ዶ/ር ሮቤርቶ ብሪንቶን፡- በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የመድሀኒት ቅመማ ጥናት ተመራማሪ እና ኢንተርፕርነር

Image“ይህን ማድረግ ይቻላል፡፡ ይሄን ማድረግ ሊከብድ ቢችልም መሞከር ይኖርብናል፡፡እንዲሁም ይህን ማድረግ አለብን፡፡” የሚሉትን ኮርኳሪ የቤተሰቦቿን መርሆዎች ይዛ ያደገችው ሮቤርታ ብሪንቶን ኒው ጀርሲ አሜሪካ ውስጥ ነው የተወለደችው፡፡

ቤተሰቦቿ እዚህ ግባ የሚባል የገቢ ምንጭ ስላልነበራቸው ኮሌጅ ለመግባት የነበራት ህልም ለጊዜው ሲጨነግፍ አንድ አነስተኛ የላብራቶሪ ቴክኖሎጂ ሙያ ማሰልጠኛ ለመግባት ተገደደች፡፡እ.ኤ.አ በ1969ዓ.ም ህይወቷን ከዚህ ማሰልጠኛ በቀሰመችው ትምህርትና ልምድ ለመቃኘት ብዙ ጊዜ አልፈጀባትም፡፡

በርካታ ተመራማሪዎች በየምርምር ማእከሉ ጥግ ይዘው እንቅልፍ ያጡበት አልዚህመር (Alzheimer) የተባለው የመዘንጋት በሽታ የሮቤርታን ቀልብ ስቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሮቤርታን ያስጨነቃት ጉዳይ አልዚመር በዕድሜ ከገፉ ሰዎች በተጨማሪ ታዳጊዎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በመጨመሩ አሜሪካ አደጋ ላይ መውደቋን መገንዘቧ ነው፡፡ ሮቤርታ በሃዘን እንደምትገልው ከሆነ 68 በመቶ ያህሉ የአልዚመር  ተጠቂዎች ሴቶች ናቸው፡፡

ትምህርቷን እንዳጠናቀቀች በአንድ አነስተኛ የስነ-አይምሮ ምርምር ተቋም የማታ ስራ አግኝታ የተቀጠረችው ሮቤርታ አንድ ምሽት በገጠማት ሁኔታ ልቧ መነካቱ እንዲህ በማለት ነበር የገለጸችው፡፡ “በዚያች ምሽት ናሙና ለመሰብሰብ ወደ እነዚህ የአልዚመር ተጠቂዎች ህክምና ስፍራ ስሄድ ሴቶቹ በሙሉ ዙሪያዬን  ከበው ይነካኩኝ ነበር፡፡ ከሰው ጋር የሚያራርቀው በሽታቸው ከእኔም ጋር አላግባባንም፡፡ መግባባት ይፈልጋሉ፡፡ከሰው ጋር መገናኘት ርቧቸዋል፡፡  ያ የሚያሣዝን ሁኔታ አሁን ድረስ በአይምሮዬ ያስተጋባል::”

“የህይወት ዘመን ስራዋ ፍሬ ያፈራው በፈጣሪዋ እርዳታ መሆኑን ስትገልጽም  ፈጣሪ ዘወትር በሩን ይከፍትልኛል፡፡ እኔም እሱ በከፈተልኝ መንገድ መንጎድ ነው፡፡” ያለች ሲሆን ለዚህም እንደአብነት የምትጠቅሰው አሪዞና በሚገኘው በሚገኘው የአካዳሚክ ፔዲያትሪክ ህክምና ማዕከል ውስጥ የላብራቶሪ ቴክኒሽያን ባለሙያ ሆኖ ለመቀጠር መቻሏን ነው፡፡ ቀለል አድርጋም “ህይወቴን በሙሉ የኖርኩት በስልጣን ተዋርድ በሚመሩ ተቋማትና ይህንኑ በሚተገብሩ ማህበረሰብ ውስጥ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ብትሄዱ ማህበረሰቡ ውስጥ ብትገባ፣በትዳር ውስጥ ብትዘልቅ፣በስራ ላይ በተዋርድ ላንተ ተብለው የተመደቡ ስራዎች አሉ፡፡ ሰዎችም ቢሆኑ በማዕረግና ያለማዕረግ ተብለው በተዋርድ ነው ስፍራ የሚሰጣቸው” ትልና “እዚያ የአሪዞና ላብራቶሪ ውስጥ ግን የተዋጣለት የመድሀኒት አዋቂ ቡድን ነበር፡፡ በዚያ ቡድን ውስጥ የስልጣን ተዋርድ አልነበረም፡፡ ስራቸውን ጠንቅቀው የሚያቁ ችሎታና ብቃት ያላቸው ሰዎች በተገቢው ቦታ ላይ ስለነበሩ ነው፡፡”

ሮቤርታ የህክምና ተማሪዎችን በላቦራቶሪ ስለሚገኙ ውጤቶች ትንተና አሰጣጥ ስታስተምር በሮቤርታ እውቀት የተማረኩ ተማሪዎች የኮሌጅ ትምህርቷን ብትቀጥል የተሻለ መምራት እንደምትችል ይነግሯታል፡፡

ይህ ነው ከማይባል የትምህርት ተቋም ተመርቃ የወጣችው ሮቤርታ እነዚህን የህክምና ተማሪዎች በእውቀት መማረኳ ይበልጥ የተበረታታችው ሮቤርታ በ25 ዓመቷ አሪዞና/Arizona ዩኒቨርሲቲን ተቀላቀለች፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላም በ1979 ዓ.ም በከፍተኛ ውጤት የዩኒቨርሲቲው ምርጥ ተማሪዎች ማህበር አባል ሆና የተመረቀች ሲሆን ትምህርቷን በዚያው ቀጥላ ከአምስት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የዶክትሬት ዲግሪዋን በእጇ አስገብታለች፡፡

