እኔ እርሳስ-ካለፈው የቀጠለ 3 (I Pencil -part 3)

Imageሊኦናርድ ሪድ እ.ኤ.አ በ1946 ዓ/ም ፋውንዴሽን ፎር ኢኮኖሚክ ኢዱኬሽን (FOUNDATION FOR ECONOMIC EDUCATION) አቋቁሞ ለ37 ዓመታት ያህል በፕሬዚዳንትነት ያገለገለ ሲሆን ኢንተርፕርነርሽፕን፣ የኢኮኖሚ ነጻነትን፣ እና የግለሰብን በንብረቱ ላይ የማዘዝ መብት በትጋት ሲያስተዋውቅ እና ሲያስተምር የኖረ ሰው ነው፡፡ የሊኦናርድ ሪድ ታሪክ በራሱ ነገረ ነጻነት ጎልቶ ይነበብበታል፡፡

ሊኦናርድ ሪድ 29 ያህል መጻህፍትን የጻፈ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ መጣጥፎችም አሉት፡፡ ከእነዚህ ውስጥ እኔ እርሳስ አንዱ ሲሆን ለህትመት የበቃውም እ.ኤ.አ በ1958 ዓ/ም ነው፡፡ በአንድ ወቅት ፕሬዝዳንት ሮናልድ ሬገን ዛሬ አሜሪካና ህዝቦቿ በሊኦናርድ ሪድ የነገረ ነጻነት አስተምህሮ የነቃነውን ያህል መጭው ትውልድም ሊኦናርድ ሪድን እንዲሁ ይፈልገዋል በማለት ተናግረዋል፡፡

እ.ኤ.አ  በ1976 ዓ/ም የኖቤልን ሽልማት የተቀበለው የምጣኔ ሃብት ሊቅ ሚልተን ፍሪድማን ስለ ሊኦናርድ ሪድ ‘እኔ እርሳስ’ እንዲህ ነበር ያለው፡፡ እስካሁን በጣም ግልጽ በሆነና እጥር ምጥን ባለ ገለጻ የአዳም ስሚዝን ‘የማይታይ እጂ’(Invisible Hand) ነገረ ነጻነትን እየተነፈሰ በገቢር የሚያሳይ ጽሁፍ አላነበብኩም፡፡ ‘እኔ እርሳስ’ ከሌሎቹ የሊኦናርድ ጽሁፎች በተለይ ግለሰቦች ስለራሳቸው እና ስለሚኖሩበት ሥርዓት ጠንቅቀው እንዲያውቁ የሚረዳ የነገረ ነጻነት ጥቅንጥቅ ነው፡፡

***

“‘እኔ እርሳስ’ የነጻ ገበያን ምንነት በቀላል አቀራረብ ያስረዳኝ ጥልቅ መጣጥፍ ነው፡፡ ‘እኔ እርሳስ’ን ሁሉም ቢያነብ ግማሽ ያህሉ የዓለም ምጣኔ ሃብታዊ ችግር ይወገዳል፡፡” በርቶን ፎልሰም-በሂልሳይድ ኮሌጅ የታሪክ ፕሮፌሰር

***

በጆርጅ ማሰን ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሃብት ፕሮፌሰር የሆኑት ዋልተር ዊሊያምስ ደግሞ የነጻ ገበያን ውስብስብነት በቀላሉ እና አዝናኝ በሆነ አቀራረብ የተረዳሁበት ጽሁፍ በማለት ነበር ስለ እኔ እርሳስ የተናገሩት፡፡ ግለሰቦች፣ ሚሊዮኖች  ምናልባትም ቢሊዮኖች በራሳቸው መንገድ ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ ከሚያስቡትና ከሚጥሩት በላይ ‘እኔ ኢኮኖሚውን የተሻለ አደርጋለሁ’ የሚሉትን ጅል ፖለቲከኞች እዚያው በጸበል እንላቸው ዘንድ የሊኦናርድ ሪድ ‘እኔ እርሳስ’ ይገፋፋናል፡፡    

