ሐመሮችን በመታደግ ላይ ያለች አሜሪካዊት ወይዘሮ-2

ካለፈው የቀጠለ…

ሐመሮች ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ የሚሰራ ስራ ሊከወን የሚችለው ሐመሮች እራሳቸው በሚቀምሩት መፍትሄ እንጅ ከሰለጠነው ዓለም በሚቀዳ የችግር መፍቻ ዘዴ  አይደለም፡፡ እንዲህ ያለው አሰራር ለሐመር አይሰራም፡፡ቁምነገሩ ሐመሮች ራሳቸው ለራሳቸው ዉስብስብ ችግር መፍቻ አለን የሚሉት መፍትሄ ምንም ይሁን ምን፤እነሱን ለመታደግ ያልተለመደ አሰራርን ሁሉ መከተል ሊኖርባት እንደሚችል የተገነዘበችው ሎሪ እንዲህ ትላለች፡፡

 “እናም ያለኝን አቅምና ችሎታ ሁሉ ተጠቅሜ የተለየ ነገር ማድረግ አለብኝ አልኩ፡፡እዚህ(አሜሪካ) ከኔ ጋር የሚተዋወቁት ችግር የችግር መፍቻ ጥበቦች እዚያ ቦታ የላቸውም፡፡ምክንያቱም እየሰራን ያለነው እጅግ በጣም የተወሳሰበ ችግርን ለማቃለል ነው፡፡የባሕል አለመተዋወቅ፤ከማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓቱ ጋር አለመጣጣም በዚህ ላይ ደግሞ የምግብና የውሃ ችግርም አለ፡፡በዚህ ባበቃ መልካም ነበር ግን በቋንቋ ረገድም ሆነ የጊዜን አጠቃቀም በሚመለከት የሚታወቅ ነገር የለም፡፡የመጓጓዣ ነገር ካነሳህ ብቸኛው ምርጫህ እግርህን መጠቀም ነዉ፡፡የመብራት አገልግሎትም ፈጽሞ የለም፡፡”   

 እዚህ ላይ ሎሪ ይህን ሁሉ ችግር ለመጋፈጥ ‘ደንበኝ ንጉስ ነዉ’ የሚለው እምነቷ በጣም የጠቀማት ሲሆን ለችግሩ መፍትሄ ይሆነኛል የምትለውንም ቀመር ለመቀመር ‘የችግሩ ባለቤት እና ኃላም የመፍትሄው ተጠቃሚ’ የሚሆነው ሐመር ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት አልተጠራጠረችም፡፡

 ሎሪ  ስትጥል ስታነሳ የከረመችውን ሃሳብ እውን ለማድረግ ጉዞ ሆነ፡፡ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ከዚያ ወደ ሐመር ምድር፡፡

 ከአካባቢው ሽማግሌዎች ጋር እየተማከረች ሁኔታዎችን እየታዘበች እና ጥያቄዎቿን እያቀረበች ለዓመታት በድንኳን ውስጥ ለመኖር ተገደደች፡፡  የሐመር የሃገር ሽማግሌዎችን “የኑሮ ዘይቤያችሁ ለምንድነው የሐመርን ሕይዎት ቀጣይነት ጥያቄ ውስጥ የዶለው?”  ስትል ጠይቃቸዋለች፡፡ ቀስ በቀስ በሐመሮችና በእሷ መካከል ያለው መተማመን እየጎለበተ መጥቶ የሃገር ሽማግሌዎቹ የማህበረሰቡን ጤና ለማሻሻል ከእሷ ድርጅት ጋር አብረው ለመስራት ተስማሙ፡፡

 በስምምነታቸው መሰረት በመጀመሪያ ደረጃ ለሐመሮች ምግብ መግዣ ይሆናቸው ዘንድ ለመዋቢያ የሚጠቀሙባቸዉን ጌጣጌጦች ወደሰለጠነዉ ዓለም ወስዶ ለመሸጥ ጂቲኤልአይ/GTLI የተባለ መስመር መዘርጋት ነበረባት፡፡ሆነ፡፡ቀጣዩና ዋነኛ ችግር የነበረውና የሆነው በማሕበረሰቡ ዘንድ የባህሪ ለውጥ ማምጣት ነዉ፡፡ የህ ደግሞ በየሜዳው ከመጸዳዳት አንስቶ እስከ አጠቃላይ የንጽህና አጠባበቅ ጉድለት ሲሆን አነስተኛ የሽንት ቤት ጉድጓድ እና የእጅ መታጠቢያ በማዘጋጀት እንዲገለገሉበት ተደርጓል፡፡

የኑሮ ዘይቤያቸውን ለመቀየር የሚደረገው ጥረት እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሲሆን ማሕበረሰቡ ጤናማ ሆኖ ይቀጥል ዘንድ ግን ያ ለውጥ የግድ አስፈላጊ ሆኗል፡፡

 ዛሬ ሎሪ ኑሮዋን በሃገሪቱ መዲና አዲስ አበባ እና በሐመሮች አካባቢ በተከለችው ድንኳን ዉስጥ አድርጋለች፡፡

 የሐመር የማህበረሰብ ሰራተኞችም ስልጠና የወሰዱ ሲሆን አነስተኛ ቡድኖችንም በመምራትም የየቡድናቸዉን ችግርና መፍትሄ እንዲወያዩበት ተደርጓል፡፡

ይህ ጥሩ ብልሃት በሚገባ እየሰራ ያለ ነው፡፡ቀስበቀስም እነዚህ የቡድን መሪዎች የየቡድናቸው አባላት የግንዛቤ ለዉጥ ያመጡ ዘንድ ግፊት እያደርጉ ሲሆን ሐመሮችም እነዚያ በዓይን የማያዩአቸዉ ተህዋስያን በሽታ እንደሚያመጡባቸው እየተገነዘቡ ነው፡፡

 “ከጊዜ ወደጊዜ መሻሻል እየታየ ነዉ፡፡” የምትለዉ ሎሪ “ከፈጠራ ችሎታየ በተጨማሪ በጣም…በጣም ታጋሽ መሆን እንዳለብኝ ነዉ ተረዳሁት፡፡ይህ ደግሞ እንደኔ አይነት ስብእና ላለው ሰው ቀላል አይደለም፡፡ሆኖም ግን በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ‘ማድረግ’ ሣይሆን ‘መሆን’ እንዳለብኝ ተማርኩ፡፡ ያ ደግሞ በእውነት ታላቅ ስጦታ ነው፡፡”

አዎ! ሐመሮችን መሆን ያልቻለ ለሐመሮች አንዳች ማድረግ አይችልም፡፡እግዚአብሔር ሐመሮችንና ሃገራቸው ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

2 thoughts on “ሐመሮችን በመታደግ ላይ ያለች አሜሪካዊት ወይዘሮ-2

  1. Pingback: ሐመሮችን በመታደግ ላይ ያለች አሜሪካዊት ወይዘሮ-2 « tmuv

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.