እኔ እርሳስ በ ሊኦናርድ ሪድ (I Pencil by Leonard Read)-2 ካለፈው የቀጠለ

Image

የትየለሌ ቅድመዘር

የዘር ሀረጋችሁን ወደኋላ  ርቃችሁ መቁጠር እንደምትቸገሩት ሁሉ እኔም የዘር ሀረጌን ወደኋላ ርቄ ሁሉን መጥራት እና መዘርዘር ያዳገተኛል፡፡ይሁን እንጂ እናንተ ላይ ግርምት መጫር የሚያስችለኝን ያህል የስር መሰረቴ ስፋትና ውስብስብነት በበቂ ደረጃ መጥቀስ እችላለሁ፡፡

እናም የዘር ሀረጌ በሰሜናዊ ካሊፎርኒያንና ኦሬጎን ግዛቶች ዉስጥ ቀጥ ብሎ ከሚበቅል ሴዳር(cedar) ከተባለ መአዛማ ዛፍ ይጀምራል፡፡እስቲ የሴዳርን ዛፎች ከመቁረጥ አንስቶ ግንዶቹን ሰብስቦ በባቡር ወደሚጫንበት የባቡር ሃዲድ ዳርቻ ድረስ እስከማጓጓዝ የሚያስፈለጉ ነገሮችን ሁሉ ለአንድ አፍታ አስቡ፡፡በዚህ ስራ መጋዞች፡የጭነት መኪናዎች፡ገመዶችና ሌሎች ስፍርቁጥር የሌላችዉ የማሽን አካላት ይሳተፋሉ፡፡ እነዚህን ቁሳቁሶች ለማምረት ደግሞ የሚሳተፉትን ሰዎችና የሚያስፈለገዉን አያሌ የሙያ(የችሎታ) አይነቶችን አስቡ፡፡ ከከርሰ ምድር የብረት ማእድን የማዉጣት ስራ ጀምሮ ማእድኑን ወደብረት መቀየር፡ከብረቱ መጋዞችን፡መጥረቢያዎችንና ሞተሮችን መስራት፡ወፍራምና ጠንካራ ገመድ ለማግኝት ደግሞ ለገመዱ መስሪያ ግብአት የሚሆነዉን ዛፍ ከማብቀል አንስቶ ገመዱ ተመርቶ እስኪወጣ ድረስ ያሉትን የጉዞ ሂደቶች፡በእንጨት ማቅረቢያ ካምፕ ዉስጥ የሚያስፈልጉ ነገሮች–የሰራተኞች መኝታ፡የእቃ መጋዘኖች፡ምግብ ማዘጋጃ ቤቶች፤የምግብ እቃዎች፤የምግብ ዝግጅት ወዘተ ያካትታል፡፡ይህን ሁሉ ስታስቡ እያንዳንዱ የእንጨት ሰራተኛ ከሚጠጣዉ አንዲት ስኒ ቡና ዝግጅት ጀርባ በሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እጅ እንዳለበት ለምንስ አይነገርም?

የሴዳር ግንዶቹ ሳን ሊንደሮ ፡ካሊፎርኒያ ወደሚገኘዉ የእንጨት ማሽን(ፋብሪካ) ይጓጓዛል፡፡ለማጓጓዙ ስራ አስፈላጊ የሆኑ መኪኖችን ፡ሃዲዶችን ፡የባቡር ኢንጂኖችን የሚያመርቱና የመገናኛ አውታሮችን የሚዘረጉ ግለሰቦችን ልብ ይበሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ የቅድመ ፍጥረቴ (ስሪቴ) ሰራዊቶች ናቸዉ፡፡