***

(ከቲ ንቅናቄ- ክፍል 3) የኔ‹ሊድ› ራሱ የውስብስብ ስራዎች ውጤት ነው፡፡ ባይሆን ኖሮ ሊዱም አይገኝም፡፡ እስቲ ተመልከቱ፡፡ የግራፋይት (graphite) ማእድኑ የሚወጣው ሲሪላንካ ዉስጥ ሴይሎን በመባል ከሚጠራው ስፍራ ነው፡፡ የማእድኑ አዉጪ ሰራተኞችና የሚገለገሉባቸው የትየለሌ መሳሪያዎች፣ የማእድኑን መያዣ የወረቀት ከረጢቶች የሚያመርቱ ሰራተኞች፣ ለከረጢቶቹ መስፊያ የሚያስፈልጉ ክሮችን የሚያመርቱ ሰዎች፣ መርከብ ላይ ጫኞች፣ መርከቦችን የሚሰሩ ሰዎች፣ በጥንቃቄ የሚያጓጉዙ ካፒቴኖች ፣መርከቡ በጉዞ ላይ ሳለ ባህር ዉስጥ ከሚገኙ ዓለቶች ጋር እንዳይጋጭ የመርከቡ ማማ ላይ ሆነዉ የመጠቆሚያ መብራት የሚቆጣጠሩ ሰራተኞች ሳይቀሩ ለኔ ውልደት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ናቸው፡፡

ግራፋይቱ ከሚሲሲፒ ከመጣ የሸክላ አፈር ጋር ይቀላቀላል፡፡ ከዚያ የማጣራት ሂደቱን እንዲያቀላጥፍ አሞኒየም ሃድሮክሳይድ (ammonium hydroxide) ይጨመርበታል፡፡እንደ ሰልፎኔትድ ታሎዉ(sulphonated tallow) ያለ ከእንስሳት ተዋጽኦ የሚመረት ስብ ለማርጠቢያነት ሲጨመርበት ከሰልፈሪክ አሲድ( sulphuric acid ) ጋር ኬሚካላዊ ሂደት( chemical reaction ) ያካሂዳል፡፡በበርካታ ማሽኖች ዉስጥ ሂደቶችን ካለፈ በኋላ ቅልቅሉ(mixture) ልክ በማሽን እንደተፈጨ ስጋ እየተግተለተለ ይወጣል፡፡ከዚያም በተፈለገዉ መጠን (ቅርጽ) ተከፋፍሎ ይጋገርና በ 1 850ዲግሪ ፋራናይት እንዲደርቅ ይደረጋል፡፡የሊዶችን ጥንካሬና ልስላሴ ለመጨመር ከሜክሲኮ በመጣ ሙቅ ውህድ የካንደሊላ ሰም ( candelilla wax )፣የቅባት ሰም፣( paraffin wax ) እና ሃይደሮጅኔትድ በሆኑ ተፈጥሮኣዊ ስቦች(  hydrogenated natural wax ) ይታከማል፡፡

የኔ አካል የሆነዉ እንጨት (ሴዳር) ስድስት የቀለም ኮቶችን ይለብሳል፡፡ስድስት ዙር ቀለም ይቀባል ማለት ነዉ፡፡የቀለሙን ግብኣቶች( ingredients) በሙሉ ታውቁታላችሁ? እስቲ ማነዉ የጉሎ ዛፍ አብቃዮች እና የጉሎ ዘይት ጨማቂዎች በቀለሙ ዉስጥ ድርሻ እንዳላቸው የሚያዉቅ? ግና ድርሻ አላቸዉ፡፡ሌላዉ ቀርቶ ያማረ ቢጫማ መልክ እንዲኖረኝ ለማድረግና ሂደቶቹን እንኳ አንድ ሰው መጥቀስ ከሚችለው ቁጥር በላይ ችሎታዎችን የሚጠይቅ መሆኑን ብታውቁ  ይገርማችሁአል፡፡ መለያ ጽሁፉንም ተመልከቱ፡፡ ካርቦን ብላክ (carbon black) ከሙጫ (resin) ጋር በሙቀት ሀይል በመቀላቀል የሚፈጠር ስስ ሽፋን (film) ነዉ፡፡ 

ሙጫ እንዴት ይመረታል? ካርቦን ብላክስ ምንድን ነዉ?

