀት አንጻር ስንመለከት በሴይሎን የማእድን አውጭ ሰራተኛና በኦሪጎኑ የእንጨት ሰራተኛ መካከል ያለዉ ልዩነት የሙያቸው አይነት መለያየት ብቻ ነው፡፡የማእድን ሰራተኛውንም ሆነ የእንጨት ሰራተኛውን፣ከፋብሪካው ኬሚስት ወይም ፓራፊንን (የፔትሮሊየም ተረፈ ምርት) ከሚያመርተው የነዳጅ ዘይት አምራች ሰራተኛ የበለጠ ሊያስመሰግነው የሚገባ ነገር አይኖርም፡፡
እነሆ የሚያስደንቅ እውነታ-የነዳጅ ዘይት አምራች ሰራተኛውም ይሁን ኬሚስቱ፣የግራፋይት ማእድን ወይም ሸክላ አፈር ቆፋሪውም ይሁን ባቡሮችን ወይም መርከቦችን ወይም የጭነት መኪኖች የሚያመርቱ ሰራተኞች፣በመናኛ ብረቴ ላይ ክርክር ለማበጀት ማሽን የሚያነቀሳቅሰው ሰራተኛም ይሁን የእርሳስ ማምረቻ ካምፓኒው ፕሬዝዳንት ሁሉም የየራሱን የስራ ድርሻ የሚያከናውነው እኔን ስለፈለገኝ አይደለም፡፡ ምናልባትም እያንዳንዳቸው ለእኔ የሚኖራቸው ፍላጎት አንድ የአንደኛ ክፍል ህጻን ከሚፈልገኝ በታች ነዉ፡፡በእርግጥ ከእነዚህ የትየለሌ ሰዎች መካከል እኔን (እርሳስ) አይቶ የማያዉቅ ብዙ አለ ወይም በእኔ እንዴት መጠቀም እንደሚችል የማያዉቅ ይኖራል፡፡ የእነዚህን ሰዎች መነቃቃት ከእኔ ውጪ ላለ ነገር ነዉ፡፡ ምናልባት እንዲህ ሊሆን ይችላል-እነዚህ ሚሊዮኖች እያንዳንዳቸው ያላቸውን ቁንጽል(ትንሽ) እዉቀት ከሚፈልጉት ወይም የሚያስፈልጋቸውን ሸቀጦች እና አገልግሎቶች በልውውጥ መልክ ማግኘት እንደሚችሉ ይገነዘባሉ፡፡ እኔ ደግሞ ከእነዚህ እቃዎች መካከል ልኖርም ላልኖርም እችላለሁ፡፡
ይቀጥላል…
ጽሁፎቹን በቀጥታ ለማግኘት የፌስ ቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ፡ https://www.facebook.com/teamuvement
በትዊተር ይከተሉን፡ https://twitter.com/TeaMovement1
ብሎጋችንን ይጎብኙ፡https://tmuv.wordpress.com
በቅድሚያ ግን ስላነበቡን ማመስገን እንወዳለን፡፡