ሐመሮችን በመታደግ ላይ ያለች አሜሪካዊት ወይዘሮ

Image

ስም፡ ሎሪ ፓፓስ

ስራ፡የግሎባል ቲም ፎር ሎካል ኢኒሺየቲቭስ መስራችና ሊቀመንበር

የትውልድ ቦታ፡ ሚኖሶታ

የትውልድ አገር፡ አሜሪካ

ሎሪ ፓፓስ ዓመቱን የምታሳልፈው በአብዛኛው የምታሳልፈዉ ደረቅና ቆላማ የአየር ንብረት ባለው የኢትዮጵያ ደቡብ ክፍል ነዉ፡፡እኒህ ወይዘሮ ድሎት ከተትረፈረፈባት ሃገረ-አሜሪካ መጥተዉ በኢትዮጵያ ድንኩዋን ዉስጥ ለማሳለፍ የተገደዱበት ምክንያት እሳቸው እንደሚሉት “ከዘመናዊው ዓለም ጋር ምንም ቁርኝት የሌላቸዉን ሃመሮችን ለመርዳት ነው፡፡”

ወይዘሮዋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሐመሮች እና ከአካባቢያቸው ጋር የተዋወቀችው የበጎ ፍቃድ ሰራተኛ ሆና በ 2007 ዓ/ም ኢትዮጵያ በመጣችበት ወቅት ነበር፡፡ በወቅቱ ሐመሮች ከፊታቸዉ የተደቀነባቸውን አስከፊ ድርቅና ሊዛመት የሚችልን ወረርሽኝ በመፍራት የመኖር ተስፋ ከፊታቸው ተሟጦባቸው ሲጨነቁ ማየት በጣም ይረብሻል፡፡

ሆኖም ሐመሮች ለሕይወታቸው ዋስትና የሚሰጥና ፋይዳ ያለዉ ለዉጥ የሚያመጣ ድጋፍ ሊያገኙ አለመቻላቸዉ አሜሪካዊቷን ወይዘሮ በጉዳዩ ላይ እንዲያስቡበት ምክንያት ሆናቸው፡፡

 ሎሪ ይህን ሃሳቧን ወደተግባር መቀየር እንደማያቅታት የኋላ ታሪኳ ይናገራል፡፡ ገና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን እንደጨረሰች በመዝገብ ቤት አደራጅነት የተቀጠረችው ሎሪ ካለችበት የስራ ደረጃ ወደ ሌላ ከፍ ለማለት ሦስት ቀናት ብቻ ነበር የፈጀባት፡፡ከዚያም ባደራጀችዉ መዝገብ ቤት ውስጥ ሰራተኛ ሆና የኩባንያውን የመዝገብ አያያዝ ሥርዓት ኮምውተራይዝድ አድርገዋለች፡፡ ከዚያ በኋላ ባገኘችው ተከታታይ የሥራ እድገትም የኩባንያውን ተለምዶአዊ የአሠራር ሥርዓት እስከ ምርት ክፍል

ድረስ ያሉትን ሂደቶች በሙሉ ኮምፒውተራይዝድ በማድረግ የዘመኑን ቴክኖሎጂ የተላበሱ እንዲሆኑ አድርጋለች፡፡  ይሄን ኩባንያ ለቃ በ1970ዎቹ Olivetti ኩባንያ ውስጥ በሽያጭ ሰራተኝነት የተቀጠረችው ሎሪ ብዙም ሳይቆይ በአሜሪካ ግዛቶች ከሚገኙ የኩባንያው የሽያጭ ሰራተኞች ሁሉ ልቃ ተገኝታለች፡፡ እሷ እራሷ እንደምትለዉ “እኔ የደንበኛን ንጉስነት ሳላቅማማ ነዉ የምቀበለው፡፡ይሄ ደግሞ ደንበኞችህን ለመርዳት እና በሚፈልጉት ጉዳይ ሁሉ ከጎናቸው እንድትሆን ያስችልሃል፡፡”

 ይሄን ልምድና በትምህርት ቤት የቀሰመችውን እዉቀት በማዳበል አብሯት የኖረዉን ህልሟን እውን ያደረገችው ሎሪ በ1984 Job Boss የተባለ የሶፍትዌር ኩባንያ መስርታለች፡፡

 “እድለኛ ነበርኩ፡፡በወቅቱ አባቴ ለእህቶቼ እና ለእናቴ ለእያንዳንዳቸዉ ሦስት ሦስት ሺሕ ዶላር ሰጥቷቸው እኔን የገንዘቡ ባላደራ አድርጎኝ ነበር፡፡እኔ ግን አደራየን በላሁና ገንዘቡን ተቀብየ Job Boss ን ለመመስረት ተጠቀምኩበት፡፡”

