ኢትዮጵያ ኢንትርፕርነርሺፕ እና ኢንተርፕርነሮች

ቅድምት እንደ መግቢያ

በሃገራችን ኢንተርፕርነር የሚለዉ ቃል አሁን አሁን እየተለመደ ቢመጣም  ከዛሬ ቀደም ባሉት ብዙ ሺሕ አመታት ኢትዮጵያዊያን የስልጣኔን አሃዱ ለዓለም ሲያተዋውቁ የአክሱምን ሃውልት የቀረፁ፤የላሊበላን እና የጎንደር ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን የገነቡ ፤የምስርን ፒራሚዶችስ ያቆሙትስ እነሱ አይደል፡፡

 ዛሬ ያ ታላቅ ህዝብ በድህነትና ውራ ሆኖ ቢኖርም ኢንትርፕርነርሺፕና ኢትዮጵያ ግን የሚተዋወቁት ያኔ ነዉ፡፡ እኔ ግን ይሄን ጽሁፍ ያቀናበርኩት የዚያን ታላቅ ህዝብ ታሪክ ለመዘከር ሳይሆን አሁን ባለችው ኢትዮጵያ  በአስደንጋጭ ሁኔታ የተንሰራፋዉን የስራ አጥ ቁጥር በመጠኑም ቢሆን ለመቀነስ እኔ ምን ባደርግ የድርሻየን እወጣለሁ ብየ እንጅ፡፡ ለዚያ ደግሞ መፍትሄው አሁንም ታላቅ ያደረገንን ኢንተፕርነርሺፕ ወደቦታው በመመለስ እና መዋዕለ ንዋይ እሱ ላይ በማፋሰስ ኢንተርፕርነሮችን ለመፍጠር በመሞከር ነዉ፡፡

 እርስዎ ኢንተርፕርነር ሆኑም አልሆኑም  ይህ ጽሁፍ ዛሬ እጅዎ ገብቷል፡፡ በዚህ ጽሁፍ በተከታታይ የሚካተቱት ሰዎች ማንነት ያለፉበት ውጣዉረድና ስኬት አንዳች ነገር በርስዎ ላይ ሊያጭር እንደሚችል አልጠራጠርም፡፡

ስለዚህ በመጽሃፉ እርስዎ የተጓዙበትን እየተጉዋዙበት ያለዉን እና ሊጓዙበት ያሰቡበትን መንገድ በግልጥ ያዩበታል፡፡ መንገድዎን ስተዉ ከሆነ ከባለታሪኮቹ በመማር ማስተካከል እና ማሻሻል የሚገባዎትን ለማረም ይሞክሩ፡፡ ኢንተርፕርነር ሁሌም ለመማር ዝግጁ የሆነ ሰው ነው፡፡

በተጨማሪም በጽኁፉ ውስጥ በተከታታይ የሚቀርቡት ባለታሪኮች በህይዎት ያሉና እዉነተኛ ታሪካቸዉን የሚተርኩት እራሳቸዉ በመሆኑ እርስዎ ጋር እያወጉ እንዳለ ሁሉ ይሰማወታል፡፡ በርግጥ እርስዎም ጥያቄ ሊጠይቋቸው ይችላሉ፡፡ለዚህ ይረዳዎት ዘንድ አድራሻቸዉን በጽሃፉ መጨረሻ ላይ አስቀምጥልዎታለሁ፡፡ ኢንተርፕርነሮቹ ሁሉም ስኬታም ቢሆኑም የሄዱበት መንገድ የገጠማቸዉ ፈተናና የችግር አፈታት ጥበብና ዘይቤያቸው እንደ መዳፍ አሻራቸዉ የተለያየ ነዉ፡፡

ከዚያ ባለፈ ኢንተርፕርነሮቹ አንዳንዶቹ ከሃብታም ቤተሰብ የተወለዱ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ስደተኞች፤ሌሎቹ ደግሞ ከድህነት የተነሱ፤የተቀሩት የት/ቤት ደጃፍ ረግጠው የማያዉቁ አለፍ ሲልም የበቁ ምሁራን ከመሆናቸዉም በላይ ሁሉንም የእድሜ ክልል ለማካተት ተሞክሯል፡፡

 በመጨረሻም በዚህ ጽሁፍ የሚጠቀሱት ዘመኖች በሙሉ እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር መሆኑን መግለጽ እወዳለሁ፡፡

 መልካም ንባብ!

የዛሬዋ ኢንተርፕርነራችን የዛሬ ሳምንት ካቀረብኩላችሁ ሐመሮችን በመታደግ ላይ ካለችው አሜሪካዊት ወይዘሮ ጋር በስራ ዓይነትና ና በባህሪ አይገናኙም፡፡የሚያመሳስላቸው ነገር ሁለቱም ኢንተርፕርነር መሆናቸው ብቻ ነው፡፡

 Imageስም፡ ካቲ ካሴይ

የትውልድ ቦታ፡ ዋሽንግተን

የትውልድ አገር፡ አሜሪካ

የ ዘ ሲያትል ታይምስ ፓስፊክ ኖርዝ ዌስት መጽሄት አምደኛ የሆነው ግሬግ አትኪንሰን በቅርብ ጊዜ ጽሁፉ “ሕግ አፍራ ካቲ ካሴይ ኮከብ ሆነች” ሲል ገልታል፡፡ የብዙዎች ልማድና እምነት ስለሆነ ብቻ ምንም ነገር አድርጋ የማታውቀው ካቲ “አስቸጋሪና ልቅ” ስትል ነበር የቀድሞዋን ካቲን የገለፀቻት፡፡