የአልዚህመርን በሽታ ለመከላከልና ለማከም ይረዳ ዘንድ የፈለሰፈችውን ዘዴ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ተግባራዊ ለማድረግ ከስምንት ዓመታት በላይ መጠበቅ ግድ የሆነባት ወይዘሮ ያለእረፍት አድካሚ ሥራ መሥራት መታወቂያዋ ነው፡፡በዚህ ምክንያት ትዳሯ ቢፈርስም ‘ለስራዋና ለተቀረው ማህበረሰብ ጤና ስትል የከፈለችው ዋጋ ነው::’ ይላሉ የሥራ ጓደኞቿ፡፡

‘ይህን ዋጋ ከፍላ አልዚህመርን መግታት ባንችል ኖሮ በ42 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ45 አሜሪካዊያን አንዱ የዚህ በሽታ ተጠቂ በሆነ ነበር፡፡’ በማለት ጥረቷ ከንቱ አለመቅረቱን የሚመሰክሩት የቅርብ ወዳጆቿ ብቻ አይደሉም፡፡

ዩኤስ ኒውስ እና ወርልድ ሪፖርት/US News & World Report/ በ 2004ዓ/ም ዶ/ር ሮቤርታ ለፈጠረችው የአልዚህመር መከላከያና ህክምና ዘዴ ዕውቅና በመስጠት ‘ዘ ሜሞሪ ማቨን’ የሚል ስያሜ የተሰጠው ዘውድ ጭነውላታል፡፡

በመቀጠል ለህልሟ የተሻለ ውጤት ያስገኝልኛል ያለችውን የደቡባዊ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የፋርማኮሎጂ /Pharmacology/ ትምህርት ክፍል የተቀላቀለችው ሮቤርታ ባለፉት 22 ዓመታት ውስጥ በዩኒቨርስቲው የሚገኘውን የሳይንስ የቴክኖሎጂና የምርምር ፕሮግራም በበጎ ፍቃደኝነት እየመራች ሲሆን በዚሁ ፕሮግራም ተመራማሪ ከሆነ ሳይንቲስት ጋርም አዲስ ትዳር መስርታለች፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ለሳይንስ እንዲተጉ የሚያደርገው ይህ ፕሮግራም በተለይ ትኩረቱ የአናሳ ዘውጌ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ተማሪዎች ሳይንቲስት ሆነው አይምሮ ከማያስበው ዓለም ማዶ ያለውን እውነት ተግባራዊ ያደርጉ ዘንድ መጣር ነው፡፡

እድሜ ለሮቤርታ እልህ አስጨራሽ ጥረት ዛሬ የዚህ ፕሮግራም ተካፋይ ተማሪዎች መቶ በመቶ የታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች ታላላቅ ተመራማሪ ሆነዋል፡፡ ሮቤርታ እንደምትገልጻቸው ከሆነ እነዚህ ተመራማሪዎች ረጅም አድካሚና አስቸጋሪ ጉዞ በማድረግ ላይ ሲገኙ አንዳንዶቹም የፀነሱትን ሃሳብ በተግባራዊ ፈጠራ ለመውለድ ምጥ ይዘዋል፡፡

ሮቤርታ ከመቶ የሚበልጡ የሳይንስ ጽሁፎችን ከማሳተሟም በላይ በ ናሽናል ኢንስቲቲዩት ኦፍ ሜንታል ሄልዝ፣በ ዘ አልዝሂመር ድረግ ፋውንዴሽን እና በ ዘ ሶሳይቲ ኦፍ ኒዩሮ ሳይንስ ውስጥ አማካሪ ሆና እየሰራች ነው፡፡ ከአልዝሂመር ጋር በተያያዘ የበርካታ ህክምና ዘዴዎች ፈጠራ ባለቤት የሆነችው ወይዘሮ አንድ የባዮቴክኖሎጅ ኩባንያ ከጓደኛዋ ጋር ሆና አቋቁማለች፡፡

በአብዛኛው የአረጡ ሴቶች ላይ የሚከሰተውን አልዝሂመር ሙሉ ለሙሉ ለመከላከልና ለማከም የሚያስችል ዘዴ የፈጠረችው ሮቤርታ “ዛሬ ሁሉም ሴቶች ትልቅ ትንሽ ወጣት ህጻን ሳይባል ወደእዚህ እድሜ በደስታ ከመድረሳቸውም በላይ ያሳለፉትንም ውብ ጊዜ ማስታወስ ይችላሉ፡፡” በማለት ትናገራለች፡፡

እግዜር እንኳንም አንችን ፈጠረ!!

**ይህን ጽሁፍ በቀጥታ እንዲደርስዎት ከፈለጉ የፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ከዚያ በተጨማሪ ለሚያውቁት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪ እንዲሁ እንዲደርጉ ይንገሩልን፡፡ የኛ ፕሮጀክት ባብዛኛው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ማዕከል ያደረገ ሲሆን ተማሪዎችን ያሰለጥናል፣ የተለያዩ ሽልማት የሚያስገኙ ውድድሮችን ያካሂዳል፡፡ ውድድሩ በብሎጋችን እና በፌስ ቡክ ገጻችን ከሚወጡ ጽሁፎችን በመንተራስ የሚካሄድ ሲሆን ፤ የቲ ንቅናቄን ዓላማ ከግብ ለማድረስ በማሰብ የተዘጋጀ ነው፡፡ ውድድሩ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ይካሄዳል፡፡ 

የፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ፡ www.facebook.com/teamuvement

 ስለትብብርዎ እናመሰግናለን፡፡

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.