 ሎሪ Job Boss ን ባቋቋመች በጥቂት ወራት ጊዜ ዉስጥ የወሰደችውን ገንዘብ የመለሰች ሲሆን ድርጅቷም ለተከታታይ 20 ዓመታት Inc. Magazine ምርጥ ከሚላቸው ኩባንያዎች አንዱ ምርጥ ኩባንያ በመሆን መዝለቅ ችሏል፡፡

በ1999 ዓ/ም ሎሪ Job Boss ን ብትሸጠውም ልብ የሚሰብሩ ሁነቶችን በዓይኗ ያየችበት ወደ አፍሪቃ ያደረገቻቸው ጉዞዎች ከአሜሪካዊያኑ ጎልፍና ቸበርቻቻ ይበልጥ ልቧን ሰቅዞ ይዞት ኖሯል፡፡

 በዚህ ምክንያት እንደገና ያካበተችውን የስራ ልምድና የፈጠራ ችሎታዋን እና ክህሎቷን በመጠቀም ለቁጥጥር አስቸጋሪ የሚባሉትን አይነት ዓለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ለማቋቋም ተፍ ተፍ ማለት ጀመረች፡፡

 ይህ ድርጅት ግሎባል ቲም ፎር ሎካል ኢኒሺየቲቭስ ሲሆን የሚቋቋመዉ በኢትዮጵያ ደቡባዊ ክፍል የሚገኙት ሐመሮች እራሳቸውን የሚችሉበትን መንገድ ለማመቻቸት እና ሐመሮች የዉጭ እርጥባን ናፋቂ እንዳይሆኑ ለማድረግ ነዉ፡፡

ሎሪ ከዚህ በፊት ያየቻቸው አሰራሮች ዘላቂነት ላይ ጥያቄ ስለነበራት ይህ ውጥኗ ቀላል የማይባል ፈተና እንደሚገጥመው ቀድማ ተረድታለች፡፡

“ቫይታሚንና ጸረ ትላትል እንክብሎችን ማደል ለነዚህ ሰዎች ችግር ዘላቂነት ያለው መፍትሄ አይደለም፡፡ ማድረግ ያለብን ነገር በተቻለ መጠን ራስን የማስቻል ስራ መስራትና የባህሪ ለውጥ እንዲመጣ ጥረት ማድረግ ነው፡፡” ትላለች-ሎሪ፡፡

ሐመሮች ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ የሚሰራ ስራ ሊከወን የሚችለው ሐመሮች እራሳቸው በሚቀምሩት መፍትሄ እንጅ ከሰለጠነው ዓለም በሚቀዳ የችግር መፍቻ ዘዴ  አይደለም፡፡ እንዲህ ያለው አሰራር ለሐመር አይሰራም፡፡ቁምነገሩ ሐመሮች ራሳቸው ለራሳቸው ዉስብስብ ችግር መፍቻ አለን የሚሉት መፍትሄ ምንም ይሁን ምን፤እነሱን ለመታደግ ያልተለመደ አሰራርን ሁሉ መከተል ሊኖርባት እንደሚችል የተገነዘበችው ሎሪ እንዲህ ትላለች፡፡

“እናም ያለኝን አቅምና ችሎታ ሁሉ ተጠቅሜ የተለየ ነገር ማድረግ አለብኝ አልኩ፡፡እዚህ(አሜሪካ) ከኔ ጋር የሚተዋወቁት ችግር የችግር መፍቻ ጥበቦች እዚያ ቦታ የላቸውም፡፡ምክንያቱም እየሰራን ያለነው እጅግ በጣም የተወሳሰበ ችግርን ለማቃለል ነው፡፡የባሕል አለመተዋወቅ፤ከማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓቱ ጋር አለመጣጣም በዚህ ላይ ደግሞ የምግብና የውሃ
ችግርም አለ፡፡በዚህ ባበቃ መልካም ነበር ግን በቋንቋ ረገድም ሆነ የጊዜን አጠቃቀም በሚመለከት የሚታወቅ ነገር የለም፡፡የመጓጓዣ
ነገር ካነሳህ ብቸኛው ምርጫህ እግርህን መጠቀም ነዉ፡፡የመብራት አገልግሎትም ፈጽሞ የለም፡፡”   

ይቀጥላል…

 

 

Thank you for your comments

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.