አሳዛኙ ቢስማርካዊ የምጣኔ ሀብት ንድፍ (በዶ/ር ቶም ጂ. ፓልመር)

Image

(ቲ ንቅናቄ) በርከት ያሉ የዌልፌር ወይም የሰራተኛውን እና የባለሃብቱን ገንዘብና ጥሪት በድጎማ እና ድሆችን በመርዳት ስም ወደ ሌሎች የማስተላለፍን ፕሮግራም የተመለከቱ ጽሁፎች ባብዛኛው ከተረጂዎቹ አንጻር እንደሚታዩ እሙን ቢሆንም ይህ ጽሁፍ የሚጦምረው ግን አገራት ይህን ዓይነት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሲተገብሩ በብዙሃኑ ላይ ምን ሊያስከትል እንደሚችል መዳሰስ ይሆናል፡፡

ድጎማ ተኮር ኢኮኖሚ አሳን ያለሃላፊነት ከማጥመድ ስራ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ለምሳሌ ውሃን እና ውስጡ የሚገኙትን ዓሣዎች የሚቆጣጠር ዓካል ከሌለ ሁሉም የውሃውና የዓሣዎቹ ባለቤት ነኝ ብሎ ይነሳል፡፡ ከዚያም በውስጡ ያሉትን ዓሣዎች በተቻለው መጠን ለማጥመድ ይታትራል፡፡ሁሉም በየፊናው በርከት ያለ ዓሣ ለማጥመድ ይሯሯጣል፡፡ በዚያ ዓይነት ሂደት ብዙ ዓሣ ማጥመድ ያልቻለው ወገን እንደሱ ያለሃላፊነት የሚያጠምዱት ሰዎች ብዙ ዓሣ ያጠመዱ ይመስለዋል እንጂ የተወሰነ ብዛት እና ቁጥር ያላቸው በውሃው ውስጥ የሚገኙት ዓሦች በገደብ አልባው ዓሣ የማስገር ፍላጎታቸው ምክንያት የሚያልቁ አይመስለውም፡፡ነገር ግን ሁላችንም መገንዘብ ያለብን ዓሣን በዚህ ዓይነት መንገድ ያለገደብ ስናጠምድ ከውሃው ውስጥ በዛው ፍጥነት ዓሳዎቹ ማለቃቸውን ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ዓሣዎቹን የምናጠምድበት ፍጥነት እነሱ ሊራቡበት ከሚችለው ጊዜ እጂግ ስለሚፈጥን ነው፡፡

የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች፣ የምጣኔ ሃብት ሊቆች፣ እና ፖለቲከኞች ይህንን ‘የብዙሃኑ አሳዛን ቅስፈት’ ሲሉ ይጠሩታል፡፡  ይህ ችግር በዛሬዋ ዓለማችን ጎልቶ ለሚታየው የዓየር ንብረት ለውጥ እና የከባቢ ዓየር ነውጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው፡፡ ችግሩ ግን ከዓየር ንብረት ለውጥም በላይ ነው፡፡

ዘመናዊወቹ እርጥባን አዘል የምጣኔ ሃብት ፖሊሲ ያላቸው አገራት ድርጊት ኃላፊነት የማይሰማቸው ዓሣ አጥማጆች ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ የእነዚህ አገራት መንግስታት ከላይ እንዳያቸኋቸው ዓሣ አጥማጆች የሰራተኛውን እና የባለሃብቱን ገንዘብ ለድጎማ እያሉ የሌሎችን ጥሪት ሲነጥቁ ሃላፊነት አይሰማቸውም፡፡ ገንዘቡም እንደ ዓሣው ሁሉ የሚያልቅ አይመስላቸውም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቀላል ሲሆን እሱም እንደ ዓሣው ሁሉ ውስን መሆኑ ነው፡፡

ከላይ ዓሣ ባለማጥመዱ ምክንያት ሌሎች ግን አጥምደው ይሆናል እንዳለው መንግስት የራሱ ባልሆነ ገንዘብ አዛዥ ሆኖ እርጥባን እንዲቀበል ያልመረጠው ሰውም ሌላው(ምናልባትም ጎረቤቱ ወይም ዘመዱ) ተቀብሎ ይሆናል ብሎ ያስብ ይሆናል እንጂ የሚያልቅንና የማያዛልቅ የሌሎች ሃብት መቀራመት እስከመቼ ብሎ አያስብም፡፡

ይህን እርጥባን ለማግኘት ሁሉም ምክንያት ይደረድራል፡፡ አንዳንዶች ለመንግስት የከፈሉትን ግብር መልሶ እንደመቀበል ይቆጥሩታል፡፡ይህን የእርስ በርስ መዘራረፍ ዕውቁ ፈረንሳዊ ጋዜጠኛ  ፍሬደሪክ ባስቲያት ‘ተለዋዋጭ ዝርፊያ’ ይለዋል፡፡

ይህ ሃላፊነት በማይሰማው መንግስት የሚፈጸም ወይም የዚህ ድርጊቱን መዘዝ በአንክሮ አለማሰብ ምክንያት የአንዱን ዘርፎ ለአንዱ የመስጠት ሂደት ከቶም ዘላቂነት የለውም፡፡ ምክንያቱም ጣሊያንን ይህ ከእነ ብዙ  ህልሟ ያሰጠመ ቢስማርካዊ የምጣኔ ሃብት ንድፍ ግሪክን አንገቷን  አንቆ ይዟታል፡፡ የአሜሪካንንም ደጂ እያንኳኳ ነው፡፡

ጣሊያን ህልሟ ምን ነበር እንዴትስ ሰመጠች አሜሪካስ ወዴት እየሄደች ነው…የዚህ ጽሁፍ ቀጣይ ክፍል ይቀጥላል፡፡

ጽሁፎቹን በቀጥታ ለማግኘት የፌስ ቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ፡ https://www.facebook.com/teamuvement

በትዊተር ይከተሉን፡ https://twitter.com/TeaMovement1

ብሎጋችንን ይጎብኙ፡https://tmuv.wordpress.com

በቅድሚያ ግን ስላነበቡን ማመስገን እንወዳለን፡፡

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.