በዋሽንግተን ጎዳናዎች ላይ እምብርቷን እያሳየች እንዲያም ሲላት ቀሚሷን እላይ ድረስ ሰንጥቃ ስትንጎራደድ ብዙዎችን አጀብ አሰኝታለች፡፡

“አንዴ እንደለመድኩት ልቅ የሆነ አለባበስ ለብሼ ስሄድ አንዲት በእድሜ የበሰሉ አሮጊት አይተውኝ ‘ዉይ የኔ ልጅ ለመሆኑ ጃኬት ነዉ እንዴ እሱ(የሰነጠቀችውን ቀሚስ እያሳዩአት)ጋር ያሸረጥሽው’ አሉኝ:: ግን እኮ ደስ ይል ነበር፡፡”

ካቲ የእናቷን ቤት ለቃ እኒያ አሮጌት መነኩሲት እንደሷ አስቸጋሪ ሴቶችን የሚገሩበት ቦታ ስትገባ እድሜዋ አስራ አምስት ብቻ ነበር፡፡በዚያም ለአስራ ሁለት መነኩሲቶች  እራት አብሳይ በመሆን የመጀመሪያ ስራዋን መጀምር ችላለች፡፡

ሥርዓት የለሽ ጯሂና ፈጣን መሆኗ ውስጧ ከታመቀው አዲስ ነገር የመፍጠር ፍላጎት ጋር ሲጋጭ መንቦግቦግ የጀመረች ‘እብድ ኢንትርፕርነር’ ናት-ካቲ የምትለው እራሷ ናት፡፡

ያ አዲስ ነገር ደግሞ አዳዲስ የምግብ አይነት ማምረትና ማዘጋጀት ነበር፡፡ፈጠራዋ ደግሞ ከትንሽ እስከ ትልቅ ስኬታማ መሆኑን የቀድሞው የኒው ዮርክ ታይምስ የምግብ ዝግጅት አምድ አዘጋጅ ክሬግ ካሊቦርን ካቲ አይን የሚማርኩ እና እጅ የሚያስቆረጥሙ ምግቦችን ፈጥራለች ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡

ካቲ ከምንም በላይ ምግብ መስራት እንደሚያስደስታት ትገልጻለች፡፡ “አዎ! እናቴና ሴት አያቴ ገንዘብ ስላልነበራቸው ያንንም ይኼንንም እየቀላቀሉ  የሚያምራቸውን ምግብ እቤት ነበር የሚሰሩት-ገንዘብ የለንማ! ለአሮጊቶቹ መነኩሲቶች ግን እንደነሱ ያንንም ይኼንንም በመቀላቀል ሳይሆን በጥንቃቄ ነበር የምሰራዉ፡፡እራት ደግሞ በመነኩሲዎቹ ትኩረት ስለሚሰጠዉ አጣፍጬ ለመስራት የምግብ ዝግጅት መጽሃፍትን ሁሉ ማገላበጥ ነበረብኝ፡፡ያን ሰርቼ እነሱን ካበላሁ በኃላ ወደ ራሴ ጉዳይ መለስ በማለት ትንሽ ሲጋራየን ጨስጨስ አድርጌ ለቀጣይ ስራዬ እዘገጃጃለሁ፡፡ ጸጉራቸዉን እና ቅንድባቸዉንም ሁሉ አስተካክላቸዉ ነበር፡፡መቼም ቆንጆ ያደረግኋቸው ይመስለኛል፡፡” ሳቅ…ሳቅ….

የካቲ ቀጣይ እቅድ የነበረው ወደ ምግብ አዘገጃጀት ት/ቤት  ማቅናት ነበር፡፡አንድ አስተማሪዋ “ካቲ ሼፍ እሆናለሁ ብለሽ አትድከሚ፡፡በፍጹም አንች ሼፍ መሆን አትችይም ይልቅስ አንች የሚያምርብሽ እንደምትፈልጊው ቂን ቂን ስትይ ነው፡፡” እንዳላት የምትናገረው ካቲ አይን አይኑን እያየች “እንደዚህማ አትበል! እኔ ሼፍ እሆናለሁ፡፡ ያውም ታዋቂ ሼፍ፡፡ከፈለክ አሁኑኑ ለውርርድ አምስት መቶ ዶላር ልናስይዝ እንችላለን፡፡”እንዳለችው እያስታወሰች “ዛሬ እሱ በሕይዎት ባይኖርም የኔ እዳ ግን አለበት፡፡”ብላለች፡፡

ካቲ በ1980ዎቹ አጋማሽ ላይ ስመ ጥር ሼፍ ከመሆኗም በላይ ዛሬ በስራዋ አሜሪካ አሉኝ ከምትላቸው የሙያው ባለቤቶች የመጀመሪያዋ እንስት መሆን ችላለች፡፡ካቲ የተለያዩ የምግብ አይነቶችን እየቀላቀሉ አዲስ የምግብ አይነት የመፍጠር ህልሟን ዕውን ለማድረግ ከሲያትል ወደ ኒዉዮርክ በማቅናት በአንድ ሬስቶራንት ዉስጥ ስራ ብትጀምርም ይህ ስራዋ በቀጣሪዋ ስላልተወደደ ወዲያው ከስራ ልትባረር ችላለች፡፡

በዚህ ወቅት ካቲ ወደ ሌላ ስፍራ ስራ ፍለጋ ለመሄድ አልተነሳችም፡፡ወደ ሲያትልም አልተመለሰችም፡፡

የዚህ ጽሁፍ የመጨረሻ ክፍል ይቀጥላል፡፡

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.