በሳን ሊነደሮ የሚገኘውን የእንጨት ቤተ ማሽን ሥራ እንመልከት፡፡የሴዳር እንጨት በትናንሹ ተቆርጦ በእርሳስ ቁመት ልክ ይሆንና ውፍረቱ ከአንድ ኢንች አንድ አራተኛ ባነሰ መጠን ትናንሽ ቦረዶች ይዘጋጃሉ፡፡እነዚህ (ቦርዶች) ወደ ማድረቂያ ምድጃ ይከተቱና እንዲደርቁ ይደረጋል፡፡ከዚያም ቀለም ይቀባሉ፡ቀለም የሚቀቡበት ምክንያት ሴቶች ፊታቸውን ባለቀለም ፓውደር (ዱሩላ) ከሚቀቡበት ምክንያት የተለየ አይደለም፡፡ሲታዩ እነዲያምሩ ወይም ውበታቸዉ እነዲጨምር ነዉ፡፡ቀለም የመቀባቱ እዉነታም ይሄዉ ነዉ፡፡ ከዚያም የእንጨት ቦርዶቹ ሰም ይቀቡና ዳግም እነዲደርቁ ይደረጋል፡፡ቀለምና የማድረቂያ ምድጃውን ለማምረት ሙቀት መብራትና ሃይል ቺንጊያዎችን ሞተሮችንና ለማሽኑ አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ ለማቅረብ ስንት የሙያ(ችሎታ) አይነቶች አስፈልገዋል?

የጽዳት ሰራተኞችስ ቅድመ ዘር ሐረጎቼ አይደሉምን? ናቸዉ እንጅ፡፡ የፓስፊክ ጋዝና ለቤተ ማሽኑ ሃይል የሚያቀርበው ሀይል የኤሌክትሪክ ኩባንያ የዉሃ ሀይል ማመንጫ ግንባታ ላይ ኮንክሪት ያፈሰሱ ሰዎች ሁሉ ቅድመ ዘር ሀረጎቼ ናቸዉ፡፡ ሙሉ ቦርዶችን ጭነው እና ግዛት አቋርጠው የሚያጓጉዙ ስድሳ የጭነት መኪኖችም ዘሬን ስቆጥር አልዘነጋቸውም፡፡

በአንድ ወቅት ለእርሳስ ፋብሪካው ወላጆቼ ካጠራቀሙት ጠቅላላ ካፒታል ዉስጥ አራት ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር (4,000,000 ዶላር) ያህሉን ለማሽንና ለህንጻዉ ግንባታ ኢንቨስት አድርገዋል፡፡በውስብስብ ማሽን አማካይነት በእያንዳንዱ የሴዳር ቦርድ ላይ ስምንት ቦዮች ይበጅለታል፡፡ቀጥሎ በሌላ ማሽን አማካይት በእያንዳንዱ ቦይ ዉስጥ ሊድ ይከተትና ማጣበቂያ (ኮላ) ተቀብቶ ሌላ ተመሳሳይ ቦርድ ይከደንበታል፡፡ አሁን ሊዱ ሳንዱዊች ሆነ ማለት ይቻላል፡፡ከዚያም አንድ ላይ ከተዋደደዉ የእንጨት ሳንዱዊች ሰባት ወንድሞቼና እኔ በእርሳስ ቅርጽ ተጠርበን እንወጣለን፡፡             

ይቀጥላል…

2 thoughts on “እኔ እርሳስ በ ሊኦናርድ ሪድ (I Pencil by Leonard Read)-2 ካለፈው የቀጠለ

 1. “I Pencil” is a superb case study of free markets in action. Half of the world’s economic problems would vanish id every one would read “I,Pencil.”

  Burton W.Wolfsom,Jr.

  Profesor of History

  Hillsdale College

  “I, Pencil,” as become a classic, and deservedly so. I know of no other piece of literature that so succinctly, persuasively, and effectively illustrates the meaning of both Adam Smith’s invisible hand-the possibility of cooperation without coercion.

  Milton Friedman

  Nobel Laureate,1976

 2. Pingback: እኔ እርሳስ ክፍል 4 – ስለእኔ ጠንቅቆ የሚያውቅ ማን ይሆን? | tmuv

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.