መናኛዉ የብረት ጥምጣሜ (ጅንፎዮ) ብራስ ( brass ) ነዉ፡፡የዚንክ (zinc) እና የመዱስ (copper) ማእድን አዉጪ ሰራተኞችንና ከእነዚህ ተፈጥሮኣዊ ምርቶች አብረቅራቂ የብራስ ምንጣፎችን (shiny brass sheets) የሚሰሩ ጥበበኞችን አስተውሉ፡፡በብረቴ ላይ የሚገኙት ጥቁር ቀለበቶች ከጥቁር ኪኔል(black nickel) ይሰራሉ፡፡ጥቁር ኒኬል ምንድን ነው? እንዴትስ ነው ብረቱ ላይ ቀለበቱ የሚታተመው? የብረቴ መሃል ስፍራ ጥቁር  ኒኬል የለውም፡፡ለምን እንደሌለው በጽሁፍ ግለጽ ብባል ገጾች ያሰፈልጉኛል፡፡

አናቴ ላይ የሚገጠም ሞገስ አጎናፃፊ ዘውድም አለኝ፡፡ ላጲስ ይሰኛል፡፡ ሰዎች በሚጠቀሙኝ ጊዜ የሚፈጽሙትን ስህተቶች ፈግፍገዉ የሚያጠፉበት ነዉ፡፡ሲፈገፈግበት የማጥፋቱን ተግባር የሚያከናውነው ፋክታይ(factice) የተባለ የላጲስ መስሪያ ግብአት ነዉ፡፡ ፋክታይስ ከኢንዶኔዢያ ከሚመጣ ሬስ ከሚባል የዘር አይነት ተጨምቆ የሚወጣ ዘይት (race-seed oil) እና ሰልፈር ክሎራይድ ( sulfur chloride ) በሚያካሂዱት ኬሚካላዊ ሂደት የሚፈጠር ጎማ መሰል ምርት ነዉ፡፡ የላጲሱ አካል የሆነው ጎማ ከእርሳስ ጋ ባለው አገልግሎቱ ሰዎች ከሚያስቡት በተጻራሪ በማጣበቂያነት ከማገልገል በዘለለ ሌላ ፋይዳ የለውም፡፡ ጎማዉን ጠንካራ ለማድረግ ሂደቶቹን የሚያቀላጥፉ ግብኣቶች እጅግ ብዙ ናቸዉ፡፡ከግብኣቶቹ መካከል ፑማይስ (pumice) የሚመጣዉ ከጣሊያን ነዉ፡፡የላጲሱን ቀለም የሚወስነዉ ደግሞ ካድሚየም ሰልፋይድ (cadmium sulfide) የተባለ ኬሚካል ነዉ፡፡

ይቀጥላል…

ይህን ጽሁፍ በቀጥታ እንዲደርስዎት ከፈለጉ የፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ከዚያ በተጨማሪ ለሚያውቁት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪ እንዲሁ እንዲደርጉ ይንገሩልን፡፡ የኛ ፕሮጀክት ባብዛኛው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ማዕከል ያደረገ ሲሆን ተማሪዎችን ያሰለጥናል፣ የተለያዩ ሽልማት የሚያስገኙ ውድድሮችን ያካሂዳል፡፡ ውድድሩ በብሎጋችን እና በፌስ ቡክ ገጻችን ከሚወጡ ጽሁፎችን በመንተራስ የሚካሄድ ሲሆን ፤ የቲ ንቅናቄን ዓላማ ከግብ ለማድረስ በማሰብ የተዘጋጀ ነው፡፡ ውድድሩ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ይካሄዳል፡፡ 

የፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ፡ www.facebook.com/teamuvement

ስለትብብርዎ እናመሰግናለን፡፡

One thought on “እኔ እርሳስ-ካለፈው የቀጠለ 3 (I Pencil -part 3)

  1. Pingback: እኔ እርሳስ ክፍል 4 – ስለእኔ ጠንቅቆ የሚያውቅ ማን ይሆን? | tmuv

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.